አስመራ ከተማን ያጠቃው “የኤርትራ አገራዊ ደህንነት ግምባር” መግለጫ ሰጠ!

(ትርጉም ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

Eriteriaየወያኔ እገዛ የሚደረግለት ኢትዮጵያ ውስጥ መሰረቱ ያደረገ “የኤርትራ አገራዊ ደህንነት ግምባር” ብሎ ራሱን የሚጠራ ኢሳያስ አፈወርቂን ከሥልጣን ለማስወገድ የተቋቋመ ሽምቅ ተዋጊ ሃይል በፈረንጆች አቆጣጠር 12/03/2015 “የተሳካ ወታደራዊ ተልዕኮ በአስመራ ከተማ! አገርህ ስትዘመት ዓይንህ መዝጋት ውግዝ ከማርዮስ!” በሚል ርዕስ ያወጣው የትግርኛ መግለጫው ትርጉም እነሆ።

የኢሳያስ አፈወርቂ/ህግደፍ/ ሥርዓት በሕዝብችን ላይ በቀጣይነት እየተፈጸመ ያለው መረን የለቀቀ ጭቆና እና እርኩስ ሥራ ፊት ለፊት ገጥሞ ለማስቆም፤ ጀግኖቹ “የኤርትራ አገራዊ ደህንነት ግምባር” ትናንት ሮቡዕ 11/03/2015 ከምሽቱ ልክ 08፡30 ሰዓት “ቀሓውታ” ተብሎ በሚታወቀው ክፍለ ከታማ በህ.ግ.ደ.ፍ. ንብረት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።

ይህ የማጥቃት እርምጃ የተፈጸመው የረቀቀ የረዢም ጊዜ ጥናት ከተካሄደ በሗላ ሲሆን፡ ጥቃቱ ለመፈጸምም የሕዝብ እና የውስጥ አርበኞች ወታዳራዊ ተባባሪዎች እጅ የታከለበት ሥራ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

ለዚህ ጥቃት መነሾው የሚከተሉት ምክንያቶች ነበሩ፡በአርባዕተ አስመራ፤ በጸሎት እንዲሁም በቅርቡ በዓዲ ቐይሕ “የህግደፍ/የኢሳያስ ሥርዓት” በሕዝባችን ላይ ላካሄደው አረሜናዊ ጭፍጨፋ የአጠፋ እርምጃ ሲሆን፤ በተጨማሪም፤ የኢሳያስ አሽከሮች የሆኑ ሆዳሞች የአገር እና የሕዝብ ሃብት የሆኑትን ተቋማት ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በመመሳጠር ለግል ጥቃማቸው እያዋሉት መሆናቸውን በጥናት ስለደረስንበት፤በስስታሞች ሲካሄድ የነበረው የአገር ምዝበራ ለማምከንም ጭምር ያነጣጠረ ነበር።

በዚህም መሰረት “ኦፐረሽን ቀሓውታ” በመባል የሰየምነው የማጥቃት እርምጃ፤ የስርዓቱ ንብረት በሆነው ትልቅ ጋራዥ ውስጥ በመግባት፤ ቢሻ የወርቅ መዓድን ላይ የተሰማሩ ልዩ የሆኑ ትላልቅ የጭነት መኪኖች ለማቃጠል ያነጣጠረ ተልዕኮ ነበር።

በተልዕኮውም መሰረት፤ግማሹ ሲቃጠሉ፤ከፊሉ ደግሞ አንደማይሆኑ ሆነው ተበላሽተዋል። ተልዕኮውን ያካሄዱት ጓዶች በሕዝብ ንብረትም ሆነ በህይወት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት ክንዋኔ በመፈጸማቸው፤ በአንድ ሰው ላይ ቀላል የሆነ የመቁሰል ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር በሕዝብ ላይ የደረሰ ጉዳት አልነበረም።

ቃጠሎው እንደታወቀም “የእሳት አደጋ መከላከያ” መኪኖች እና የኢሳያስ የጸጥታ ክፍሎች ወዲያውኑ ወደ ቦታው በመሄድ፤ የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተው ግራ ተጋብተው እንደነበር ሁኔታውን በቅርብ ሆነው የተከታተሉት ጓዶች ገልጸዋል።
የጸጥታ ክፍሎቹ ወሬውም በመላ ከተማዋ እንዳይዳረስ በመስጋት፤ የተቻለውን ሁሉ ቢያደርግም፤ ሕዝቡ ግን በተወሰደው እርምጃ ደስታውን እየገለጸ ነው።

እኛ ግ.ሃ.ድ.ኤ. (ግምባር ሃገራዊ ድሕንነት ኤርትራ) እዚህ ላይ ለመግለጽ የምንፈልገው፤ ከጨቋኙ ስርዓት ጋር ፊት ለፊት ለመግጠም፤ፍልሚያው “እውስጥ አገር” ውስጥ መሆን እንዳለበት ረዢም ጊዜ አጥንተን በወሰድነው ውሳኔ መሰረት የተከናወነ ነው።

ይህ አርምጃ አስፈላጊነቱ ተጠንቶ የተወሰደ የመጀመሪያ ክንዋኔ ሲሆን፤ አርምጃው የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንዳልሆነ ፍትሕ ለጠማው ሕዝባችን ለማበሰር እንወዳለን።

በተጨማሪም፡ አብዛኛው በህግደፍ ሥር ያለው ሰራዊት በስርዓቱ ተጨቋኝ መሆኑን ስለምናውቅ፤ኢላማዎቻችን በሰራዊቱ ላይ ያነጣጠረ አይሆንም። ሆኖም፤ ከጨቋኙ ሥርዓት ጐን ቆሞ በሕዝባችን ላይ ግፍ የሚፈጽም የሰራዊቱ አባልም ሆነ ቡድን በዚህ አጋጣሚ እራሱን አንዲያስተካክል ስንመክር፤አሻፈረኝ ብሎ በሕዝብ ላይ ግፉ እየፈጸመ የሚቀጥል ግለሰብ ወይንም ቡድን ቢኖር ለምንወስድበት እርምጃ ተጠያቂው እራሱ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

በተጨማሪም የአገር ሃብት እና የሕዝብ ንብረት በሆኑ ተቋማት ላይ በስስትነት ተነሳስተው የሚበዘብዙ እና የሚያስበዘብዙትን ለማስቆም በተባባሪዎቻችን የውስጥ ወታደራዊ ሃይሎች እና ዜጎች ጋር ትብብራችንን በማቀናጀት የምናስቆማቸው መሆኑን እንገልጻለን።
በዚህ አጋጣሚ በተለያዩ ዘርፎች ሆነው ሥርዓቱን በማገልገል ላይ ያሉ ክፍሎች እና ወታደራዊ ቡድኖች በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው የስርዓቱን ግፍ ለማስቆም ከሕዝቡ እና “ከአገራዊ የደህንነት ግምባር ሠራዊት” ጐን ቆሞ የድርሻውን ለመወጣት ጊዜው የደረሰ መሆኑን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

“ኩሉም በላይ የአገር እና የሕዝብ ደህንነት እናስቀድም!!”

የኤርትራ አገራዊ ደህንነት የጸጥታ እና ወታደራዊ ክፍል ጉዳዮች ጽ/ቤት፡12/03/2015

ይላል።

ዜናውን በትግርኛ ወይንም በእንግሊዝኛ አንብባችሁ ለመረዳት ላስቸገራችሁ ዜጎቻችን እንዲረዳ የተተረጐመ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *