የህወሃት መሪዎች የአዲስ አበባና የትግራይ በሚል በሁለት አንጃ ተፋጠዋል!

 የህወሃት ሁለቱን አንጃዎች የሚመሩት አባይ ወልዱና ዶ/ር ደብረ ጽዮን ከተወሰኑ የህወሃት ባለስልታናትና ከብአዴኖቹ ጋር
የህወሃት ሁለቱን አንጃዎች የሚመሩት አባይ ወልዱና ዶ/ር ደብረ ጽዮን ከተወሰኑ የህወሃት ባለስልታናትና ከብአዴኖቹ ጋር

የህወሓት ሁለቱ ኣንጃዎች ፍጥጫ…!
***********************************

አምዶም ገ/ስላሴ

ህወሓት የሚመራው መንግስት በትግራይ ህዝብ፣ ሙሁራን፣ ተማሪዎች፣ የፖለቲካ ኣክቲቪስቶች፣ የህወሓት ኣባሎች ሳይቀሩ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰው ይገኛል።

ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በሗላ ህወሓት የነበረት ግርማ ሞገስ ያጥች ስትሆን በጦርነቱ ምክንያት ለሁለት የተከፈለችው ህወሓት ጠበንጃዋ ኣንግባ ሁሉንም የተለየ ሃሳብ የያዘ ሰው የተለያዩ ቅጥያ እያሰጠች ድራሹን ስታጠፋው ነበር።

የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ጋር የነበረው ቁርኝት ከፍተኛ ከመኖሩና ሙሉ ድጋፍ እንደሰጣት ዋና ማሳያው “ውድብና”( ድርጅታችን ) ሲላት ለታጋዮችም “ደቅና”(ልጆቻችን) በሚል የማቆላመጥ ስም ይጠራት ነበር።

የህወሓት ጥፋቶች በስራ የሚከሰቱ ስህተቶች በመቁጠር ይቅር እያለ እያለፈ ከነ ችግሮቿ ተሸክሞ ዓመታት ቢጠብቅም በረኻ እያለች የገባችለት ቃል ክዳ ለጥቂት ባለ ስልጣኖች ብቻ የቆመች መኻንና የህዝቡን ችግር፣ ፍላጎትና መስዋእትነት የማይታያት ዓይነ ስውር መሆንዋ ማረጋገጥ ከጀመረ በሗላ የትግራይ ህዝብ “ውድብና” ሲላት የነበርችው በስሟ “ሕወሓት” ብሎ መጥራት “ደቅና” (ልጆቻችን ) የሚለውን “ንሳቶም”(እነሱ)ብሎ መጥራት ከጀመረ ዓመታት ኣልፈዋል።

ህወሓት የህዝብ ጥያቄ፣ ችግር፣ እሮሮ፣ ስቃይ፣ እርዛት፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች መስማት የማትችል ዱዳ ሁና ኣልፈዋለች።

የትግራይ ህዝብ የህወሓት ስም መጥራት ተጠይፎ “እነሱ” እያለ ቢጠራቸውም ኣመራሮቹም ሰሚ ጆሮ ኣልነበረባቸውም።

የትግራይ ህዝብ ህወሓት “ጠላቶችህ ሊውጡህ ኣሰፍስፈው እየመጡ ነው፣ እኔ ከሌለው ኣንተ መጥፋትህ ነው” የሚል ፕሮፖጋንዳ ብቸኛው የድጋፍ ምንጭ ኣድርጋ ስትጠቀምበት የነበረችው ከንቱ መቅረት የጀመረውና ህዝቡ የራስ መተማመኑ መመለስ የጀመረው ዓረና ትግራይ ከተመሰረተና በመላ ትግራይ ተንቀሳቅሶ ህወሓትን የሚያስንቅ ፖለቲካዊ ኣቋምና ከሌሎች ኢትዮዽያውያን ለትግራይ ህዝብ ሊያጠፋ የሚያስብም የሚችልም እንደሌለ በማረጋገጡ፣ ለዘመናት ድህነት፣ ሙስና፣ የመልካም ኣስተዳደር እጦት፣ በኣገሩ እኩል የመጠቀም መበትና ሌሎች ዲሞክራሲያዊና ሰብኣዊ መብቶች ሊከበሩለት የሚያስችል የተሻለ ኣማራጭ ይዞ ሲመጣ ከፍተኛ ድጋፉን ሰጥተዋል።

ህወሓት በኣጭር ግዜ ዓረና ያገኘው ህዝባዊ ቅቡልነት መርምሮ ለማስተካከልና ያጣውን ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ ከማስመለስ ይልቅ ዓረና ድርጅት ለማፍረስ ሰርጎ ገቦች ማሰማራትና በዓረና ኣባላት ላይ እስከ ግድያ የደረሰ ጥቃቶች ስትፈፅም ግዜዋን ኣሳልፋዋለች።

እነዚህ ፀረ ዲሞክራሲያዊ ተግባሮች በዓረና ኣባላትና በትግራይ ህዝብ ዘንድ የታዩት ህወሓት በሌላ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት መቀያር ያለባት መሆንዋ ራስዋ ያቀረበቻቸው ማስረጃዎች ሁነው ጠቅመዋል።

የዘንድሮ 2007 ምርጫ የህወሓት ህዝባዊ መሰረት ከስሩ የተነቀለበትና በስልጣን የመቆየትዋ ምክንያት የትግራይ ህዝብ ድጋፍ ሳይሆን ጠበንጃዋና ዓፈናዋ ብቻ መሆኑ ፍንትው ኣድርጎ ኣሳይቶን ኣልፈዋል።

የ”100 ፐርሰንት” ድምፅ ልፈፋ በመሬት የሌለ መሆኑ የኢትዮዽያና የትግራይ ህዝብ፣ የተቃዋሞ ድርጅቶችና ኣባሎቻቸው፣ የተቀዋሚ ደጋፊዎች፣ የገዢው ፓርቲ ኣመራሮች(ምርጫው ካለፈ ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ የትግራይ ካድሬ ሰብስበው ኣዋርዳቹናል በሚል ዘለፋና ስድብ ኣዝንቦባቸው ነበር) ፣ ኣባላትና ደጋፊዎች ሳያወላውሉ ያረጋገጡበት ዕድል ፈጥሮ ኣልፈዋል።

 

የምርጫው ምጤትም

—————-

 

፩) የዓረና ኣባላትና ደጋፊዎች የዘንድሮ ምርጫ የትግራይ ህዝብ ተሳትፎና ለዓረና የነበረው ድጋፍ በጣም ኣስገራሚ ነበር። ህዝቡ የህወሓት ያማጥላላት ፕሮፖጋንዳ ሳያደናግረው በልበሙሉነት ዓረናን መርጠዋል። የዓረና ኣባላትና ደጋፊዎች በኣሁኑ ሰዓት የኣሸናፊነት መንፈስ የድል ኣድራጊነት ወኔ ተላብሰው የገኛሉ።

 

፪) የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ኣመራሮች፣ ኣባላት፣ ሙሁራንና ወጣት ኣባሎች ከፍተኛ የሽንፈት ስሜት አያንፀባረቁ ይገኛሉ። እነዚህ የህወሓት ኣባሎች በሁት የሚከፈሉ ሲሆኑ የኣዲስ ኣበባና የትግራይ ኣንጃዎች ተብለው ተባዱነዋል።

 

፫) የ”ልማታዊ ባለሃብቶች” ተብለው በህወሓት የተመደቡትና ህወሓት ፈጠርኳቸው ብሎ ዘወትር የሚዘምርላቸው ባለሃብቶችም በህወሓት ህልውናና የመቧደን ስራ ተጠምደው ይገኛሉ። እነዚህም የኣዲስ ኣበባና የትግራይ የሚል ስም ይዘዋል።

 

፬) ወጣትና ፊደል ቀመስ የህወሓት ኣባላትም እንደዚሁ የትግራይና የኣዲስ ኣበባ የሚል ቡዱን ሰርተው በየፊናቸው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

 

፭) የትግራይ ወጣቶችም የህወሓት ኣቅመቢስነትና እንደ ህዝባዊ ድርጅት የመቀጠል እድሏ ኣጠራጣሪና እርባና ቢስ መሆኑ በመረዳት የተልያዩ መሰባሰቦችና ኣዲስ ፖለቲካዊ ድርጅት የመመስረት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ሙከራዎች እያደረጉ ይገኛሉ።

 

እነዚህ እንቅስቃሴዎች ህወሓት ኣሁን ባለችበት ደረጃ ሁና መቀጠል እንደማትችል ድምዳሜ የደረሱ ናቸው።

 

“በኣሁኑ ሰዓት ህወሓት በጥሩ ኣቋም ላይ ትገኛለች” የሚል ኣቋም ይዘው የሚንቀሳቀሱ የትግራይ ክልል ቡድን ኣቶ ኣባይ ወልዱና ቴድሮስ ሓጎስ የሚመሩት ሲሆን የነዚህ ደጋፊ የሆነው የወጣቶች ቡድን “ስልጣኑ ለኛ ወጣቶች መሸጋገር ኣለበት” የሚል የኣዳሽ ኣቋም ይዞ የሚደግፋቸው ነው።

 

የነሓሴ ወር ጉባኤና የሁለቱ ኣንጃዎች ቅስቀሳ

————————————-

 

ህወሓት 12ኛው ጉባኤዋ በመቐለ ከተማ ነሓሴ 14/ 2007 ትጀምራለች።

በዚህ ጉባኤ ኣሸንፎ ለመውጣት የኣዲስ ኣበባና የትግራይ ኣንጃዎች የየራሳቸው ቅስቀሳዎች እያካሄዱ ይገኛሉ።

  1. A) የትግራይ ቡዱን = ይህ ቡዱን “ትግራይ በጣም ኣድጋለች፣ ህዝባችን ከድህነት ተላቀዋል፣ 11 ፐርሰንት ኣድገናል፣ ሙስናና መልካም ኣስተዳደርም ጠላቶች(ዓረናና የኣዲስ ኣበባ ኣንጃ በኣንድነት የሚከስ ነው) እንደሚያወሩት ኣይደለም። መለስ የተወልን ራኢ ይዘን ለ50 ዓመት ኢትዮዽያን እንገዛለን” የሚል ሆኖ እንደ ዋነኛው ሃይል ኣድርጎ የሚንቀስቀሰውም

1) ከክልል እስከ ቀበሌ የተደራጀው ኣባልና ኣቶ ኣባይ ወልዱን ሊቀ መንበር ኣድርጎ ያስመረጠው ኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ(1ለ5) ኣደረጃጀት ተጠቅሞ የኣዲሳበባው ኣንጃ በጉባኤው ካድሬውን ተጠቅሞ ኣሽቀንጥሮ ለመጣል ነው። የዚህ ማሳያም በመላ ትግራይ ያሉት ኣደረጃጀቶች የጉባኤው ተሳታፊ ካደሬ መልምሎ “.የመለስ ራኢ እንዳትክዱ ድርጅታችንን እንዳትወድቅ ኣደራ” እያለ እያስማለቸው ይገኛል።

2) በትግራይ ክልል ያሉት ባለሃብቶች በተለይም ከባለስልጣኖች ተባብረው ሃብት ያጠራቀሙ ደጋፊዎቻቸው ኣደራጅተው የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ለማሸነፍ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

፫) የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት ሁነው ከፍተኛ ሃብት መሰብሰብ የቻሉትን ጭምር ድጋፍ ለማግኘት እየሰሩ ናቸው።

 

B ) የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ= ይህ ቡድን “የመለስ ራኢ” የሚል ሽፋን ተከናንበን ትግራይ ውስጥ እየሰራን ያለነው ለድርጅታችን ህልውና ኣደጋ ላይ የሚጥል ነው” የሚል ኣቋም ያንፀባርቃል።

በትግራይ ክልል ድህነት ኣንሰራፍተዋል፣ ረሃብ፣ የመልካም ኣስተዳደር ችግር፣ የሙስና መስፋፋት፣ በኣጠቃላይ “የመለስ ራኢ” በሚል ሽፋን ተሽፍነን በዳታ ክምር ብቻ ድርጅታችን መቀጠል ኣትችልም።

ተቃዊሚዎች እያግኙት ያሉት የህዝብ ድጋፍም በያዙት ጠቃሚ ኣማራጭ ሳይሆን በኛ ድክመት ነው” የሚል ኣቋም ይዘው እየተታገሉ ነው።

 

ሀ) የነ ዶክተር ደብረፅዮንና ዶክተር ኣርከበ ዕቑባይ የሚመሩት ኣንጃ ሲሆን “ህወሓት ኣሁን ባለችበት መንገድ ከቀጠለች ለህልውናዋ ኣደጋ ነው።” የሚሉትና “ኣሁን ከቀበሌ እስከ ፖሊት ቢሮ ያለው ኣመራር ኣቅመ ቢስና በሙስና የተዘፈቀ መሰረታዊ የኣመራር ለውጥ ማምጣት ግድ የሚል ነው” ብሎ የሚያምን ነው።

 

ለ) የዚህ ኣንጃ ደጋፊዎች በትግራይ ክልል እንዳይሰሩ የተለያዩ እንቅፋቶች የደረሰባቸው ባለ ሃብቶች እና በተለያዩ ጫናዎች ተሰላችተው ከትግራይ የተሰደዱ ልማታዊ ባለሃብቶች ሲሆኑ እነዚህም የትግራዩ ኣንጃ ከተሸነፈ በትግራይ መስራት የሚፈልጉ ናቸው።(ኣቶ ኣባይ ወልዱ ወደ ኣስተዳዳሪነት በመጡበት ወቅት ከኣለማጣ እስከ ሑመራ እነ ገዛገርላሰና ኣርጋዊ ሃይሉ ጨምረው ከ110 በላይ ባለሃብቶች ማሰራቸው የሚታወስ ነው።)

 

ሰሞኑን ኣቶ ዳዊት ገብረእግዚኣብሄር በዓይጋ ፎረም በኩል የትግራይ ሁኔታና ያሉት ችግሮች ኣፍረጥርጠው የተናገሩትም የዚሁ ዘመቻ ኣካል ነው።

 

ሐ) የፌደራል ድህንነት መስራቤት= ለትግራዩ ኣንጃ ደግፈው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉት የወረዳ ካቢኔ ኣመራሮች በሙስና ማስያዝና ማሳሰር ጀምረዋል። ለምሳሌ የምስራቃዊ ዞን የኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ ሃላፊዎች ከፈዴራል የመጡ የደህንነት ሰዎች እየታሰሩ ይገኛሉ። በትግራይ ሙሰኛ ታሰረ ከተባለ በፈጠረው ፖለቲካዊ ልዩነት እንጂ ከክልል እስከ ቀበሌ ያለው የሙሰኛ መዓት ከማሰር ህወሓት ማሰር ይቀላል።

 

መ) በትግራይ ክልል ያሉ ልማታዊ ባለሃብቶች የዘረፉትን የህዝብ ሃብት ከነሙሉ ሰነዱ በማሳየት ለኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ለመቃወም ከሞከሩ ዘብጥያ እንደሚገቡ እያሳይዋቸውና በድንጋጤ ሽባ የሆኑ ይገኛሉ።

ሰሞኑን ኣንድ ሚልዮን ብር ለልጁ ጥሎሽ የሰጠ የክልል ምክር ቤት ኣባል “ልማታዊ ባለሃብት” በመቐለ ከተማ በጣም ኣነጋጋሪ ሆኖ ከማለፉም በላይ የትግራይ ክልል ኣንጃ ደጋፊነት ተፈርጀዋል።

 

በመቐለ ከተማ በመጪው የህወሓት ጉባኤ ኣቶ ኣባይ ወልዱ ከሚስታቸው ወይዘሮ ትርፉ ኪዳነማርያም ከስልጣናቸው እንደሚነሱ የተረጋገጠ መሆኑ እየተወራ ይገኛል።

 

የህወሓት ወደ ሁለት ኣንጃዎች የተከፈለችው ባለፈው ጉባኤ ሲሆን በወቅቱ የትግራይ ክልል ኣንጃ የነ ኣቶ በረከት ስምኦን ብኣዴን ድጋፍ ተብጅቶለት ባሸናፊነት ማጠናቀቁ ይታወቃል።

 

በኣሁነ ሰዓት የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በኣዲስ ኣበባ እየተካሄደ ይገኛል።

 

* ከታች ያለው ፎቶ የኣቶ ዳዊት ገብረእግዚኣብሄር ሲሆን ሰሞኑን በዓይጋ ፎሮም በትግርኛ ቃለ መጠይቅ ያካሄዱ ሲሆኑ በትግራይ ያለው ኣስከፊ የህወሓት ድክመት፣ ፀረ ልማት፣ ፀረ ዲሞክራሲና ፀረ ሰላም ተግባና ባህሪ ፍንትው ኣድርገው በማሳየት በዓረና ኣባላት፣ የፌስቡክ ኣክቲቪስቶችና ባጠቃላይ በትግራይ ህዝብ ሲነገለት የበሩት ተግባራት በርሳቸው የደረሱ በደሎች ጭምር በማቅረብ በተለይ ህወሓት በጭፍን ሲደግፉ ለነበሩት ወገኖች ኣስደንጋጭ ምግ ግር ኣድርገዋል።

 

የነዚህ ሁለት የህወሓት ኣንጃዎች ኣሸናፊ ሁኖ የሚወጣው ቡዱን በትግራይና በትግራይ ህዝብ እንዲሁም በኢትዮዽያ ህዝብ የሚያመጣው ወይም የሚፈጥረው ተኣምር የለም። የኣቶ ኣባይ ወልዱ ኣንጃ ካሸነፈ የኣሁንዋ ትግራይና ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ይቀጥላል ማለት ነው።

 

የኣዲስ ኣበባ ኣንጃ ካሸነፈ ደሞ በኣቶ ፀጋይ በርሀ የነበረችው ትግራይ ተመልሳ ትመጣለች እንደማለት ነው። ማንኝዓውም ኣንጃ ካሸነፈ ወደ ስልጣን የሚመጡ ሰዎች ይቀያየሩ እንደሆነ እንጂ መሰረታዊ የሚባል ለውጥ ኣይኖርም።

ያው << ወጮ ተገልበጥካዮ>> ወጮ ወይም ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ ኣያጣፍጥም እንደሚባለው ነው። የትግራይ ወጣቶች የጀመራቹት ኣዲስ ዲሞክርሳሲያዊ ድርጀት የመመስረት ስራቹ ጥንክራቹ ግፉበት። ከዓረና ትግራይ ጎን ተሰልፈን ያለነውም ከሌሎች ኢትዮዽያውያን ጓዶቻችን ሁነን ዲሞክራሲያዊት ትግራይና ኢትዮዽያ በትላችን እውን እንደርጋለን።

 

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

 

አምዶም ገ/ስላሴ የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ሲሆን ከዚህ ቀደም የፕ/ት ኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ላይ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ በሰጠው ማብራሪያ የህወሃት መሪዎች በአባኢ ወልዱ የመቀሌው ቡድን በዶ/ር ደብረ ጽዮን የሚመራ ሲሆን በጊዜው የቡድኑን አሰላለፍ ተከትሎ አንዳንድ ካድሬዎች የእስር ሰለባ እንደነበሩ መዘገባችን አይዘነጋም። ሁለቱም ቡድኖች ከብአዴን ተላላኪዎችን በደጋፊነት በየበኩላቸው ለማሰለፍ ጥረት ላይ መሆናቸውንም በጊዜው ጠቁመን ነበር።

ህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *