የተቃዋሚ አመራሮች ላይ ለመመስከር የተዘጋጁ የሐሰት ምስክሮች በፖሊስ አጀብ በተበዳይ ቤተሰቦች ላይ ክትትል ማድረጋቸው ተገለጸ

Mamushet_Amare_01-new_1

የመኢአድ ሕጋዊ ፕ/ት አቶ ማሙሸት አማረና ሌሎች የፓርቲው በእስር ላይ የሚገኙ የእስር አመራሮችና አባላት ላይ አገዛዙ ላዘጋጀው የሐሰት ክስ ለመመስከር የተዘጋጁ የራሱ የቀበሌ የተደራጁ የስለላ ቡድኑ አባላት የተበዳይ ቤተሰቦችንና፣ችሎቱን ለመከታተል የሚሄዱ ፓርቲው አባላትን ያለ ፍላጎት ፎቶ በማንሳት፣ቪዲዮ ከመቅረጽ አልፈው በመኖሪያ አድራሻቸው በፖሊስ አጀብ ታግዘው ክትትል እያደረጉና እያስፈራሩዋቸው እንደሚገኙ ለተበዳይ ቤተሰቦች ቅርብ የሆኑ የህብር ምንጮች ገለጹ።

የዛሬዎቹ የሀሰት ምስክሮች ከመሰከርን እንፈራለን በሚል ፍርድ ቤትን ተገን አድርገው የተበዳይ ቤተሰቦችንና የትግል አጋሮችን ለማሸማቀቅ ያቀረቡት አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ማስረጃ ካላችሁ ክሰሱ ብሎ ምስክርነቱን መስማት እቀጥላለሁ በማለቱ ዛቻው ቤት ለቤት የተበዳይ ቤተሰቦችን በፖሊስ አጀብ ማሳደድና ማስጨነቅ ሲሆን ይህም የሚሰጡትን የሀሰት ምስክርነት ተከትሎ ማንነታቸው ለአደባባይ እንዳይወጣ ማሸበር መያዛቸውን እነዚሁ ምንጮቅ ገልጸዋል። በምንጮቻችን መረጃ መሰረት አቃቤ ህግ በአቶ ማሙሸት አማረ ላይ ያደራጃቸው የሀሰት ምስክሮች ወጣት አቢይ ሀጎስ ረዳ ፣ ወጣት አብዱልፈታ አብድልቃድር ሀቢብ ፣ወጣት አለሙ ሀይሉ ገ/ሕይወት እና ዮሃንስ መዝገቡ አብርሃ ናቸው። ግለሰቦቹ የበታች የደህነት አባላት መሆናቸውን በቀበሌ አካባቢ የሚያውቋቸው የህብር ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል።

አቶ ማሙሸት አማረ ከዚህ ቀደም አይ.ሲ.ስን ለመቃወም በሰልፉ ላይ ተገኝቶ አመጽ ሲቀሰቅስ ነበር ለሚለው የአገዛዙ የመጀመሪአ ክስ ሲ.ኤ.ም.ሲ በሚገኘው ፍርድ ቤት ሁለት የሀሰት ምስክሮች ቀርበው <<አቶ ማዩሸት በስፍራው ነበር አመጽ ሲያስነሳ ብጥብጥ ሲያደርግ ነበር>> ብለው የመሰከሩ ሲሆን በዕቱ አቶ ማሙሸት በልደታ ፍርድ ቤት ከመኢአድ ሕጋዊ ፕ/ት ሀላፊነቱ በሕገውጥ ውሳኔ ከሶ አባረረውን ምርቻ ቦርድን ከሰው ልደታ ፍርድ ቤት በመሆኑ ይህብኑ ከፍርድ ቤቱ በሰውና በሰነድ ማስረጃ አቅርቦ ክሱ ተቋርጡ ይፈቱ የሚል ውሳኔ ፍርድ ቤት ቢሰጥም ውሳኔው ሳይከበር ከእስር ቤት እስር ቤት ተዛውሮ ክሱ በሰልፉ ዋዜማ በአይ.ሲ.ስ ልጆቻቸውን ያጡን ለቅሶ ደርሶ የአካባቢውን ወጣቶችን ለአመጽ አደራጅቷል ወደሚል ተለውጧል።በጊዜው የአራዳ ፍርድ ቤት አዲሱን ክስ አይቶ በአምስት ሺህ ዋስ ይውጡ ቢልም ለሁለተና ጊዜ ውሳኔው ተጥሶ ዛሬም እስር ላይ ናቸው።

Mamushet_court_order_060215_002

በአሁኑ ወቅት የምርቻ ቦርድን ሕገ ወጥ ውሳኔ ያልተቀበሉ የመኢአድ ሕጋዊ አመራር አባላትና አባላት አቶ ማሙሰት አማረን ቸምሮ በመላው አገሪቱ እየታደኑ በርካቶች ታስረው የሚገኙ ሲሆን የፓርቲው ም/ል ፕሬዝዳንት በፍርድ ቤት በማዕከላዊ እስር ቤት ዘራቸው እየተጠቀሰ የደረሰባቸውን ኢሰብኣዊ ኤአያዝ፣ድብደባና አጼአፊ ንግግር ለማስረዳት ሞክረው ተደጋግሞ በፍርድ ቤት ክልከላ የተደረገባቸው ሲሆን በሀሰት የሽብር ክስ በሌላ ችሎት እየተመላለሱ ሲሆን የፓርቲው የውጭ ግንኙነት በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ከፍተና ድብደባ እየተፈጸመባቸው ያሉበት ሁኔታ እንዳይታወቅ ቤተሰብም ፣ ጠበቃም ሆነ ጓደኛ እንዳይጠይቃቸው ተከልክሎ የቅርብ የትግል አጋሮቻቸው ስላሉበት ሁኔታ ስጋት ውስት እንዳሉ ለህብር በላኩት ማስታወሳ ገልጸዋል።በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ዘገባ እናቀርባለን።

ህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *