Hiber Radio : የሊቢያው አክራሪ ቡድን አይሲስ ኢትዮጵያዊኖችን ለጦርነት እየመለመለ መሆኑ ተጋለጠ ፣ አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የደገፉት የእንግሊዝ ፖለቲከኛ ከፍተኛውን የፓርቲ ስልታን አገኙ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ደስታቸውን ገልጸዋል፣ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሞቱ ወታደሮቿን ቁጥር ለመግለጽ ፈቃደኛ አለመሆኗ ተገለጸ፣ በሶማሊያ የህብረቱ ጦር ከአንድ ሺህ በላይ ወታደሮችን ማጣቱ ተገለጸ፣ በማዕከላዊ በደረሰባቸው ድብደባ አካል ጉዳተኛ የሆኑት የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቤቱታቸው ሳይሰማ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደባቸው ፣ሰማያዊ ፓርቲ አዲሱን ካቢኔ አቋቋመ እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መስከረም 9 ቀን 2008 ፕሮግራም

<… በተቃዋሚ ስም የተቀመጡት አንዳንዶች የአቶ ሞላን ክህደት መደገፋቸው ራሱን የቻለ ክህደት ነው። መንግስት ሰጠኝ ያለውን ተልዕኮ የፈጸመ ሰው ተመልሼ ወደ መንግስት ገባሁ ሲል ተቃዋሚ ሆነህ ምን ብለህ ነው የምታመሰግነው? ክህደት ነው ያልኩት ይሄንን ነውየሕዝቡ መሰረታዊ ጥያቄ የዲሞክራሲ ጥያቄ እስካልተመለሰ አንዱ ከዳ ሌላው ለስርዓቱ ጊዜያዊ ድል መስሎ ካልታየ በስተቀር ህዝቡ አንዱንም ቅስቀሳቸውን አልተቀበለውም ደገፉ የተባሉትም …>   አቶ ይድነቃቸው ከበደ የሰማያዊ ፓርቲ የም/ቤት ሰብሳቢ በግል የአገር ቤቱን የከዱትን አቶ ሞላን በተመለከተ ለስርዓቱ ቅስቀሳ ሕዝቡ ያለውን ስሜት ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…ምርጫ ቦርድ ለእነ አቶ አበባው የሰጣቸው መኢአድ ጽ/ቤቱን ብቻ ነው አባላቱ ከእኛ ጋር ናቸው። ብዙ ጠንካራ አደራጆች አባላት በየቦታው ታስረውብናል።ትግላችን ይቀጥላል …ፖለቲካው በቲፎዞ መሆን የለበትም። በአገሪቱ ያለው ኢፍትሐዊ ስርዓት እስኪለወጥ አቅማችንን አስተባብረን መታገል አማራጭ የለውም። የኢትዮጵየያ የተቃውሞ ፖለቲካ ያው እስሩንም መገደሉንም እያስተናገድን የምንሄድበት ነው። የታሰሩትን አለመርሳት ይገባል…> አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ሕጋዊው ፕሬዝዳንት ለህብር ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ ክፍል ሁለት (ሙሉውን ያዳምጡ)

በእንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ ትልቅ ጥረት ያደረጉት አዛውንቱ ፖለቲከኛ በፖለቲካው አደባባይ አሸናፊ የሆኑበት ሂደትና የወደፊቱ ጉዞዋቸው (ልዩ ጥንቅር)

በቬጋስ የኢትዮጵያውያን ታክሲ አሽከርካሪዎች የመብት ሙግት የፍርድ ቤት ሂደት (ቃለ መጠይቅ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የሊቢያው አክራሪ ቡድን አይሲስ ኢትዮጵያዊኖችን ለጦርነት እየመለመለ መሆኑ ተጋለጠ

የሃይማኖት ነጻነታችን ተደፈረ ያሉ ስድስት ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች ስልጤ ዞን ውስጥበአሽባሪነት ክስለከባድ እስራት ተዳረጉ

የተባበሩት አረብ ኢሜሪት  ለኢድ አልደሃ  በአል ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያንን ነዳዮችን ስጋ ልታበላ ነው  ተባለ

አቶ አንዳርጋቸው  ጽጌ አንዲፈቱ  ከፈተኛ ጥረት ያደረጉት የእንግሊዙ ፖለቲከኛ ሰሞኑን  ታላቅ ስልጣን አገኙ

ኢትዮጵያ ሶማሊያ ውስጥ ሰለሞተ ሆነ ሰለቆሰለ የመከላከያ ሃይል አሃዝ  መግለጫ አልሰጥም አለች በሶማሊያ የሚገኘው ህብረቱ ከአንድ ሺህ በላይ ወታደሮቹን ማጣቱን ወታደራዊ መረጃዎች ገለጹ

ከምርጫ በኋላ ድምጹ የጠፋው ሰማያዊ ፓርቲ አዲሱን  ካቢኔውን አዋቀረ

በማዕከላዊ በደረሰበት ድብደባ የአካል ጉዳተኛ የሆነው የህጋዊው የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቤቱታውን /ቤት ሳይሰማው ቀረ

የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዘመነ ምህረት እንደይጠየቅ እንደታገደ ነው

 ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት ህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-092015-092715

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *