Hiber Radio: ተጨማሪ ጥሪ ለፓርላማ አባላት -ፓርላማው ከታሪካዊ ሞት ራሱን ያድን!!

ተጨማሪ ጥሪ ለፓርላማ አባላት -ፓርላማው ከታሪካዊ  ሞት ራሱን ያድን!!

ከደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮኮቦች ህብረት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ፡

የሀገራችን ኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲና ለፍትህ የሚያደርገዉን የመጨረሻዉን ትግል ለማፈን ይረዳዉ

ዘንድ የህወሓት/ኢህአዴግ የአስችኳይ ግዜ አዋጅ በሚል ስም በመላዉ ሀገራችን ያወጀው ጦርነት መልኩን ቀይሮ በወታደራው ጁንታ

አገርቷን ስልጣን ለመቆጣጠር እና ለመግዛት ያወጣው እቅድ መሆኑ ግልፅ ነው። ይህንን እቅዱን እውን ለማድረግ ለይስሙላ

የሚጠቀምባቸዉ የመንግስት መቃቅርን ወደ ጎን ትቶ በመላ አገርቷ የጅምላ ግድያና አፈና በስፋት ለመፈጸም መሆኑን ካዋጁ በሁላ

በኦሮሚያ በተለይም በወለጋ: በጉራጌ እና በሌሎችም የሀገራችን ክፍል በማካሔድ ላይ ያለው እስራት፣ ስቃይ፣ መከራና ጭፍጨፋ በቂ

ምስክር ነው።

በህዝብ ተውካይነት ስም በፓርላማው ውስጥ የምትገኝ የደቡብ ተወላጆች ይህንን በአስቸኮይ አዋጅ ስም በመላዉ የሃገራችን ህዝብ

ላይ የታወጀውን የግድያና ያፈና ጦርነት ተቃውማችሁ ውድቅ እንድታደርጉ በስሙ የተወክላችሁት የደቡብ ሕዝብ የሚያቀርበውን ጥሪ

በመቀበል ሕልናቸሁን ከጉድፍ በማፅዳት ራሳችሁን ከታሪካዊ ሞት እንድታድኑ እና ከሌሎች የሀገራችን ህዝቦች ያለንን የቤተሰባዊነት

ስሜትና አጋርነት የሚያጠናክር አራያነት ያለዉ ተግባር እንድታከናዉኑ በማለት ሕዝባዊና አገራዊ ጥሪ እናቀርባለን።

በሌላ በኩል በውድቀት ጣር ላይ ያለው የወያኔ ፋሽስታዊ ስርዓት በወለጋ: በጉራጌ እና ሌሎች በአከባቢዎች በወገኖቻችን ላይ

የሚፈፅመውን የጅምላ ግድያ፣ እስራት፣ ስቃይና መከራ አጥብቀን እያወግዝን በትግሉ ለተሰዉ ታጋይ ወጣቶች ክብር እየስጠን

ለቤተሰቦቻቸውም መፅናናትን እንመኛለን። የችግሮች ሁሉ ዋነኛ ምንጭ የሆነዉን የወያኔ ስርዓት ለማፍረስ የሚታደርጉትን የነጻነትና

የፊትህ ትግል አስፈላጊ በሆነ መንገድ ሁሉ ድጋፍ እና ትብብር ከምን ጊዜውም በላይ አጠናክረን እንቀጥላለ። ለዝህ የተቀደሰ ተግባር

ድርጅታችን ከሕዝቡ ጎን በፅናት መቆሙን እናረጋግጣለን

ትግላችን ፍትሀዊ ነው : ግባችን ነፃነት ነው

 የደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮከቦች ህብረት

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *