ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖትን በየመን ፖሊሶች እንዲያዝ ያቀነባበረው ግለሰብ ከኤምባሲ ሰዎች ጋር ግንኙነት እንዳለው ተገለጸ ፣በሀሰተኛ መንገድ የተቀነባበረበት ክስ ለሕይወቱ አደገኛ መሆኑ ተገለጸ

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ከልጁ ጋር እና የመጽሐፉ የገጽ ሽፋን

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ከልጁ ጋር እና የመጽሐፉ የገጽ ሽፋን

በየመን ፖሊሶች ዛሬ ማለዳ ሰንዓ ውስጥ የታሰረው ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖትን በሀሰተኛ የሰላይነት ስም የከሰሰው ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ግርማ ወ/ሰንበት የሚባል ሲሆን ከዚህ ቀደም ከግሩም አጠገብ የነበረና በአሁኑ ወቅት ከኤምባሲ ሰዎች ጋር በመሆን በግሩም ላይ ለሳውዲና ለእስራኤል ይሰልላል የሚል መሰረተ ቢስ ሀሰተናኛ ክስና በተጨማም፣በስደተኞች ስም ገንዘብ ከውጭ ያስመጣል ማለቱን ፖሊሶች እንደገለጹላቸው የህብር ምንጮች ከሰንኣ ገለጹ።

ግለሰቡ ግሩም ከታሰረ በሁዋላ በኤምባሲ በር ላይ ወድቀው ለወራት አገራቸው መግባት ያልቻሉና ግሩም በተደጋጋሚ ወገኖቹ እንዲረዳቸው ሲጠይቅላቸው፣ ምግብ ከራሱና በየመን ከቁ ወገኖቹ ጭምር እያስተባበረ ሲደግፋቸው የነበሩትን <<በስማችን ገንዘብ ተወስዷል>> በሉና ምስክርነት ስጡ ብሎ ሲያግባባቸው እንደነበር እነዚሁ ምንጮች ገልፀዋል።ይህ ግለሰብ በአገር ቤት የሲቪል ሰርቪስ እሰራ ነበር የሚልና በባህር በአደገኛ ሁኔታ ወደ የመን በመጣበት ወቅት ግሩም ተቀብሎ እንዳስተናገደው የግሩም <<የሞት ጉዞ>> የተሰኘው መጽሐፍ ሲመረቅ በስፍራው እንደነበር አስታውሰዋል።ይህን ግለሰብ ደውለን ስለ ሁኔታው ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ሞክረን ሳይሳካልን ቀርቷል።

ግለሰቡን በሚመለከት በደረሰን ተጨማሪ መረጃ ከግሩም መታሰር በሁዋላ ታቢአ ሄዶ ምስክሮች እንደሚያመታ ገልጾ ሲወጣ <<ግሩምም ዝባላ እስር ቤት አስገባለሁ>> ብሎ ሲዝት በአካባቢው ከነበሩ በሁኔታው ከተበሳጩ ኢትዮጵያውያን ግር መጋጨቱን ገልጸዋል። በዚህ ግጭት ሳቢያ ወደ ጣቢያ ተወስዶ እንደነበር ይታሰር ይልቀቁት የሚታወቅ ነገር እንደሌለ አመልክተዋል።

በየመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኛ የሆነ ዳንኤል የተባለ ግለሰብ በበኩሉ በጦርነቱ እግራቸው የተቆረጡ ኢትዮጵያውያንን በስማችን ግሩም ገንዘብ ወስዷል ባላችሁ መስክሩ በሚል ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ በኤምባሲ ጉዳያቸው የተያዘ እነዚህን ግለሰቦችን ጣቢያ ወስዶ በሀሰት ሊያስመሰክር እቅድ እንዳለው በይፋ ሲናገር መስማታቸውን ገልጸዋል።

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት ላይ የተቀነባበረው ሀሰተና ክስ ለህይወቱ ሚአሰጋ በመሆኑ ጉዳዩ ትኩረት አግኝቶ ከተመሰረተበት ሀሰተና ክስ ነጻ እንዲሆን በየመን እና አካባቢው ያሉ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ሁሉም የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ እነዚሁ ምንጮች ገልጸዋል።

በሳውዲ ሚገኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ዛሬ ማምሻውን የግሩምን ሁኔታ ተከታትሎ ከባለቤቱ መታሰሩን ማረጋገጡን ጠቅሰን አስቀድመን መዘገባችን ይታወሳል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *