ሰበር ዜና ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ታሰረ

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ከልጁ ጋር እና የመጽሐፉ የገጽ ሽፋን
ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ከልጁ ጋር እና የመጽሐፉ የገጽ ሽፋን

የመን የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ዛሬ ማለዳ በየመን ወታደሮች ቁጥጥር ስራ መዋሉን የዋለ ሲሆን በየትኛው እስር ቤትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ተጨማሪ ማጣራት ለማድረግ ወደ የመን በተደጋጋሚ ደውለን ሳይሳካልን ቀርቷል።

የጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖትን መታሰር ከቤተሰቡ ጭምር ያረጋገጠው ሳውዲ የሚገኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሲሆን በዚህ ላለፉት ሶስት ቀናት ጋዜጠኛ ግሩም ሲታደን መቆየቱንና ዛሬ ማለዳ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን አረጋግጠውለታል።

ቤመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወቅታዊ ሁኔታ በመከታተል፣ለተቸገሩት የበኩሉን አስተዋጽዎ በማድረግ በውጭ ያሉ ወገኖቹ እንዲረዳቸው ጥረት በማድረግ ወቅታዊ መረጃ በማቅረብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ህብር ሬዲዮን ጨምሮ በዚያ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ወገኖቹ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ መረጃ ሲሰጥ ቆይቷል። በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ያሉ መንገድ አግኝተው በጦርነት ውስጥ ካሉበት እንዲወጡ ጉዳያቸው ትኩረት እንዲያገኝ ሲጥር የቆየ ቢሆንም ወደ አገር መግባት የማይችል በመሆኑ ወደ ሌላ አገርም መሻገር ሳይችል በየመን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን(ዩ.ኤን.ኤች.ሲአር) ዘላቂ መፍትሄ ሳይሰጠው ቆይቷል።

የጋዜጠኛ ግሩም መታሰርን አረጋገጠችለት ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ ለጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እንደገለጸችው ጋዜጠኛ ግሩምን ያሳሰረው ኢትዮጵያዊ መሆኑንና የታሰረበትም ምክንያት ” ከተለያዩ ሃገራት በተረጅዎች ስም ገንዘብ ትሰበስባለህ ፣ ወደ ከየመን ውጭ መረጃ ታሰራጫለህ ” የሚል ክስ እንደሆነ ጠቁማኛለች ።

በየመን ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መረጃን ከማቅረብ ባለፈ ፣ ረግተው በማያውቁት የየመን ከተሞችና በርሃ ላይ በአደጋ ተከበው ለሚሰቃዩ ስደተኛ ወገኖች በነፍስ ደራሽ የነበረው ብርቱ ጋዜጠኛ ግሩም የየመኑን የኢትዮጵያን የስደት መከራና ሰቆቃ የሚዳሰወስ “የሞት ጉዞ ” የሚል መጽሐፍ ማሳተሙ አይዘመጋም ።

በጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት እስራት ዙሪያ ህብር ሬዲዮ በቀጥታ ወደ ቤተሰቡ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ አድርገን ለጊዜው ስልኩ ባይሰራም ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንቀርባለን።

የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠና የሆነው ግሩም ተ/ሀይማኖት በአገር ቤት በሳተናው፣በአስካልና ምንሊክን ጨምሮ በተሌአዩ የነጻ ፕሬስ ጋዜጦች ላይ የሰራና በተደጋጋሚ የታሰረ፣በተደራራቢ ክስ የነበረበት ሲሆን በአስቸጋሪ ሁኔታ ከአገር ወጥቶ ወደ የመን ተሰዶ ከአስር ኣመት በላይ በየመንና በተለያዩ አረብ አገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹን ሁኔታ በመከታተል ሲጽፍ ቆ ሲሆን የሞት ጉዞ መጽሐፉም የወገኖቻችን አስከፊ ስደት ውጤትን በብዕሩ ከትቦ ለንባብ አብቅቷል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *