Hiber Radio: ሰበር ዜና -በቅሊንጦ ቃጠሎ የተከሰሱ ብይኑን በመቃወማቸው አፈሙዝ ዞረባቸው፣የተከሳሽ ቤተሰቦች ዋይታ አሰምተዋል፣የተከፈተባቸው የሽብር ክስ በወንጀለኛ መቅጫ እንዲታይ ተወሰነ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በጊዜያዊነት በ4ወንጀል ባስቻለው ችሎት በቅሊንጦ ቃጠሎን ተከትሎ ከተከሰሱት መካከል እነ መ/አ ማስረሻ ሰጤ፣ዶ/ር ፍቅሩማሩን ጨምሮ የተወሰኑ ተከሳሾችን የሽብር ክሱን  በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ እንዲታይና ወንጀሉን ተከላከሉ ሲል የወሰነ ሲሆን የተወሰኑ ተከሳሾችን በነጻ ለቋል።ተከሳሾች ብይኑን በመቃወማቸው በእስረኞች ላይ በፍርድ ቤት ፖሊሶቹ መሳሪያ አቀባብለው አፈሙዝ በማዞራቸው የተከሳሽ ቤተሰቦች በዋይታ ሐዘናቸውን መግለጻቸውን የመረጃ ምንጮቹን ጠቅሶ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ከአገር ቤት ዘገበ።

በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ የተከሰሱት ዛሬ በችሎቱ በተፈጠረ ችግር በርካታ አፈሙዝ ዞሮባቸዋል። በተከሳሾቹ ላይ ጥይት ሲቀባበልባቸው፣ አፈሙዝ ሲዞርባቸው ያዩ የተከሳሾች ቤተሰቦች ዋይታ አሰምተዋል። አልቅሰዋል። ያለው ዘገባ አንዲት ዮናታን ተስፋዬ ሲያፅናናቸው የነበሩ እናት “እኔ ልቅደም፣ እኔን ቀድሞ ይግደለኝ” እያሉ ለተከሳሽ ልጃቸው ሲያለቅሱ ነበር ሲሉ ጠቅሷል።

መቶ አለቃ ማስረሻ፣ ዶክተር ፍቅሩ ማሩ፣ አሸናፊ አካሉ፣ አግባው ሰጠኝ፣ ወልዴ ሞቱማ፣ ሚስባህ ከድር፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ ደረጀ መርጋ፣ ከበደ ጨመዳ፣ ደሴ አንዳርገው፣ ፍፁም ቸርነት ጨምሮ 28 ተከሳሾች እስር ቤት ውስጥ አመፅ በማደራጀት፣ በመምራት፣ በመሳተፍ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ አንቀፅ 464/2/ሀ፣ ለ፣ 461/ሀ እና 494 /2 ስር እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል።

በወቅቱ በችሎት “በቃጠሎው የተገደለውኮ አብሮ አደጌ፣ የሰፈሬ ልጅ፣ ጓደኛዬ ነው። አባቴ የእሱን ሞት ሰምቶ በልብ ድካም ነው የሞተው” ሲል በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት በተገደሉት እንዲከላከሉ ከተበየነባቸው መካከል 34ኛ ተከሳሽ ፍፁም ጌታቸው ተናግሯል። ችሎት በተረበሸበት ወቅት የተከሳሾቼ ቤተሰቦች ሲያለቅሱ ተስተውላል።ብዙ እናቶች ሲያለቅሱ ነበር።

በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ የተከሰሱት እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ክስ ከሽብር ወንጀል ወጥቶ በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ እንዲታይ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

በመሆኑም መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ ወልዴ ሞቱማ፣ አግባው ሰጠኝ፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ አበበ ኡርጌሳ በእስር ቤት ውስጥ አመፅ በማደራጀትና መምራት ወንጀል፣ በወንጀለኛ መቅጫ 464/2/ለ ስር ይከላከሉ ተብሏል። የሌሎቹ እየተበበበ ነው።

ከ38ቱ ተከሳሾች መካከል

31ኛ ተከሳሽ ጌታቸር እሼቴ

32ኛ ተከሳሽ ቶፊቅ ሽኩር

33ኛ ተከሳሽ ሸምሱ ሰኢድ

34ኛ ተከሳሽ ፍፁም ጌታቸው በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ በተገደሉት ሰዎች ነፍስ እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል።

6ኛ ተከሳሽ አብዱሉሂ አልዩ

7ኛ ተከሳሽ እስማኤል በቀለ

11ኛ ተከሳሽ ቃሲም ገንቦ

18ኛ ተከሳሽ አንጋው ተገኘ

21ኛ ተከሳሽ ሰይፈ ግርማ

 

27ኛ ተከሳሽ ዲንሳ ፉፉ

28ኛ ተከሳሽ ናስር ደጉ

29ኛ ተከሳሽ ናኦል ሻሜሮ በነፃ እንዲሰናበቱ ተበይኗል።

ይህ በእንዲህ እነንዳለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ የተከሰሱ 16 እስረኞች ላይ በምርመራ ወቅት የደረሰባቸውን ጉዳት በሪፖርቱ አኳትቷል። በዚህም መሰረት:_

1) ከበደ ጨመዳ:_ ቀኝ እጅ ላይ ትንሽ ጠባሳ፣ ቀኝ እግር አውራ ጣት ስብራት፣

2)ኢብራሂም ካሚል:_ ቀኝ እግር ላይ ጠባሳ፣ ግራ እጅ ላይ ጠባሳ፣ የካቴና እስር ምልክቶች

3) አግባው ሰጠኝ_ግራ ታፋ ላይ ሰፊ ጠባሳ፣ ቀኝ እግር ላይ ጠባሳ፣ ግራ እግር ላይ በሚስማር የተመታ ምልክት፣ ጀርባ ላይ የግርፋት የሚመስሉ ምልክቶች

4)ቶፊቅ ሽኩር: ቀኝ እጅ ላይ ጠባሳ፣ የሁለት እግር አውራ ጣት ጥፍር መነሳት፣ ግራ እጅ ጠባሳ

5) ሸምሱ ሰይድ: የጀርባ የግርፋት የሚመስሉ ምልክቶች

6) ሚስባህ ከድር: የካቴና የእስር ምልክቶች፣ ቀኝ እጅ ላይ ሰፊ ጠባሳ፣ ግራ እጅ ላይ አነስተኛ ጠባሳ፣ ቀኝ እና ግራ ታፋ ላይ ጠባሰ፣ የግራ እጅ ጠቋሚ ጣት ስብራት

7) ፍፁም ጌታቸው: የቀኝ እጅ ጉዳት

8) ተመስገን ማርቆስ:_ የቀኝ እጅ ስብራትና ጠባሳ፣ ሁለቱም እግሮች ሰፋፊ ጠባሳዎች

9) አሸናፊ መለሰ: የቀኝ እና ግራ ታፋ ላይ ጠባሳዎች፣ የግራ እጅ የቀለበት ጣት ስብራት

10) ካሳ መሃመድ: ቀኝ እጅ ጥልቅ ጠባሳ፣ ጭንቅላት ላይ የመፈንከት ምልክት

11) ሲሳይ ባቱ: ቀኝ እጅ ላይ ጠባሳና የጠቆረ ምልክት

12) አቡዱልደፋር አስራት: ቀኝ እና ግራ እግር አውራ ጣት ጥፍር መነቀል

13) ደረጀ መርጋ: ግራ እግር ላይ ስድስት ጠባሳዎች፣ ሁለቱም እጅ ላይ ካቴና እስር የጠቆሩ ምልክቶች

14) ቶፊክ ፈርሃ: ግራ እጅ ላይ ጠባሳ፣ የካቴና እስር የጠቆሩ ምልክቶች

15) ኡመር ሀሰን: የግራ እግር አውራ ጣትና የቀኝ እግር ከአውራ ጣት ቀጥሎ ያለው ጣት ጥፍር መነቀል

16) ሰይፈ ግርማ: ከጀርባ ትክሻ በግራ በኩል በሚስማር የተመታ ጠባሳ፣ ሁለቱም እግሮች ላይ ጠባሳ መኖሩን መግለጹ ይታወሳል ሲል ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ጽፏል።

ከዚህ ቀደም እስረኞቹ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣በአገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃናት በሸዋ ሮቢት የቅሊንጦን ቃጠሎ ተከትሎ ሲቃወሙ የነበሩ እስረኞች ዐይናቸው እያየ ተገድለው እሳት መጨመራቸውን፣ሊያመልጡ ነው በሚል ሆን ተብሎ የተፈጸመውን ግድያ ማታቸውን አጋልጠዋል።ድርጊቱን  የፈጸሙና ዛሬም በእስር ቤቱ በሀላፊነት ላይ ባሉ የእስር ቤቱ ሀላፊዎችን አሳልፎ ላለመስጠት በሸዋ ሮቢት አማራና ጉራጌ ብሔር ተወላጅ የሆኑትን ግንቦት ሰባት ኦሮሞ የሆኑትን ኦነግ ሙስሊሞችን ከአሸባሪዎች ጋር የወገኑ ሲሉ ከፍተኛ ግፍ እንደፈፀሙባቸው በዝርዝር ይፋ አድርገዋል።የአገዛዙ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ያወጣውን የተድበሰበሰ ሪፖርትና አጥፊዎች እንዳይቀጡ ለመሸፋፈን የተደረገውን ሙከራ አውግዘዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *