Hiber Radio: ወንጀለኛው ፋሽስት ወያኔ ሳይወገድ ከእስር ልንፈታ አንችልም! በአቻምየለህ ታምሩ

ምድሪቷን በጭካኔ ያጨቀያት የፋሽስት ወያኔ የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ ሳይወገድ፣ ክብረ ወሰን የተቀዳጁ ወንጀለኞች ለፍርድ ሳይቀርቡና ሕዝባዊ መንግሥት ሳይቋቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ስርየት ብሎ ነገር የለም። ኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት «ሊፈቱ ነው» የተባሉት በግፍ የእግር ብረት ውስጥ ሆነው በትግራይ መርመሪዎች የሚሰቃዩዋቸውና የጭካኔ ጥማቸውን የተወጡባቸው የህሊና ሰዎች ብቻ አይደሉም። ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ከትግራይ በበቀሉ ፋሽስቶች የማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ ነን።

የነ እስክንድር ነጋም ሆነ የነ አንዷለም አራጌ አይነት የህሊና ሰዎች የታሰሩለት አላማ ሳይፈታ ከጠባቡ የትግራይ ፋሽስቶች የሰው ማረጃና መተልተያ ቄራ ወደሰፊው የማሰቃያ እስር ቤት ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ እንዲዘዋወሩ ሞራላቸውን አላሽቀው፣ አካላቸውን ጎድተው፣ ስብዕናቸውን ፍቀውና እሁንም በቁጥጥራቸው ስር አድርገው ልክ እንደ ደሮዋ በረጅም ገመድ አስረው ስለለቀቋቸው መፈታታቸውን አያሳይምና «ተፈቱ» አያስብልም።

ለቁጥር የሚያታክቱ እስክድር ነጋና አንዷለም አራጌ አይነት ንጹሐን በትግራይ ፋሽስቶች የማሰቃያ ቤት ውስጥ በግፍ ገላቸው ተተልትሎ፤ ጸጉራጨው በደረቁ ተነቅሎ፤ ጺማቸው ተነጭቶ፤ የእግርና የእጅ ጥፍሮቻቸው በጉጠት ወልቀው፤ በብልታቸው ላይ የታሸገ ውሃ እንዲንጠለጠል ተደርጎ ተኮላሽተው፤ በኤሌክትሪክ ሽቦ ሰውነታቸው ተተልትሎ፤ እንደ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅለውና ተዘቅዝቀው ታስረው በግፍ ተደብድበው፤ እንቅልፍ እንዳያገኙ ፣ ለብቻቸው እንዲታሰሩ፣ ውሃ ውስጥ እንዲዘፈቁ፣ ተገደው የራሳቸው ያልሆነውን ቃል የራሳቸው እንደሆነ አድርገው በማስፈረም በግፍ እንዲታሰሩ ተደርገው፤ አንዱ እስረኛ ሌላውን በግዳጅ እንዲደበድብ ተደርጎ፤ በሰቃይ እልቆ ቢስ የህሊና ታሳሪዎች ተገድለው፤ የቀሩትንም በታሰሩበት በእሳት ተማግደውና በማንነታቸው ሲዘለፉ፣ ሲዋረዱና የስነልቦና ጉዳት ሲደርስባቸው ኖረው ይህንን ያህል መስዕዋትለት የከፈሉበት አላማ እስካልተፈታ ድረስና ይህንን ሁሉ ጭካኔ የፈጸመው ፋሽስታዊ አገዛዝ እጁ በመጫኛ የኋሊት ታስሮ ለፈጸመው ግፍና አረመኔያዊ ድርጊቱ ተጠያቂ ሆኖ ለፍርድ እስካልቀረበ ድረስ ግፉዓንን ከጠባቡ ማሰቃያ ቤት ወደ ሰፊው እስር ቤት እንዲዘዋወሩ መፍቀዱ በግፍ ታስረው ፍዳቸውን ሲያዩ ለከረሙ የሕሊና እስረኞች የግፍ ግፍ እንጂ ፍትህ ሊሆን አይችልም፤ የፋሽስቶችን የግፍ አገዛዝም ሙሉ በሙሉ ወንጀለኛነትና በቃላት ከሚገለጸው በላይ በሰው ደም መጨማለቁን ሊለውጠው አይችልም።

የፋሽስት ወያኔ የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ ተወግዶ የወንጀለኛው አገዛዝ ባለቤቶች ለፍርድ እስካልቀረቡ ድረስ ሶስት ትውልድ በማሰቃየት ክብረ ወሰን የተቀዳጀው አገዛዝ እስክንድ ነጋን ዛሬ ከጠባቡ ማሰቃያ ቤት ወደ ሰፊው እስር ቤት እንዲዘዋወር ቢፈቅድለት ነገ ግን እሱንም ሆነ በእስር ቤት ተወልዶ በናፍቆት ሲሰቃይ የኖረው አንድ ልጁን በግፍ ማሰሩ የማይቀር ነው።

የሕሊና ሰው የሚታሰረው ለሕዝብ ጥቅም ነው። በኛ አገር ግን ለሁላችን ነጻነት በግፍ የታሰሩና ተፈቱ ተብለው ከጠባቡ ማሰቃያ ቤት ወደ ሰፊው እስር ቤት እንዲዘዋወር የተፈቀደላቸው እስካሁን ያየናቸው ልጆቻቸውን ትተው የታሰሩ አባቶች እንኳን ለታሰሩለት ሕዝባቸው ለወለዷቸው ልጆቻቸው እንኳ አባት ሆነው ሲጠቅሙ አላየንም። ይህ የሆነው ደግሞ የታሰሩለት ሕዝባቸው ግፋቸው ፍትህ እንዲያገኝ ባለማድረጉ ነው። ይህ የበጃቸው ፋሽስቶች የታሰሩ ሰዎችን ስቃይም የትርፍ ማካበቻ አድርገታውል።

በዛሬዋ ኢትዮጵያ ገንዘብ ያላቸው ባለጊዜዎቹ አሳሪዎቻችን ስለሆኑ ሰቆቃ ፈጽመው የጭካኔያቸው ማርኪያ አድርገው የአካልና የህሊና ቁስል አድርሰው ከጠባቡ ማሰቃያ ቤት ወደ ሰፊው እስር ቤት እንዲዘዋወሩ የፈቀዱላቸውን ታሳሪ የህሊና ሰዎች ለልጅ ማሳደጊያ የፈጠሩትን ሳይወርሱት የቀረ ሀብትና ተንቀሳቀሽ ንብረት ካላቸው ለነሱ ከበርቴዎቹ በእጅ አዙር እየሸጡ እነሱ ባዘጋጁት የነርቭ ህክምና ሆስፒታል እያስረከቡ ነፍሳቸው እንዳትወጣ ሞታቸውን ብቻ እንዲጠባበቁ ሲያደርጓቸው ማየት አንድ ትውልድ የሆንንበት ያለፈው ሀያ ስድስት የፋሽስት ወያኔ የመከራ አመታት የሰቆቃ ትውስታችን ነው።

ስለዚህ በቃላት ከሚገለጸው በላይ ጨካኝ ወንጀለኛ የሆነው ፋሽስት ወያኔ ከነ ሕገ አራዊቱና የአፓርታይድ ድንጋጌው ተወግዶ ግፈኞች እኛን ያሰቃዩበት እጃቸው የኋሊት በመጫኛ ታስሮ እውነተኛ ችሎት ፊት ቀርበው ለፈጸሙት ጭካኔ ፍርዳቸውን እስካላገኙ ድረስ ለትንፋሽ ማግኛና ለጊዜ ለመግዣ ብለው «የፖለቲካ እሥረኞች ይፈታሉ» ስላታለሉን በፋሽስት ወያኔ ግፍ በጨቀየችዋ ኢትዮጵያ ስርየት ሊኖር አይችልም።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *