Hiber Radio: የዘሐበሻ አዘጋጆች ለሀብታሙ አያሌው ሕክምና ያሰባሰቡትን ከ28 ሺህ ዶላር በላይ አስረከቡ፣ አስተዋጽዎ ያደረጉትን በሙሉ አመስግነዋል

ለቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፈ አቶ ሀብታሙ አያሌውን ወደ ሰሜን አሜሪካ መጥቶ እንዲታከም በስሙ ገንዘብ ጎ ፈንድ ሚ በመክፈት ካሰባሰቡት የዘሐበሻ አዘጃጆች አንዱ ለጎ ፈንድሚና ለመላኪያ ከጣው ከወጪ ቀሪውን ከ28ሺ በላይ ዶላር ማስረከባቸውን ለማወቅ ተቻለ።

ለሐብታሙ አያሌው ከአገር ሲወታ ለማሳከም የተሰበሰበውን ገንዘብ በሃላፊነት በጊ ፈንድሚ አካውን በመክፈት የራሳቸውን አስተዋጽዎ ጨምሮ አስተባበሩት የዘሐበሻ አዘጋጆች ከጥቂት ሳምንታት በፊት እንዲዘጋ አድርገው ለሕክምናው ለጊዜው የወጣ ወጪ ባይኖርም ሕክምናው ወደፊትም ቀጣኢ በመሆኑ የተሰበሰበውን ገንዘብ ለሀብታሙ መድረስ ስላለበት ባለፈው ሳምንት በባንክ ጎ ፈንድ ሚ ከቆረጠው የአገልግሎት ከቀረውን $29,012.52 ሲሆን wire ማድረጊያው $30.00 ተቀንሶ $28, 892.00 በአቶ አለማየሁ በከል ለሀብታሙ አያሌው እንዲደርስ አድርገዋል።

ሀብታሙ አያሌውን ለመርዳት ከአገር ቤት ከመወጣቱ በፊት በመጀመሪያው ዙር በተደረገው የጎ ፈንድ ሚ የዕርዳታ ማሰባሰብ የተገኘውን ሙሉ ለሙሉ ከ21 ሺህ ዶላር በላይ ከወጪ ቀሪ ተልኮ እንደደረሰው ራሱ አቶ ሀብታሙ ከእስር ቤት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህብር ሬዲዮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ሀብታሙ አያሌውን ለመርዳት የዘሐበሻ አዘገጆች፣የሰሜን አሜሪካ አንድነትና ጥቂት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ያደረጉትን ጥሪ መሰረት አድርገው በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሀብታሙን ለመርዳት ላደረጉት አስተዋጽዎ አዘጋጆቹ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዛሬም በወያኔ የግፍ እስር ቤት ስቃይ እተቀበሉ ያሉ ወገኖችን በማሰብ ቤተሰቦቻቸውን መደገፍና ማስታወስ እንደሚገባ ገንዘቡን ከላኩበት ሰነድ ጋር የላኩልን ማስታወሻ ይገልጻል።

ሀብታሙ አያሌው ወደፊት አስተዋጽዎ ያደረጉትን ወገኖችን የሚያመሰግንበት ልዩ መድረክ እንደሚኖር በቅርቡ ለህብር ሬዲዮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ መግለጹ ይታወሳል። ከግርጌ ለሀብታሙ አያሌው በወልስ ፋርጎ ባንክ አማካኝነት ለአቶ አለማየሁ አበበ የተላከበትና በጎ ፈንድ ሚ አጠቃላይ የተገኘውን ገንዘብ የሚያሳየው ሰነድ ተያይዘ ቀርቧል።

ተያይዞም ሀብታሙ አገር ቤት ሳለ በመጀመሪያው ዙር በዘሐበሻ አዘጋጆች አማካኝነት የተሰበሰበው ገንዘብ የተላከለት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ይህንኑ ያረጋገጠበት ቃለ መጠይቁም ሊንክ ለማስታወስ ተያይዞ ቀርቧል።

ህብር ሬዲዮ በቅርቡ ከሀብታሙ አያሌው ጋር ሰፋ አለ ቃለ መጠይቅ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከዩቱብ ማዳመጥ ይቻላል

 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *