Hiber Radio: አገዛዙ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ተጠየቀ፣እስክንድርና አንዷለምን ጨምሮ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ዛሬም አልተፈቱም

(ህብር ሬዲዮ) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዷለም አራጌን ጨምሮ 746 የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን አገዛዙ በሰጠው መግለጫ ይፈታል ተብሎ ሲጠበቅ ዛሬ የአገዛዙ ሰዎች በእስር ቤት ተገኝተው እስክንድርና አንዷለምን ባልሰሩት ወንጀል የከሰሱበትን የሀሰት ክስ የሚያንጸባርቅ የይቅርታ ጥያቄ አቅርበው እንዲፈርሙ ቢጠይቁም ሁለቱም የህሊና እስረኞች ባለመፈረማቸው አልተፈቱም። የጋዜጠኛ እስክንድር አለመፈታትን አስመልክቶ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት ሲ.ፒ.ጄ ባወጣው መግለጫ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እስክንድር ከእስር እንዲፈታ በመግለጫ ጠይቋል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና የቀድሞ የሕጋዊው አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆነው አንዷለም አራጌን ትላንት እፈታለሁ ያለው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ የግንቦት 7 አባል ነኝ ብላችሁ ብሎ እንዲፈርሙ ያቀረበውን የይቅርታ ጥያቄ ባለመቀበል በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ያለ በደላቸው ለዓመታት ታስረው ይቅርታ እንዲጠይቁ ማለት ስርዓቱ ካልወደቀ በስተቀር በፍጹም በአገሪቱ ላኢ የሚደርሰውን ጥፋት፣ሲፈጽም የቆየውንና ዛሬም ተቃወሙኝ ባላቸው ንጹሃን ላይ የሚያደርገውን የበቀል እርምጃ ለማቆም ፍላጎት እንደሌለው የእነ ጋዜጠና እስክንድር ነጋና የሌሎቹም የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ ብሎ ሚጠብቀው ሕዝብ በተለይ በማህበራዊ ድርጊቱ አገሪቱን የሚመሩትን ሰዎች ተራ ዱርዬነት የሚያሳይና ለውጡን ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በአገር ውስጥና በውጭ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚጠይቁም ተስተውለዋል።

ሲፒጄ በበኩሉ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ያለ አንዳች ቅድ ሁኔታ ትላንት እፈታለሁ ያለው መንግስት ቃሉን ጠብቆ እንዲፈታ ጠይቆ ሰባት ኣመት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የቆየው እስክንድር ነጋ 18 ኣመት የተፈረደበት በሰላማዊ መንገድ ሀሳቡን መበግለጹ ዓለም አቀፍ ደረጃውን ባልጠበቀውና ፍትህ በጎደለበት የፍርድ ሂደት እንደነበርም ይሄው  የመብት ተሟጋቹ መግለጫ አስታውሷል።

አንዷለም አራጌም እንደ እስክንድር ሁሉ በተከፈተበት የፈጠራ ክስ ሳቢያ በአገዛዙ ካንጋሮ ፍርድ ቤት የዕድሜ ልክ ፍርድ ያለ ጥፋቱ ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን ሁለቱብ በአገዛዙ ደህነቶች ታፍነው ከተያዙበት እ.ኤ.አ ሴፕተምበር 14/2011 ጀምሮ ከእስር እንዲፈቱ በተደጋጋሚ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ሲጠይቁ መቆየታቸው አይዘነጋም።

ቄሮ አስቀድሞ ስርዓቱ ቃሉን ጠብቆ የቴናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያሉትን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ባለመፈታታቸው ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ይደረጋል ሲል ጥሪ አድርጓል። በአድማው ሳቢያ ስራ አይኖርም፣ሱቆች ዝግ ይሆናሉ፣የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ስለሚገታ ሕዝቡ ያንን አውቆ የራሱን ዝግጅት እንዲያደርግ ይሄው ጥሪ አሳውቋል።

ህብር ሬዲዮ አስቀድሞ በዜና ዘገባችን ቄሮ ሌሎችም የሚተባበሩበት አድማ ለመጥራት በዝግጅት ስላለ ህዝቡ አስቀድሞ የምግብና የማገዶ ሸመታ ዝግጅት እንዲአደርግ፣እህል እንዲያስፈጭ ጥሪ ማድረጉን ባለፈው ዕሁድ መዘገባችን አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት አገዛዙ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና አንዷለም አራጌን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች መካከል አገዛዙ 746 ታራሚዎችና ተጠርታሪዎች በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ እንደሚፈቱ በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን አማካይነት  ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በርካቶች እነ አቶ በቀለ ገርባ፣እነ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ፣እነ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣እነ ጄ/ል አሳምነው ጽጌና ጄ/ል ተፈራ ማሞን ጨምሮ የተለያዩ በእስር ላይ ያሉ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን በስም እየጠሩ ይፈታሉ ብለው የጠበቁ ሲሆን የዛሬውን ውሳኔ ተከትሎ የብዙዎች ተስፋ ወደ ቁጣ የተቀየረ መሆኑን በማህበራዊ ተከትሎ የሚወጡ ተቃውሞዎች ያሳያሉ።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *