Hiber radio፡ በኢትዮጵያ መንግስት በሚዲያ የጦርነት ቅስቀሳ ጀመረ፣የጋሞ ብሄረሰብ አገዛዙ በቃን ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድራለን አሉ፣ኤርትራ በማንኛውም ሰዓት ኢትዮጵያ ልትወረኝ ትችላለች አለች፣በአርባ ምንጭ ወንድሙ የነጻነት ትግሉን በመቀላቀሉ አንድ ወጣት በደህነቶች ተይዞ ከፍተኛ ማሰቃየት ተፈጸመበት ብገደል ሀላፊነቱ የመንግስት ነው ብሏል፣የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች ለእንግሊዝ መንግስት በምሬት ተማጽኖ አቀረቡ፣የጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ እና የኤድዋርዶ ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም

habtamu11

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 26 ቀን 2007 ፕሮግራም

<…የጋሞ ብሄርን ከብሄር የሚያጋጭ ፣የጋሞን ማንነት የሞያንቋሽሽ ከራሱ ከመንግስት በጀት 1.5 ሚሊዮን ብር ተመድቦ የተጻፈ መጽሃፍ ነው የተቃውሞው መነሻ አሁን የጋሞ ብሄር በቃን ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድራለን፣የተሰረቀውን የ2007 ምርጫ ተከትሎ ያስቀመጣችሁልንን አንቀበልም ብሎ ቁጣውን በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ገልጿል …>

ሀዴ አንበሴ የጋሞ ብሄረሰብ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው ቁጣቸውን ስለገለጹበት ተቃውሞ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

 

<…ኦባማ ቁጥር አንድ እና ኦባማ ቁጥር ሁለት ያደረጉት ንግግር አንድ አይደለም ሰኞ የተዘረፈውን ምርጫ እያወቁ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ብለው ማክሰኞ ያደረጉትን ንግግር ስታይ ነገ ደግሞ ለጥቅማቸው እስከሆነ ሌላ አቋም እንደማይዙ ማረጋገጫ የለም ዋናው ሕዝቡ ለራሱ ነጻነት ራሱ መሆኑን ማወቅ ነው…ኦባማ መጥተው ስለሄዱ ሳይሆን በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊዎችም ሆነ በሌሎቹ የፖለቲካ እስረኞች ላይ በዚህ ሰዓት በንጹሃኑ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ በፈጠራ ክሱ ሳቢያ መፍረድ በምስራቅ አፍሪካ አለመረጋጋት መጋበዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ መፍረድ ነው…> ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ የፕ/ት ኦባማ ጉዞ እና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን የፍርድ ቤት ሂደት በተመለከተ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ጣሊያኖች አቡነ ጴጥሮስን ያስወለቋቸውን የክህነት ልብሳቸውን አስለብሰው መስቀላቸውን መልሰው አደባባዩ ላይ ያወጧቸው እኛን ደግፈው ንግግር ያደርጋሉ የሚል የተሳሳጠ መረጃ ከባንዳ አግኝተው ነበር መናገር ሲጀምሩ አርበኞችን ደግፈው ፋሺስቶችን ሲያወግዙ ነው በንዴት መጀመሪያ አንደኛው በጥይት የመታቸው መትረየሱ ተከትሎ መጣ…ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ መታወስ በሚገባቸው ደረጃ እየታወሱ ታሪካቸው ራሱን ችሎ አልተጻፈም ትውልዱ ከዚህ በላይ ማድረግ ማስታወስ አለበት ሐውልታቸውም ለምን ተመልሶ ቦታው እስካሁን አልቆመም ያለበትስ ብሎ መጠየቅ ይገባል።ኢህ ካልሆነ ግን…> የታሪክ ተራኪው ኤድዋርዶ ባይኖሮ የአቡነ ጴጥሮስን 79ነኛ የሰማዕትነት መታሰቢያ አስመልክጦ ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የፕ/ት ኦባማ የኢትዮጵያው የይስሙላ ምርጫ ውጤት ላይ የሰጡት አወዛጋቢ አስተያየትና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ( ልዩ ጥንቅር)

አሜሪካና ዙምባብዌን እያወዛገበ ያለው ሰሞነኛ የአንበሳ ጉዳይ ( ልዩ ዘገባ)

በቬጋስ የታክሲ እንቅስቃሴ ላይ የተጋረጡት ፈተናዎች እና በቅርቡ የተጨመሩ ታክሲዎች በአሽከርካሪው ሕይወት ላይ የፈጠሩት ጫና (ቃለ መጠይቅ)

የኢትዮጵያን ቀን በቬጋስ ለማክበር እየተደረገ ያለው ዝግጅት(ውይይት)

 ሌሎችም

ዜናዎቻችን

መንግስት የጦርነት ቅስቀሳ በመገናኛ ብዙሃን ጀመረ

አርበኞች ግንቦት ሰባትን የሚያጥላላ ዶክመንተሪ እየተዘጋጀ ነው

ኤርትራ በማንኛውም ሰዓት በኢትዮጵያ ልወረር እንደምትችል የፕ/ት ኢሳያስ አማካሪ ገለጹ

የጋሞ ብሄረሰብ አባላት በመንግስት በጀት ታትሞ ባንቋሸሻቸው መጽሐፍ ሳቢያ በቃን ራሳችንን እናስተዳድራለን ሲሉ በሰልፍ ተቃውሟቸውን ገለጹ

በአርባ ምንጭ አንድ ወጣት ወንድሞ ወደ ኤርትራ በመሄዱ በደህነቶች ተደብድቦ ጉዳት ደረሰበት

ብገደል ተጠያቂው መንግስት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይወቅልኝ ብሏል

የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች እንግሊዝ ተገቢውን ጫና እንድታደርግ ጠየቁ

የኦሳማ ቢን ላድን እናትና እህቱ እንግሊዝ ውስጥ የግል አውሮፕላናቸው ተከስክሶ ሞቱ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-080215-080915

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *