ለአርበኞች ግንቦት 7 ከዲሲ ግብረ ሀይል የመድሃኒትና የገንዘብ ልገሳ ተደረገ

dc-force-01

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵአውያን ያቋቋሙት የዲሲ ግብረ ሀይል ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ነጻነት ተዋጊዎች የ15 ሺህ ዶላር የሚያወታ መድሃኒትና አስር ሺህ ዶላር የገንዘብ ልገሳ በትላንትናው ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ በአንድ ሬስቶራንት ውስጥ ባካሄዱት ስነ ስርዓት ላይ ለግንባሩ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አስረከቡ።

ዲሲ ግብረ ሀይል ለነጻነት ተዋጊዎቹ ያለውን የገንዘብና የመድሃኒት ልገሳ ካበረከቱ በሁዋላ ይሄው ድርጊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸዋል።ዶ/ር ብርሃኑ ለሰራዊቱ የተበረከተውን የመድሃኒት የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ ተቀብለው ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም ሁሉም በያለበት ትግሉን አንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በዚሁ ወቅት ዶ/ር ብርሃኑ በስፍራው በተገኙበት ወቅት እንደተናገሩት በመላው ኢትዮጵያ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን የድርጅታችን አባል መሆን አይጠበቅባችሁም ነገር ግን ትግሉ የናንተም በመሆኑ የበኩላችሁን አስተውጽዖ በማድረግ የኢትዮጵያዊነት ግዴታችሁን ተወጡ። የጀመራችሁትን ትግል አጠናክራችሁ ቀጥሉ። ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ማለታቸውን ግብረ ሀይሉ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችንና በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *