Hiber Radio : የህወሓት የስልጣን ሽኩቻ ድርጅቱንና የሚቆጣጠረውን ኢህአዴግን ያዳክማል ተባለ፣ተቃዋሚዎች ተባብረው እንዲቆሙ ተጠየቀ፣አቶ በቀለ ገርባ ኢትዮጵያ ሲገቡ ምን እንደሚጠብቃቸው እንደማያውቁ ገለጹ፣ የአረንጓዴዎቹ ጎርፎች የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የቤጂንግ ድል፣ የሱዳን ባለስልጣን ድንበሩ ካልተካለለ መፍትሄ የለም ማለታቸው፣አቶ አንዳርጋቸውን ለምስክርነት የጠሩት የመኢአድ አመራሮች በቅሊንጦ ድብደባ ተፈጸመባቸው፣ አርበኞች ግንቦት 7 ለነጻነት የሚያደርገው ትግል እንደ ወያኔ 17 ኣመት ጫካ ውስጥ መንፏቀቅ አይጠይቀውም መባሉ፣ኢትዮጵያ ሳተላይት ወደ ህዋ አመጥቃለሁ ማለቱዋ ምዕራባውያንን ማስገረሙ እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 24 ቀን 2007 ፕሮግራም

<…የህሓት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ በጉባዔው በግልጽ ታይቷል። በተለይ ተቃዋሚን ለማጥቃት ያደራጁት አንድ ለምስት በስልጣን ክፍፍሉ ወቅት ለአቶ አባይ ወልዱ ቡድን ትልቅ ሚና ነበረው። የአቶ ስብሃት ቡድን የአዲስ አበባው ቡድን ነው የሚደግፈው በዚህ ጉባዔ የሳቸው ተቀባይነት እየቀነሰ መሄዱ በግልጽ ታይቷል። ሁለቱም አዲስ አበባውም ሆነ መቀሌው ቡድን ዓላማቸው አንድ ነው ነገር ግን የውስጥ ሽኩቻ ሲኖር መዳከም አይቀርም … የኢህአዲግ የበላይ ህወሓት ነው ። የህወሓት መዳከም የኢህአዴግን መዳከም ያስከትላል…ተቃዋሚዎች በአንድ ላይ መቆም አለባቸው…> አቶ ምዶም ገ/ስላሴ የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ የህወሓት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻና መዘዙ በተለይ ለለውጥ የሚደረገውን ትግል በማፋጠን በተመለከተ ያለውን ሚና ጭምር አንስተን ተወያይተናል። (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…በቅሊንጦ ከሕጋዊው የመኢአድ አመራሮች አንዱ አቶ መለሰ መንገሻ በተፈጸመበት ድብደባ ከተኛበት መነሳት አይችልም ። ሰውነቱ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ሌሎች እስረኞች ነግረውናል ። አቶ ዘመነም እጁ በካቴና የታሰረበት ጣቶቹ አብጠው መንቀሳቀስ አይችሉም …አንድ ሰው እስኪቀር ሆን ተብሎ መኢአድ ሕጋዊ አመራሮችና አባላት ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እንታገላለን …> አቶ አበበ ውቤ የሕጋዊው መኢአድ አመራር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወታቴች ጌዳይ ሀላፊ በቅሊንጦ ድብደባ የተፈጸመባቸውን በተመለከተ ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በአማርኛን ቋንቋ በአይፎን ለመተየብ የሚያስችለውን ቀላል ዘዴ ተግባራዊ ካደረጉት ኢትዮጵያዊ ምሁር ዶ/ር አበራ ሞላ ጋር ያደረግነው ቆይታ (ሙሉውን ያዳምጡት)

አጼ ሃይለሰላሴ ከሞቱ ከአርባ አመት በሁዋላ ለምን ዛሬም በብዙዎች ዘንድ እንደ አዲስ   ይታወሳሉ? የግርማዊነታቸው ደካማ እና ጠንካራ ጎኖቻቸው ሲፈተሽ( ልዩ ጥንቅር )

ከመቶ ሺዎች በላይ ኢትዮጵያዊያን አህቶታችችን የሚገኙባት ቤሩት በቆሻሻ ሳቢያ የተቀሰቀሰባትሕዝባዊው የቆሻሻ አብዮትአክራሪው አይሲስን እንዳይጋብዝ ተሰግቷል

ሕዝቡ ለገዢዎቹ የጊዜ ገደብ ሰጥቷል፣ጠ//ሯምከደሙ ንጹህ ነኝ ፣ስልጣኔን እለቃለሁሲሉ አስጠንቅቅዋል

በቬጋስ የኢትዮጵያውያን ቀን ሊከበር ነው ቆይታ ከበዓሉ አዘጋጆች ጋር(ሙሉውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የህወሃት የስልጣን ሽኩቻ ድርጅቱንና የሚቆጣጠረውን ኢህአዴግን ጭምር ያዳክማል ተባለ

ተቃዋሚዎች እንዲተባበሩ ጥሪ ቀረበ

አቶ በቀለ ገርባ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ምን እንደሚጠብቃቸው እንደማያውቁ ገለጹ

በቅሊንጦ በእስር ላይ የሚገኙ የመኢአድ አመራሮች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመባቸው

 በቤጂንግ የአረንጓዴው ጎርፍ ባለድሎች በአንድ ቀን ሁለት ወርቅ በማግኘት ታሪክ ሰሩ

አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት እንደ ወያኔ 17 ዓመት ጫካ ውስጥ መንፏቀቅ የለብንም ሲሉ ገለጹ

አንድ የሱዳን አገረ ገዢ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር በአፋጣኝ እንዲካለል ጥሪ አቀረቡ

ኢትዮጵያ በመጭው አምስት ዓመት ሳተላይት ወደ ህዋ አመጥቃለሁ ማለቷ ምእራባዊያን ሸሪኮቿን አስገርሟል

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት ህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-083015-090615

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *