Hiber Radio: ቴዲ አፍሮ ባህርዳር ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት | አቀባበሉን ተመልከቱት

የአማራ ክልል ቴሌቭዥን እንደዘገበው ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በባህር ዳር ከተማ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ/ ‹‹ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ›› የሚለውን ኮንሰርቱን ጥር 13/2010 ዓ/በባህር ዳር ከተማ ለአድናቂዎቹ ያቀርባል፡፡ ቴዲ አፍሮ ‹‹ኢትዮጵያ ››የሚለውን አልበሙን ከለቀቀ በኋላ የሚያቀርበው የመጀመሪያው የሙዚቃ ኮንሰርቱ ነው ሲልየክልሉ ቴሌቭዥን ዘግቧል::

ቴዲ ባህርዳር ሲገባ በሰጠው ቃል “ስለፍቅር ፣ስለሰላም እና ስለ አንድነት እንዘፍናለን፡፡ስለተደረገልኝ አቀባበል እጅጉን አመሰግናለሁ፡፡እንዲህ አልጠበቅኩም፡፡” ብሏል::

አቀባበሉን ተመልከቱት

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *