Hiber Radio: ጎንደር ሕብረት ወያኔ ጎንደርና ቅማንትን ለመከፋፈል ማሰቡን ትቶ ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ ጠየቀ፣የአሜሪካው ፕ/ት ዶናል ትራምፕ ” ሕይወታቸው በሰው እጅ ያልፋል” ያሉት የህዝብ እንድራሴ ታላቅ ተቃውሞ አስነሱ፣በኦሮሚያ ክልል ከረቡዕ ነሐሴ 17 ጀምሮ ለአምስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠራ ማስጠንቀቂያም ተላልፏል፣የባሕር በር አልባዋ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገር ወደብ ለመግዛት እየተደራደረች ነው፣በአገር ቤት የአዲስ ዓመት ኮንሰርቱ ለታገደበት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በመላው ዓለም በማህበራዊ ሚዲያው ዳግም ሊከበር ነው፣በካናዳ በአሰቃቂ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው የጠፋውን ሶስት ልጆች አስከሬን ለማጓጓዝ የድጋፍ ጥሪ ቀረበ፣እነ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ለቀረበባቸው የፍርድ ቤት ማዘዣ ተገዢ የመሆናቸው ጉዳይ እያጠራጠረ ነው እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 14 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…ወያኔ ጎንደርን ብቻ ሳይሆን ለራሱ እንዲያመቸው ሁሉንም ለመከፋፈል ሞክሯል።ጎንደርን በአራት ለመክፈል ያሰቡት  ወልቃይትን ጨምሮ የትግራይ አካል አድርገው በጉልበት ለማስቀረት ነው። ይሄ የጀመሩት ከፋፍሎ ለማዳከም መሞከርን ሕዝቡ ነቅቶበታል ከዚህ በፊት እንዳደረጉት አንድ የሆነውን አማራውና ቅማንቱን ለማታኮስ ማሰባቸው የትም አያደርስም።የተጀመረው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል ይልቅ የሚበጃቸው ለትውልድ የሚተርፍ ጥፋት ሳያስከትሉ በፊት…> አቶ አበበ ንጋቱ የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የስራ አስፈጻሚ ሊቀመንበር በወቅታዊ ጉዳይ ከህብር ጋር ያደረጉት አጠር ያለ ቃለ ምልልስ(ቀሪውን አዳምጡት)

<…በሕግ ፊት ትራምፕም አንድ ግለሰብም ያላቸው መብት ዕኩል ነው። ትራምፕ ይሄ የሚናገረውን ሁሉ እንደልቡ የሚናገረው   የግለሰብ የመናገር መብቱን ጠብቆ የተናገረው ነው።በሕግ ፊት ከሌላው ግለሰብ ዕኩል ነው። ከዚህ ውጭ ግን በተለይ ምርጫውን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር የፈጠረው ግንኙነት በተመለከተ ቢዘገይም የተጀመረው ምርመራ …የሰሞኑ የነጭ ዘር የበላይ ነው የሚሉ የናዚ ደጋፊዎች በተለይ ወደ ግችት የሄዱበት ሁኔታ ከዚህ በሁዋላ በሌላ ቦታ እንዳይደገም ትልቅ ጥንቃቄ የሚያደርጉ ይመስላል።ከዘህ ቀደምም በተመሳሳይ…> ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም በሰሞኑ የነጭ የበላይነት አቀንቃኝ ዘረኞች ስለተፈጠሩት ግጭቶችና ስለ ፕ/ት ትራምፕ አስተያየት ተጠይቀው ከሰጡን ምላሽ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

የኢትዩ- ጃዝ አባት የሆነው አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ እና አስገራሚ ገድሎቹ ሲፈተሹ (ልዩ ጥንቅር)

 <…የቴዎድሮስ ራዕይ ቴዎድሮስን እንደ ሰው የምናይበት ታላቅ ቴአትር ነው።ቴአትሩን አውሮፓ ይዘን የምንሄደው ግን…እኔ ስሞት አበባ ከሚያኖሩልኝ ይሄን ትልቅ ስራ የሰራ ጣይቱ የጥበብ ማዕከልን ቢደግፉልኝ፣የእቴጌ ጣይቱን ሐውልት በአዲስ አበባ ለማቆም የምናደርገውን ጥረት ቢያግዙኝ ትልቅ ድጋፍ ነው። የአውሮፓው የቴዎድሮስ ራዕይ ቴአትር የሚታይባቸው ስምንት ከተሞች…> አርቲስት ዓለም ጸሐይ ወዳጆ ስለ አውሮፓው የአዲሱ ዓመት የቴዎድሮስ ራዕይ ጉዞዋና ተያያዥ ጉዳዮች ከሰጠችን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን አዳምጡት)

 ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ጎንደር ሕብረት ወያኔ ጎንደርና ቅማንትን ለመከፋፈል ማሰቡን ትቶ ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ ጠየቀ

የአሜሪካው / ዶናል ትራምፕህይወታቸው በሰው እጅ ያልፋልያሉት የህዝብ እንድራሴት ታላቅ ተቃውሞ አስነሱ

ትራምፕ ማለት ለእኔ  የጭንቀት እና የሰመመን ምክንያት ናቸውሴናተር ማሪያ

በኦሮሚያ ክልል ከረቡዕ ነሐሴ 17 ጀምሮ ለአምስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠራ ማስጠንቀቂያም ተላልፏል

አድማውን ሌሎች በወያኔ የተበደሉ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ተላለፈ

የባሕር በር አልባዋ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገር ወደብ ለመግዛት እየተደራደረች ነው

የጅቡቲ ወደብ ዋጋ ያስመረረው ሕወሓት/ኢህአዲግ ሱዳንን እያግባባ ነው

በአገር ቤት የአዲስ ዓመት ኮንሰርቱ ለታገደበት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በመላው ዓለም በማህበራዊ ሚዲያው ዳግም ሊከበር ነው

የአ/ እና የአስመራ ገዢዎች 40 ሜትር የራዲዮ ሞገድ ላይ እየተፋለሙ ናቸው ተባለ፣ የሕወሓት/ኢህአዲግ የኤርትራ የራዲዮን ሞገድን እያወከው ነው ተብሏል

በካናዳ በአሰቃቂ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው የጠፋውን ሶስት ልጆች አስከሬን ለማጓጓዝ የድጋፍ ጥሪ ቀረበ

አንጋፋው የሚዚቃ ባለሙያ ሙላቱ አስታጥቄ በቬጋስ የሙዚቃ ስራዎቹን አቀረበ

እነ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ለቀረበባቸው የፍርድ ቤት ማዘዣ ተገዢ የመሆናቸው ጉዳይ እያጠራጠረ ነው

የአ/አ እና የአስመራ ገዢዎች በ40 ሜትር የራዲዮ ሞገድ ላይ እየተፋለሙ ናቸው ተባለ፣ የሕወሓት/ኢህአዲግ የኤርትራ የራዲዮን ሞገድን እያወከው ነው ተብሏል

በኢትዩጵያ ውስጥ የተከሰተው ደርቅ እና ረሀብ እየከፋ መጥቷል፣እስከ አሁን ድረስ ከ ሁለት ሚሊዬን በላይ ከብቶች አልቀዋል

ኢትዮጵያዊው አዛውንት የልጅ ልጃቸው እኩያ አገቡ፣ሩጫቸውን የጨረሱ ሁለት አሜሪካን ጥንዶች ተሞሸሩ

የሱዳኑ ፕ/ት አልባሸር ከኢትዩጵያ አርሶ አደሮች ጋር ግጭት አይኖርም ይላሉ

” ድንበር በማካለሉ ጉዳይ ላይ ከስምምነት ላይ ደርሰናል”ፕ/ት አልባሽር

እና ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *