ሶሪያዊው ስደተኛና ያልተጠበቀው አጋጣሚ የፈጠረላቸው ዕድል

Sirean_coach_ronaldo_03

በታምሩ ገዳ

ከወላጅ አባቱ ጋር በዘረኛዋ ጋዜጠኛ የተደበደበውታዳጊ ሰደተኛ ከ እውቁ ሮናልዶ እቅፍ ገባ

በቅርቡ የሶሪያውን የእርስ በርሰ ጦርነት ከሸሹት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰደተኞች መካከል እንድ ሰደተኛ አባት በምስራቅ አውሮፓ(ሃንጋሪ ውስጥ) ከፖሊስ ለማምለጥ ሲጥሩ በአንዲት ጋጠወጥ ሃንጋሪያዊት ጋዜጠኛ(ፔትራ ላሳዛሎ) ከእነ ወንድ ልጃቸው ተጠልፈው መወደቃቸውን ተከትሎ ጋዜጠኛዋ ወዲያውኑ ከሰራዋ ሰትባረር አሳዛኙም በደል የደረሰባቸው ሶሪያዊው አባት(ኦሳማ አብዱል ሞሸን)እና የ 7 አመቱ ለጃቸው ዛይድ የአለም መገናኛ ብዙሃናት ትኩረትን ስበው ሰንበተዋል። ታዲያ ሰሞኑን ከ ወደ ስፔን የተሰማው መልካም ዜና እንደሚያበሰረው ከሆነ የአባት እና የልጅዩው ሰደተኞች ገተመኝ ከልባቸው የዘለቀው የሰፔን እግር ኳስ አካዳሚባለፈው ሳምንት የ ስደተኝነት ፍቃድ እንዲያገኙ አመቻችቶላቸዋል። እኛ በዚያች ምግባረ ብልሹ ጋዜጠኛ እግር ተጠልፈው ከእነ ልጃቸው መሬት ላይ የወደቁት አባት(ኦስማን) በትውልድ አገራቸው ሶሪያ የ ቀደሞ እግር ኳስ አሰልጣኝ በመሆናቸው የሰፔንም መንግስት መተነኛ ልምምድ አደረገው ስፔን ወስጥ ወደቀደሞ ሰራቸው (አሰለጣኝነት )እንዲመለሱ እና አዲስ ህይወታቸውንም እንዲገነቡ ተሰፋ ሰጥቷቸዋል ።አባት እና ልጅም በሳምንቱ ማብቂያ (ቅዳሜ)እለት ወደ ስፔኑ በርናቡ ተጉዘው እወቁ የሪያል ማድሪድ ክለብ ከግራንዳ ከለብ ጋር ባደረጉት ውድድር እና 1ለ0 ባሸነፉበት ግጥሚያ ላይ በከብር እንግድነት ተገኝቷዋል ። ጨቅላው ዛይድም ከታዋቂው የአለማችን ፣የማድሪድ አጥቂ እና ፖርቱጋል ቡድን ተጨዋች ከክርስቲያን ሮናልዶ ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ቡድኑ ወ ደ ሜዳ ሲገባ ሮናልዶን አጅቦታል። በነገራችን ላይ የ ማድሪድ ክለብ በዚህ አመት ወስጥ ከሶሪያ ለተፈናቀሉ እና ስፔን ለተጠለሉ የ አንድ ሚሊዮን ዮሮ እርዳታ ለግሷል። ከልጅነቱ አንስቶ ሲመኘው የነበረው የሪያል ማድሪድ ከለብ እና ከተአምረኛው ሮናልዶ ጋር በአካል ለመገናኘት አድሉን ያገኘው ዛይድ በሺዎች የሚቆጠሩ የማድሪድ ክለብ ደጋፊዎች የቡድኑን መለያ ሹራብ ላጠለቀው ለታዳጊው ለዛይድ ያላቸውን ልዩ ፍቅር አሳይተዋል። እርሱም በመላሹ “ከልጅነቴ አንስቶ ልጎበኝው ሰመኘድው የነበርው ሪያል ማድሪድን ለመጎበኘት ታደልኩ”ብሏል።ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ማለት ይሄን ጊዜ ነው።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *