የመጨረሻው የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ከትንሹ እስር ቤት ትልቁን በ20 ሺህ ብር ዋስ ተቀላቀለ

Befekadu-Hailu-05

ጥቅምት 5/2008 አራቱ የዞን ዘጠኝ አባላት በነፃ እንዲለቀቁ ሲወሰን፣ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 257/ሀ እንዲከላከል የተባለው በፍቃዱ ሀይሉ በ20 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቅ ተወሰነ፡፡ ጦማሪና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሀይሉ ጥቅምት 5/2008 ዓ.ም ለልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ጠይቆ በነበረው መሰረት ለዛሬ ጥቅምት 10/2008 ዓ.ም የዋስትናውን ጉዳይ ለማየት ቀጠሮ የሰጠው የልደታ ፍርድ ቤት በ20 ሺህ ብር ዋስ ወጥቶ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል ወስኗል፡፡በፍቃዱ ከቅሊንጦ ዞን9 ብለው እሱና ጓደኞቹ የሕዝቡን መታፈን ወዳሳዩበት ትልቁ እስር ቤት ተቀላቅሏል።

ጥቅምት 5/2008 ዓ.ም አራቱ የዞን ዘጠኝ አባላት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ በተወሰነበት ወቅት ክሱ ከሽብርተኝነት ወጥቶ በማስረጃነት የቀረቡበት ፅሁፎች አመፅ ቀስቃሽ ናቸው በሚል በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 257/ሀ እንዲከላከል የተወሰነበት በፍቃዱ ሀይሉ መከላከያ ምስክሮቹን እንዲያሰማ ለህዳር 27/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡

በአሁኑ ወቅት በፈጠራ ወንጀል 18 ዓመት የተፈረደበትን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ እነ ተመስገን ደሳለኝና ሌሎቹንም ጋዜጠኞች፣የተቃዋሚ መሪዎች ላይ የተላለፈውን ሕገ ወጥ ፍርድ ተሽሮ እንዲፈቱ የተጠናረከ ጥረት እንዲቀጥል በማህበራዊ ሚዲአው ጥያቄዎች ብቅ ማለት ጀምረዋል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *