እንኳን ለቡሄ አደረሳችሁ! በኢትዮጵያ ያለውን አፈና በቡሄ ዜማ!

በአዲስ አበባ ህጻናት በቡሄ ጭፈራ ላይ እና የቡሄ ደመራ
በአዲስ አበባ ህጻናት በቡሄ ጭፈራ ላይ እና የቡሄ ደመራ

ህፃናት በጠዋቱ፡- ከዛ ማዶ ‹‹አሸባሪ››፣ ከዚህ ማዶ ‹‹አሸባሪ››

ኢህአዴግን አስደንባሪ፣

አንድ ለአምስት አቃጣሪ፣

ሆያ ሆዬ ጉዴ እኔንም ሊያስረኝ ነው እንዴ?

ሲሉ የሰማሁ መለኝ! (በነገራችን ላይ የከተማ አስተዳደሩ ሳይፈቅድላቸው ነው እንዲህ ዱላና ሌሎች ፀረ ሰላምነታቸውን በግልፅ የሚያሳዩ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያዎችን ይዘው የወጡት፡፡ በቅርቡ ዶክመንተሪውን ይጠብቁ!) ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው

የጥንቱ የቡሄ ጭፈራ ግጥም ሲታወስ

ሆያ….. ሆየ! ሆያ….. ሆየ! እዛ ማዶ ጭስ ይጨሳል፣

አጋፋሪ ይደግሣል፡፡

ያቺን ድግስ ውጬ ውጬ፣

በድንክ አልጋ ተገልብጬ፡፡

ያቺ ድንክ አልጋ አመለኛ፣

ያለ አንድ ሰው አታስተኛ፡፡

ሆይሽ ሆዬ ጉዴ፣

ጨዋታ ነው ልማዴ፡፡ ….

የእኔማ ጌታ የሰጠኝ ሙክት፣

ባለዶቃ ነው ባለምልክት፣

መስከረም ጠባ እሱን ሣነክት፡፡

የእኔማ እመቤት የፈተለችው፣

የሸረሪት ድር አስመሰለችው፡፡

ሸማኔ ጠፍቶ ማርያም ሰራችው

 

ህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *