Hiber Radio: ከፈርስት ሒጅራህ ፋዉንዴሽን የተሰጠ መግለጫ: የወልዲያው ግድያ ፥ የህወሃትን የሽንገላ ተሐድሶ ማሳያ!

በኢድ የንጹሗንን ደም ያፈሰሰው በህወሃት የሚመራው አምባገነናዊ ስርዓት፤ በኢሪቻ በዓል ላይ ደግሞት በመቶዎች የሚቆጠሩ እንዲሞቱ አድርጓል። በሁለት በዓላት ላይ የፈጸመዉን ስተህተት በሌላ ስህተት ለማረም የፈለገ እስኪያስመስልበት ድረስ ህወሃት ዳግም አጋዚን አሰማርቶ ጥምቀትን አክብረው የሚመለሱ ወጣቶች ላይ ጥይቱን አርከፍክፎ ገድሎ፣ አቁስሏል። የብዙዎችን ቤትም በሐዘን ድባብ እንዲሞላ አድርጓል።

አገሪቷ ዉስጥ ያለውን ህዝባዊ ቁጣን ለማብረድ፣ ፖለቲካዊ ምህዳሩን ለማስፋት፣ «በጥልቅ ተሐድሶ» እንደሚለወጥ ህወሃት ቃል ገብቶ ነበር። ቅሉ ታጥፎ በሳምታት ዉስጥ በወልድያ ከተማ ዉስጥ የአጋዚ ጦር አልሞ ተኳሾች የጥምቀት በዓል አክብረው በሚመለሱ ወጣቶች ላይ የፈጸሙት ዘግናኝ ግድያን ፈጸሙ። ፈርስት ሒጅራህፋዉንዴሽንን ይህ የወልድያ ወጣቶች ግድያ በጣሙን አስቆጥቶታል።

ፈርስት ሒጅራህ «ፍትህ ዘር የለውም!ፍትህ በሐይማኖት አይገደብም!»ብሎ በጽኑ ያምናል። ፈርስት ሒጅራህ የፍትህ አለም አቀፋዊ መርሆዎችን ከአፍ አድርጎ በመያዝ የሚሰራ በመሆኑ፤ የወልድያ ወጣቶች ደም ደመ-ከልብ ሆኖ እንዳይቀር የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። በዓመት በዓል ቀን ደማቸው የፈሰሰው የወልድያ ወጣቶች ግድያ ከፍትህ ምህዋር በጣሙን ያፈነገጠና ኢሰብዓዊ ተግባር በመሆኑ ሁሉም ዜጎች የዘር፣የሐይማኖት ልዩኑትን በመተውና በጋራ ዓላማ በመጣመር ፍትህን ያነግሱ ዘንድ ፈርስት ሒጅራህ ጥሪዉን ያቀርባል።

የወልድያ ወጣቶች በድምጻቸው ተቃዉሞ ማሰማታቸው በህገመንግስት የተረጋገጠላቸው መብት ነው።ወጣቶቹ ድምጻቹ ተሰማ ተብለው በአለሞ ተኳሽ አጋዚ ሰራዊት መገደላቸው መቸም ቢሆን የማይረሳ ታላቅ ወንጀል ነው። ህወሃት ያሰማራቸው አጋዚዎች ወጣቶቹን በድምጽ ማጉያ እንዲበተኑ አላስጠነቀቁም፣ ውሃ በማፍሰስ በድምጽ የሚቃወሙ ወጣቶችን ለመበተን አልሞከሩም፣አስለቃሽ ጭስ አልተኮሱም፣ጥይት ወደሰማይን ለማስጠንቀቅ አልተኮሱም ልክ በጦርነት ሜዳ ላይ እንደሚፋለሙት ጠላት የወጣቶችን ደረት በጥይት በሳስተው የጭካኔያቸውን ጥግ አሳዩ እንጂ። ይህ ሰብዓዊነት የጎደለው ታላቅ ወንጀል ነው።

ፈርስት ሒጅራህ ፋውንዴሽን ይህንን ለመሰለው ዘግናኝ ወንጀል በፍጹም በጭራሽ ታጋሽ አይሆንም። ፈርስት ሒጅራህ ወንጀሉን በጽኑ ያወግዛል።ፈርስት ሒጅራህ የወልድያ ወጣቶችን ኢሰብዓዊ አገዳደልን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ያደርሳል። ፈርስት ሒጅራህ በአገሪቷ ዉስጥ ያሉትንም ዜጎች የሚያሸብረን ስርዓት ተጠያቂ ከማድረግ ወደሗላ እንደማይል በቁርጠኝነት ያሳስባል። ፈርስት ሒጅራህ ቅስማቸው በሐዘን ለተሰበረ የሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።

ህዝብ ያሸንፋል ጨቋኝኞች ይሸነፋሉ

አላህ ፍትህን በኢትዮጵያ ላይ ያንግስ!

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

ፈርስት ሒጅራህ ፋዉንዴሽን

ዋሽንግተን ዲሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *