Hiber Radio: ዶ/ር መረራ ጉዲና ከእስር በሁዋላ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ድጋፉን ገለጸላቸው ፣ከፓርቲያቸው ጋር ስለቀጣዩ ትግል እመክራለሁ ማለታቸው ተገለጸ

(ህብር ሬዲዮ) የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር እውቁ የተቃዋሚ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬ ከተፈቱት የፖለቲካ እስረኞች አንዱ ሲሆን ከእስር ቤት መውጣታቸውን ተከትሎ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ ከመንገድ እስከ መኖሪያ ቤታቸው አጅቦ ታላቅ ድጋፍ ያደረገላቸው ሲሆን የአካባቢው ቄሮ(የኦሮሞ ወጣቶች) ከረፋዱ ጀምሮ የፓርቲያቸው ዓርማ የሆኑትን ቀይና ጥቁር ቀለም ያለበት ባንዲራ ቀለም የመንገድ መለያ እስከመቀባት ሄደዋል።

ዶ/ር መረራ ጉዲና ከእስር ቤት መውታታቸውን ተከትሎ አጅቦ ቤት ላስገባቸው ሕዝብ በኦሮሚና ቋንቋ ንግግር ማድረጋቸውንና በቤታቸውም ለአገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ መስጠታቸውን ናሆም ተስፋዬ ለሪፖርተር ከስፍራው ዘግቧል።የወደፊት የፖለቲካ ትግላቸውን አስመልክቶ ከፓርቲያቸው ጋር እንደሚመክሩ ገልጸዋል።

የአገዛዙ ልሳን የሆኑ መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑን አንዴ ይፈታሉ ዘግይተው የማህበራዊ ሚዲያው ወሬ ነው ያሉት የዶ/ር መረራ መፈታት ትላንት በአገዛዙ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚ/ር ነገሬ ሌንጮ መግለጫ ከተገለጸ በሁዋላ የዶ/ር መረራ ምስል አለበትን ምስል ያለበትን ካኔቴራ በመልበስ ፣በጠዋት የአካባቢው ቄሮ ያለ ፍርሃት አደባባይ ወጥተው የኦፌኮን አርማ ቀለም በመቀባት ለፓርቲውና ለዶ/ር መረራ ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን ያገኘነው ተጨማሪ መረጃ ያስረዳል።

ዶ/ር መረራን ጨምሮ ተፈቱ ከተባሉት 115 የፖለቲካ እስረኞች ሌላ የኦፌኮን ም/ል ሊቀመንበር በቀለ ገርባ፣የሕጋዊው መኢአድ ሊቀመንበር ማሙሸት አማረ፣የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት እነ አታላይ ዛፌ፣በዘራቸው ምክንያት ከመከላከያና እና ከተለያዩ ቦታዎች የተያዙት እነ መ/አ ማስረሻ ሰጤ፣በአገዛዙ የፈጠራ ወንጀል ሳቢያ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት እነ እስክንድር ነጋ እና ታፍነው በልዩ ልዩ እስር ቤቶች የይስሙላውንም ፍርድ ቤት ያላዩ የነጻነት ታጋዩን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣መግደል ሙከራ ተደርጎባቸው ራሳቸውን ለመከላከል የቆሙትና አማራ ህዝባዊ ተጋድሎና እምቢተኝነትን ለማቀታጠል ምክንያት የሆኑት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ፣በዘራቸው ሳቢያ ከፍተና ግፍ የተፈጸመባቸው በመፈንቅለ መንግስት ስም የታሰሩት እነ ጄ/ል ተፈራ ማሞ እና በፌዴራል፣በክልል ስም ባላቸውና በሌላቸው ግልጽና ስውር እስር ቤቶች የታሰሩ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን ስርዓቱ  ካልፈታ እና እውነተኛ የህዝቡ ጥያቄ ካልመለሰ በጥቂት እስረኞች መፈታት መዘናጋት አይገባም የሚል ተደጋጋሚ ጥሪ ሲቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።

ማዕከላዊ የሚዘጋው ቢሮው ስለተበበ እንጂ የግፍ እስር አያያዝ አገልግሎቱ በሌላ ህንጻ ለመቀጠል ስርኣቱ መንቀሳቀስ ከጀመረ መቆየቱን የሚገልጹት መረጃዎች አቶ ሀይለማሪያም ማዕከላዊን በደርግ ጊዜ ሰቆቃ ሲፈጸምበት እንደነበር ብቻ የተቀሱት ስርዓቱ ከተጠያቂነት ለመዳን ነው የሚሉ ወገኖች ቢኖሩም በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጭምር በዓለም አቀፍ እና በኢትዮጵያም ሕግ  የተከለከ  ማሰቃያ (ቶርች) የሚፈጸምበት ማዕከላዊ እንዲዘጋ ሲጤቅ መቆቱ ይታወሳል። በሕወሃት የበላይነት ሚመራው አገዛዝ በማዕከላዊ ብቻ ሳይሆን በልዩ ልዩ ድብቅ እስር ቤቶች በእስረኞች ላይ  ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ ተደጋግሞ መገለጹ አይዘነጋም።

የስርዓቱ ደጋፊዎች በአስር ሺህ ከሚቆጠሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችጉዳይን ወደ ጎን በማድረግ የዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ የ115ቱ ተፈቱ የተባሉ እስረኞች መለቀቅ ትልቅ የፖለቲካ ተሐድሶ አድርገው ለማቅረብ እየሞከሩ ሲሆን ስርዓቱ አንዱን እያሰረ አልፎ አልፎ ጥቂቶችን እየፈታ ዛሬ ድረስ መዝለቁን በማየት ሕዝቡ ትግሉ ላይ አተኩሮ ትግሉን እንዲቀጥል በተደጋጋሚ ጥሪ መደረጉ ይታወሳል።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *