በአዲስ አበባ አነስተኛ ነጋዴዎች በከፍተኛ የግብር ጫና እየተማረሩ ነው ፣ጫና የሚፈጥሩ ባለስልጣናት የሹመት እድገት አግኝተዋል

market_001_2015

• የየካ ክፍለ ከተማ ነጋዴዎች በግብር እየተማረሩ ነው በየካ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ነጋዴዎች በ2006 ዓ.ም ይከፍሉት ከነበረው በ10ና 10 በመቶ ግብር ጭማሬ በ2007 ዓ.ም እንዲከፍሉ መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ነጋዴዎቹ ያማረሩ ባለስልጣናት እድገት እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ግብሩ የተጨመረባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2008 ዓ.ም ከ31 እስከ 38 ሚሊዮን ብር ለማሟላት በመታቀዱ ነው፡፡ በተለይ በየካ ክፍለ ከተማ የሚኖሩት ነጋዴዎች የክፍለ ከተማው የገቢዎች አወሳሰን ኃላፊ አቶ ወንድሙ አባቡቶ በሚወስኑባቸው ከአቅም በላይ በሆነ ግብር የተመረሩ ሲሆን ሰውዬው በዚሁ ህዝብን በማማረር ተግባራቸው ከቀበሌ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በሶስት አመት ውስጥ ወደ ክፍለ ከተማ ማደጋቸው ተግልጾአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አቶ ወንድሙ አባቡቶን ወደ ፌደራል ገቢዎች እድገት ለመስጠት ለሳምንት ሶስት ቀን በሲቪል ሰርቪስ የዲግሪ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ አቶ ወንድሙ በህዝብ ላይ በደል እየፈፀመ መሆኑን የበታች ሰራተኞች አቤቱታ ቢያቀርቡም ‹‹አርፋችሁ ስሩ እሱ ስራውን በሚገባ እየሰራ ነው፡፡›› የሚል የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ የተለያዩ ገበያዎች ላይ አገዛዙ ሆን ብሎ አነስተኛ እና ብዙሃን ነጋዴዎችን በከፍተኛ የታክስ ጫና ከገበያ እያስወታ የስርኣቱ ሰዎች በቀላሉ ወደ ገበያው እንዲገቡ ሲያደርግና ብዙዎችን ለችግር ሲዳርግ መቆየቱ ይታወሳል።የዘንድሮውም የታክስ ቻና ሆን ተብሎ የተለጠጠውን የከተማዋን በጀት ለማሳካት በሚል ድሃውን ነጋዴ ለማፈናቀልና ስርዓቱ የወለዳቸውን ነጋዴዎች በምትካቸው ለማስገባት ጫና መፍጠር መጀመራቸውን ያሳያል የሚሉ አስተያየቶችም ደርሰውናል።

ህብር ሬዲዮን በየቀኑ በድህረ ገጻችን ወይም በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *