ዛሬ ከእስር የተፈቱት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እስር ቤት የቀረው በፍቃዱ ሐይሉ እንዲፈታ ጠየቁ

zone_9_blogers_ask_02

ከነጻዎቹ ዞን ዘጠኝ ጦማሪያን መካከል በፈጠራ ክስ ሳቢያ 541 ቀናት ታስረው ትላንት በፍርድ ቤት ነጻ የተባሉትና ዛሬ የተፈቱት ጦማሪ አቤል ዋበላ፣ጦማሪ አጥናፍ ብርሃኔ እና ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ከቅሊንጦ እስር ቤት ተለቀው ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቻቸው የተቀላቀሉ ሲሆን በአንዱ ክስ ይከላከል ተብሎ ዛሬም እስር ቤት የቀረውን ጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉ እንዲፈታ ጠየቁ።

ጦማሪአኑ ከእስር በሁዋላ በጋራ በፍቃዱ ይፈታ የሚል ጥአቄያቸውን ይዘው ፎቶ ተነስተዋል። የትላንቱን ውሳኔ ተከትሎ የጦማሪአኑ መግለጫ በገጻቸው የወጣ ሲሆን ትግሉ በፍቃዱ እስኪፈታ ይቀጥላል ስለሚያገባን እንጦምራለን ማለታቸው ይታወሳል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *