Hiber Radio: የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም መልስ ያላገኘው ሕዝብ ተመሳሳይ ተቃውሞና አመጹን ይቀጥላል ተባለ፣ወጣቶች ለነጻነት ትግል ዛሬም መሳሪያ አንስተው በረሃ መውረዳቸው ተገለጸ፣ግዙፉ የናይጄሪያዊው ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ400 በላይ ኢትዩጵያኖችን ያለ ስራ ዋስትና አባረራቸው፣በባህር ዳር በአጋዚ በግፍ የተገደሉ ሰማዕታትን ለማሰብ የተጠራውን አድማ ተከትሎ ውጥረት ነግሷል፣ኢህአዲግ ጦሩን ቁልፍ ወደ ሆነች የሶማሊያ ግዛትሰሞኑን ላከ፣በሆድ እቃው ውስጥ አደንዛዥ እጽ ሸሽጎ ለማለፍ የሞከረ ተጓዥ በኢትዮጵያ አውሮፕላን ውስጥ መሞቱ አነጋጋሪ ሆነ እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 30 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመታወጁ 10 ዓመት በፊት በአገሪቱ ከምርጫ 97 በሁዋላ የሆነውን ማየት ያስፈልጋል። ሕዝቡ በጸረ ሽብር አዋጁ፣በአፈናው፣በመያድ አዋጁ በየትኛውም መንገድ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ሀሳቡን እንዳይገልጽ የተደረገበት ገደብ አድጎ አፈና ሲበዛ በአደባባይ ለተቃውሞ ለዚያ የተሰጠው ምላሽ ተጨማሪ አፈና ሲሆን ወደ አመጽና ብጥብጥ አድጓል …ዛሬም የተለወጠ ነገር የለም የተለመደ አፈና ካለ ስርዓቱ ራሱ ለመለወጥ ካልፈለገ ሕዝቡ ስርዓቱን …>  የአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህሩና ጦማሪው ስዩም ተሾመ  ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ያድምጡት)

<…በባህር ዳር በአንድ ቀን የፈሰሰው የንዩሃን ደም የሚረሳ አይደለም ሕዝቡ ሰማዕታቱን ሲያስብ አደራቸውን መርሳት የለበትም…የለውጥ ፈላጊው ተቃዋሚ እርምጃን በተለይ የእውነተኛ ትብብር አለመኖር አንዱ ከአንዱ ጋር ተባብሮ ያለመስራቱን በተመለከተ በተለይ ሚዲያው ግልጽ ውይይት የሚደረግበትን የህዝቡ ትግል በእውነት የሚደገፍበትን ለለውጡ የሚደረገው እንቅስቃሴ ትርጉም ያለው እንዲሆን ሀላፊነት ያለባችሁ ይመስለኛል…  > አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ  በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጠን ማብራሪያ(ቀሪውን ያድምጡት)

የኢትዮጵያዊቷ አትሌት አሳዛኝ የባህር ማዶ ኑሮ ሲፈተሽ

“እንደ አሮጌ ቁና ተጣልኩኝ፣እንደ ባሪያ ነበር የተቆጠርኩት” (ልዩ ዘገባ)

<…በደህነት መ/ቤት ውስጥ የነበሩ ሁለት የትግራይ ተወላጆች ተጋጩ ፤የግጭቱ መነሻ አፋር የኔ የጨው ማምረቻ አካባቢ እሱም ከፍቷል ያ አካባቢ የኔ ነው ለአፋሮቹም ነግሬያቸዋለሁ የሚል ነው።አፋሮቹ በጨው ላይ ስልጣን ሳይኖራቸው ሁለቱ የኔ ግዛት ነው በሚል ይጣሉ ነበር። የሙስናው ዘመቻ እነሱን አይነካም ሌላውን ለማጥቂያ ካልሆነ…> የቀድሞው የአማራ ክልል የደህነት ሀላፊ አቶ አያሌው መንገሻ ከሰጡት ሰፋ ያለ ማብራሪያ(ክፍል ሁለት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም መልስ ያላገኘው ሕዝብ ተመሳሳይ ተቃውሞና አመጹን ይቀጥላል ተባለ

ወጣቶች ለነጻነት ትግል ዛሬም መሳሪያ አንስተው በረሃ መውረዳቸው ተገለጸ

ኢህአዲግ በህዝቡ ላይ ጥሎት የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተንስቷል ቢልም የህጉ ሰለባዎች ዛሬም እየማቀቁ ይገኛሉ

በባህር ዳር በአጋዚ በግፍ የተገደሉ ሰማዕታትን ለማሰብ የተጠራውን አድማ ተከትሎ ውጥረት ነግሷል

ከቦንቡ ፍንዳታዎች ጀርባ የሕወሃት ደህነቶች ተጠርጥረዋል

ግዙፉ የናይጄሪያዊው ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ400 በላይ ኢትዩጵያኖችን ያለ ስራ ዋስትና አባረራቸው

“መስራት እየቻልን በጠባብ ፓለቲካ ሳቢያ ውንብድና ተፈጽሞብናል”የእርምጃው ሰለባዎች አቤቱታ በከፊል ሲነበብ

የኢህአዲግ አገዛዝ በ አ/አ በሰሜን ኮሪያ ዲፕሎማቶች እና ወታደራዊ ባለሙያዎች ላይ ቁጥጥር ማድረግ ጀመረ

ኢህአዲግ ጦሩን ቁልፍ ወደ ሆነች የሶማሊያ ግዛትሰሞኑን ላከ

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በድንበር ምክንያት ግጭቶች መበራከታቸውን የዶ/ በየነ ጴጥሮስ ፓርቲ ገለጸ

ሰማዕታቱ ሲታሰቡ የተነሱለት ዓላማ ሊታወስ እንደሚገባ ተገለጸ

በሆድ እቃው ውስጥ አደንዛዥ እጽ ሸሽጎ ለማለፍ የሞከረ ተጓዥ በኢትዬጵያ አየሮፕላን ውስጥ መሞቱ አነጋጋሪ ሆነ፣

አትዬጵያኖችን በህገውጥ መንገድ ሲያሸገገር የነበር ግለስብ ኬኔያ ውስጥ ህይወቱ በጠፋ ወገናችን ጉዳይ በፓሊስ አየተፈለገ ይገኛል

እና ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *