Hiber Radio ፡የኢትዮጵያው አገዛዝ ሶማሊያ ውስጥ የሚዋጋው በአሜሪካ ግፊት መሆኑን ወታደራዊ ሰነድ አጋለጠ፣በሚኒሶታ ለአርበኞች ግንቦት ሰባት የጀመረውን ትግል ለማጠናከር አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን 78 ሺህ ዶላር አዋጡ፣ በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ኢኮኖሚው ውድቀት ላይ መሆኑን አመነ ፣በቀይ ሽብር ጊዜ ፈጽመዋል በተባለው ወንጀል ተጠርጥረው በኔዘርላንድ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያዊ በአገር ቤት ሞት ተፈርዶባቸዋል ፣ የድምጻዊ አብዱ ኪያር አዲሱ <<አልተነጣጠልንም >> ዜማ በአገዛዙ ሚዲያዎች እንዳይደመጥ ታገደአምንስቲ ኢንተርናሽናል የዞን 9 ጦማሪያን አስቀድሞም መታሰር እንዳልነበረባቸው ገለጸ፣ የቦስትዋና ፍርድ ቤት ለከዱት ኤርትራውያን አስር የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዎቾች ጥገኝነት ሰጠ እና ሌሎችም አሉን

Hiber_radio_cover_101815_02

የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 7 ቀን 2008 ፕሮግራም

<… የወያኔ መሪዎች በዘር ማጥፋት ወንጀል መዘፈቃቸውን የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በየጊዜው የሚያወጣውን ማስረጃ ማየት ነው። ይሄን ረስተው በአሜሪካ ፍርድ ቤት የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪዎችን እንከሳለን የሚሉት ፍርድ ቤቱን እነሱ እንደሚቆጣጠሩት አለመሆኑን ካለማወቅ ነው ።ሌላው ቀርቶ ፕሬዝዳንቱ ፍርድ ቤት የማዘዝ ስልጣን እንደሌለው አያውቁም…እኛ እነሱ በሐውዜን ያደረጉትን ድራማ አንሰራም ነገር ግን… > አቶ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የውጭ ግንኙነት ሀላፊ በሚኒሶት በተደረገው የግንባሩ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለተጠየቁት ከሰጡት ምላሽ(ቀሪውን ያዳምጡት)

<…በኢትዮጵያ ብሔራዊ ዕርቅ የሚያስፈልገው ወያኔ እርስ በእርሱ ሊያጣላው ሲያቃቅረው በቆየው ሕዝብ መካከል እንጂ ከዚህ ሁኔታዎች እየገፉ የመጨረሻ ደረጃ ላኢ ካለ ስርዓት ጋር አይደለም ። መነጋገር መወያየት ያስፈልጋል። አንዱ አንዱን ማነጋገር አለበት…የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ነጻ ናቸው ከአንዱ በስተቀር የቀሩት ተፈተዋል። የታሰሩለት ዓላማ አልተፈታም አንዳንድ ሰዎች የታሰሩት ተፈቱ ሲሉ እነሱ የሚፈልጉት ትኩረታችን እዚያ ላይ እንዲሆን ነው። መሰረታዊው ጥያቄው እስካልተመለሰ ግን…>

አቶ ኦባንግ ሜቶ የትብብር ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጡት አስተያየት (ሙሉውን ያዳምጡት)

እስራኤልና ፍልስጤምን ሰሞኑን ደም ያቃባው የጎዳና ላይ ግጭት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስጋት እና ቁጣ ሲዳሰስ (ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የኢትዮጵያው አገዛዝ ሶማሊያ ውስጥ የሚዋጋው በአሜሪካ ግፊት መሆኑን ወታደራዊ ሰነድ አጋለጠ

በሚኒሶታ ለአርበኞች ግንቦት ሰባት የጀመረውን ትግል ለማጠናከር አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን 78 ሺህ ዶላር አዋጡ

በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ኢኮኖሚው ውድቀት ላይ መሆኑን አመነ

የውጪ ምንዛሪ ዕጥረት አጋጥሞታል

በቀይ ሽብር ጊዜ ፈጽመዋል በተባለው ወንጀል ተጠርጥረው በኔዘርላንድ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያዊ በአገር ቤት ሞት ተፈርዶባቸዋል

አምንስቲ ኢንተርናሽናል የዞን 9 ጦማሪያን አስቀድሞም መታሰር እንዳልነበረባቸው ገለጸ

የድምጻዊ አብዱ ኪያር አዲሱ <<አልተነጣጠልንም >> ዜማ በአገዛዙ ሚዲያዎች እንዳይደመጥ ታገደ

የቦስትዋና ከፍተኛ /ርድ ቤት ለአስር ኤርትራውያን እግር ኳስ ተጫዋቾች የፖለቲካ ጥገኝነት ሰጠ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-101815-102515

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *