Hiber Radio: የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የመገንጠል አለመሆኑን ጃዋር መሐመድ መግለጹ፣ሕወሃት የኢሳያስን መንግስት የተቃዋሚ መሪዎችን ማሰሩ፣የብአዴን አመራር መከፋፈል፣ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየወደቀች ያለች አገር መባሉዋ፣በአዲስ አበባ የውጭ ዘፋኞች ያለ ከልካይ ሙዚቃቸውን ማቅረባቸው፣የእነ ሰራዊት ፌስቡክን በዋዜማ ዝግጅት ላይ ማጥላላት ፣ ለሕወሃት ተላልፈው የተሰጡት የኦብነግ መሪ ጉዳይ ያስነሳው ተቃውሞ፣የናይጄሪያ ባለሀብቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድን መክሰስ፣የቴዲ አፍሮ እገዳና ዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ጳጉሜ 5 ቀን 2009  ፕሮግራም

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ

<…ስርዓቱ እየተዳከመ ነው። ይልቅ አሳሳቢው ነገር ያለ በቂ ዝግጅት ድንገት ተገንድሶ እንዳይወድቅ ነው። ለዛ ስራ መስራት አለብን …እኔን ተከትሎ የሚቀርበው ወቀሳ ትግሎን ለማጥላላት ካልሆነ በቀር የሚፈይደው የለም። ከዛሬ ሃምሳ ዓመትም በፊት በተመሳሳይ የኦሮሞን ትግል ለማጥላላት ሐይሌ ሐይሌ ፊዳ ይባል ነበር። ዛሬ ሃያ ዓመት ደግሞ…> አክቲቪስትና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር ጃዋር መሐመድ   በወቅታዊ ጉዳይ ከህብር ጋር ካደረገው ሰፋ ያለ  ቃለ ምልልስ(ክፍል አንድ)

<…አንዳንዱ መንግስት አሰደደኝ ብሎ እነሱው መረጃ አሲዘው ሰደውት ገና የስደተኛ ማመልከቻው ሳያልቅ ጀምሮ ኤምባሲያቸው ገባ ወጣ እያለ ከእነሱ ጋር ሲሰራ ታየዋለህ…በምርጫ 97 ማግስት በሰኔ ዝዋይ በታሰርንበት ወቅት በአንድ ክፍል ከታሰርነው ውስጥ ሶስቱ ሊሰልሉን አብረው የታሰሩ ነበሩ። አንዱ እዚህ ውጭ አገር በስደተኛ ስም መጥቶ ኖርዌይ ይኖር ነበር።እጁ ላይ ሳይቀር መለስን የተነቀሰ  በሁዋላ ግን ተነቃበትና… > ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ያሬድ ሀ/ማርያም ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ (የመጨረሻ ክፍል)

“ኢትዮጵያዊ በመሆኔ ብቻ የጀመርኩትን የዶክትሪት ትምህርትን ተከልክዬ ወደ አገሬ ተባረርኩ”አሳዛኙ የኢትዮጵያዊው ተማሪ ሰቆቃ ሲዳሰስ(ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የመገንጠል አለመሆኑን ጃዋር መሐመድ ገለጸ የትብብር ጥሪ አቅርቧል

የሕወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ያደራጃቸውን የኤርትራ መንግስት  ተቃዋሚ መሪዎችን አሰረ

ኢትዮጵያ በዘመነ ኢሕአዲግ በዓለም ላይ ሰላም እና መረጋጋት ከራቃቸው አገራት ተርታ ተመደበች

የአማራን መሬት አሳልፎ የሰጠው የብአዴን ከፍተኛ አመራር ከውስጥ ተቃውሞ እየበረታበት መሆኑ ተገለጸ

ናይጄራዊያን ቱጃሮች በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በአገራቸው መንግስት ላይ የከፍተኛ ገንዘብ ክስ ፋይል ከፈቱ

በአገር ቤት በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ የበዓል ገበያው የተቀዛቀዘ ነበር

ከመቋድሾ ውስጥ ታፍነው ለኢህአዲግ ደህንነቶች ሰሞኑን ተላልፈው የተሰጡት የኦብነግ ባለስልጣን ጉዳይ ታላቅ ቁጣ ቀሰቀሰ

ኦብነግ ከአሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት እንደሌለው ገለጸ የሶማሊያን መንግስት ተቃወመ

“በእኛ እና በኢሕአዲግ መካከል ወንጀለኞችን አሳልፎ የመሰጣጥ ስምምነት። አለ “የሶማሊያ መንግስት ምላሽ

በአዲስ አበባ የተለያዩ የውጭ አገር ዘፋኞች የሙዚቃ ዝግጅት አቀረቡ

የቴዲ ኮንሰርት በተከለከለበት ሚሊኒየም አዳራሽ እነሰራዊት ፍቅሬ ሕዝቡ የሰለቸውን ፕሮፖጋንዳ ሲያቀርቡና ፌስቡክን ሲያጥላሉ አመሹ

ኢሕአዲግ በአርቲስት ቴዲ አፍሮ ላይ ሰሞኑን ያሳደረው ጫና ላይ የእስራኤሉ ጋዜጣ ሰፊ ዘገባ አቀረበ

በሆድ እቃቸው ውስጥ አደንዛዥ እጽ የሸሽጉ ተሳፋሪዎች አ/አ እና ካይሮ  ላይ ተያዙ

እና ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *