የቀድሞ የአንድነት ከፍተኛ አመራር የጻፈው <<ሀገር የተቀማ ትውልድ>> ተነባቢ ሆነ

የ> ደራሲ ዳንኤል ተፈራና የመጽሐፉ ገጽ
የ<<ሀገር የተቀማ ትውልድ>> ደራሲ ዳንኤል ተፈራና የመጽሐፉ ገጽ

የቀድሞው የአንድነት ከፍተኛ አመራር በሆነው በዳንኤል ተፈራ ሰሞኑን ተፅፎ ለገበያ የቀረበው ‹‹ሀገር የተቀማ ትውልድ›› የተሰኘው ወጥ የሆነ የፖለቲካ መፅሐፍ እየተነበበ መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡

እንደምንጮቻችን ገለፃ ወጣቱ ደራሲ፣ አርታኢና ፖለቲከኛ ዳንኤል ተፈራ በአጠቃላይ ለአንባቢ ያደረሳቸው መፅሐፎች ሦስት ሲሆኑ ስድስት ለሚሆኑ የፖለቲካ መፅሐፎችም የአርትኦት ስራ ሰርቷል፡፡ ሰሞኑን ገበያ ላይ ውሎ እየተነበበ ካለው ‹‹ሀገር የተቀማ ትውልድ›› ከሚለው መፅሐፉ በፊት እጅግ ተነባቢ የሆኑ ሁለት መፅሐፎችን ለአንባቢያን እንዳደረሰም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የደራሲው ቀዳሚ ስራ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና በኋላም የተቃውሞ ጎራው መሪ የነበሩትን ዕውቅ ሰው ዶ/ር ነጋሶ ጎዳዳ ሶለንን የህይወት ታሪክ የሚዳስስ ‹‹ዳንዲ- የነጋሶ መንገድ›› የተሰኘው ነው፡፡ ይሄ መፅሐፍ በ2003 ዓ.ም ለህትመት የበቃ ሲሆን በአንድ ሳምንት ብቻ ሃያ ሺ ኮፒ በመሸጥ ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው፡፡ ከዚያ በኋላም ለአራት ጊዜ እንደታተመ ደራሲው አረጋግጧል፡፡ ደራሲው እንደሚገልጠው መጽሐፉ 384 ገፆችና አምስት ንዑስ ክፍሎች ያሉት ሲሆን የዶክተሩን ከልጅነት እስከ ዕውቀት እንዲሁም የፖለቲካ ታሪካቸውን ያካተተ ነው፡፡ መፅሐፉን ለማዘጋጀት አመት ከሶስት ወር እንደፈጀ ደራሲው ይናገራል፡፡

ቀጣዩ የዳንኤል ስራ ከ1997 ዓ.ም በኋላ በፓርላማ አባልነታቸው በከፍተኛ ተከራካሪ በነበሩት የተከበሩ አቶ ተመስገን ዘውዴ የፖለቲካ ህይወትና እንዲሁም በፓርላማው ውስጥ ሕወሃት/ኢህአዴግ ሲፈፅም የነበረውን ሸፍጥ ያጋለጡበት ‹‹ከፓርላማው በስተጀርባ›› የተሰኘው መፅሀፉ መሆኑን ለዘጋቢያችን ተናግሯል፡፡

ሰሞኑን ገበያ ላይ የዋለው ‹‹ሀገር የተቀማ ትውልድ›› ደግሞ የፀሃፊው ወጥ የፖለቲካ ስራ ሲሆን 224 ገፅ ያለው ነው፡፡ መፅሐፉ በ27 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በዋናነት በዘመነ ኢህአዴግ ወጣቱ ትውልድ እንዴት የሀገር ፍቅር እንዲያጣ እንደተገረገና ሀገር አልባ ለማድረግ የተከናወኑ የፖለቲካ ሸፍጦችን የሚተርክ መፅሐፍ ነው፡፡ ደራሲው እንደገለፀው፡- ‹‹ስርዓቱን በአሽከርነት ካላገለገልክ እጣ ፈንታህ ሃገር መቀማት ነው፡፡ ‹‹ሃገር ማለት ሰው ነው!›› ይሉሃል እንጂ ሃገር ኢህአዴግ ሆኗል፡፡ ኢህአዴግ ካልሆንክ ስራ አይኖርህም፣ ኮንዶሚንየም አይደርስህም፣ መነገድ አይፈቀድልህም፣ ደመወዝ አይጨመርልህም፣ ጡረታ አይከበርልህም፣ የትምህርት እድል አይሰጥህም፣ በነፃነት መወዳደርና ጨረታ ማሸነፍ አያስችልህም፡፡ ይህ ማለት ሃገር ተቀምተሃል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ለመፃፍና ትውልዱ ሀገር እንዲቀማ የሰሩ፣ የቀሙ፣ ያስቀሙ፣ ያቀማሙና የተቀሙትን ታሪክ በማንሳት ሀገር ይረከባል የሚባለው ትውልድ እንዲነቃቃና የሀገር ባለቤት እንዲሆን በማሰብ የተፃፈ ነው በማለት ሀሳቡን ገልጧል፡፡

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *