የአርበኞች ግንቦት 7 ታላቅ አገራዊ ስብሰባ ዛሬ በጎልድ ኮስት ሆቴል ይካሄዳል ፣ የፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ የግንባሩ መሪዎች መልዕክት ይተላለፋል

 የግንባሩ መሪዎች ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ነአምን ዘለቀ እና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ (ፎቶ ዘ-ሐበሻ)
የግንባሩ መሪዎች ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ነአምን ዘለቀ እና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ (ፎቶ ዘ-ሐበሻ)

የአርበኞች ግንቦት 7 ሀገር የማዳን ጥሪ በሚል መሪ ቃል የጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ዛሬ ከቀኑ 5 ፒ.ኤም ጀምሮ በላስ ቬጋስ በጎልድ ኮስት ሆቴልና ካዚኖ ይካሄዳል ።የግንባሩን መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ የመሪዎቹ መልዕክት እንደሚተላለፍና በአካል ከድርጅቱ አመራሮች መካከል አቶ ሙሉነህ እዩኤልና አቶ ጋሻው ገብሬ ይገኛሉ።

ለአርበኞች ግንቦት 7 ባለፈው ዕሁድ በዋሽንግተንና በሲያትል ቅዳሜ በዳላስ ከፍተኛ ሕዝብ በየስብሰባው አዳራሽ ተገኝቶ ለትግሉ አለውን ድጋፍ ላቅ ባለ ደረጃ አሳየ ሲሆን በዚህም ከሶስቱ ከተሞች ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ($200 ሺህ ዶላር) መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል። በዳላስ በአንድ የውጭ አገር ዜጋ የተሰራው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ምስል በ38 ሺህ ዶላር ጨረታ ሲሸጥ በዲሲ በከፍተና ፉክክር ለሌላ የአቶ አንዳርጋቸው ምስል ከሰባ ሺህ ዶላር በላይ በጨረታ አውጥቶ ተሸጧል።

ከግንባሩ መሪዎች መካከል ሊቀመንበሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ኤፍሬም ማዴቦ እና ሌላው ከፍተና አመራር አቶ ነአምን ዘለቀ ለወሳኝ ትግል ኤርትራ መግባታቸው በአገር ውስጥና በውጭ በነጻነት ወዳዱ ወገን ከፍተና መነቃቃት የፈጠረ ሲሆን በተቃራኒው በአገዛዙ መሪዎች ዘንድ መደናገጥ መፍጠሩን አስቀድመን በህብር ሬዲዮ መዘገባችን ይታወሳል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *