የሶሪያው ፕ/ት ባሽር አላ አሳድ ለመጀመሪያ ጊዜ ንጹህ አየር ተቀብለው ተመልሱ-ቱርክ “ፕ/ት እሳድ አንደ ወጡ በዚያው በ ሞስኮ ቢቀሩ ምኞታችን ነበር” ትላለች

Asad_03

(በታምሩ ገዳ)

ላለፉት አራት አመታት በርሰ በርስ ጦርነት ከምትታመሰው አገራቸው ሶሪያ መወጣት ተሰኗቸው የነበሩት የሶሪያው ፕ/ት ባሽር እላ አሳድ ባልተጠበቀ ሁኔታ ማክሰኞ ምሽት ሩሲያ (ሞስኮ) ላይ መታየታቸው ፖለቲከኞችን ጉድ አሰኝተዋል።

በአንድ ወገን በአሜሪካ መንግስት በሚታገዙ ታጣቂዎች፣ በሌላ ወገን እራሳቸውን እስላማዊ መንግስት ብለው በሚጠሩ አክራሪዎች ዙሪያ ገባቸወን ከ2011 አኤአ ጀምሮ ጥቃት ሲሰንዘረባቸ የከርሙት አምባገነኑ ፕ/ት ኣላ አሳድ ካለፉት ሶስት ሳምንታት ጀምሮ በአየር ግዛታቸው ላይ ተዋጊ ጄቶቿን አሰማርታ አክራሪዎችን በማጥቃት ጊዜያዊ ፋታ እና እስትንፋስ የሰጣቻቸው ሩሲያን አና ባለሰሰልጣኖቿንን በግንባር ለማመሰገን ሞስኮ የተገኙ ሲሆን አሳድ”ሩሲያ በነፍስ ባትደርሰልን ኖሮ አልቆልን ነብር።” በማለት ለፕ/ት ፑቲን እና ለመንግስታቸው ያላቸወን ልዩ አክብሮት ገልጸዋል።

ኣላ አሳድን ወደ ሞስኮ ብቅ እንዲሉ የገበዟቸው ፑቲን በበኩላቸው “ወታደራዊ የበላይነት ለፖሊቲካዊ መፍትሔ መንገድ ጠራጊ ነው፣እኛ ወደ ሶሪያ የዘመትነው አክራሪዎችን ለመደምሰሰ እና ፕ/ት አሳድ አክራሪዎችን አንደያሸንፉ ለማደረግ ነው ፣ አሜሪካ ግን እቅዷ ፕ/ት አላ አሳድን ለማሰወገድ ብቻ ነው ።’በማለት ሞስኮ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከ 55 በላይ የአክራሪዎች ኢላማዎችን ዶግ አመድ ማደረጓን በመግለጽ ላለፈው አንድ አመት አየር ሃሎቻቸውን በሶሪያ ሰማያት ላይ አሰማርተው የረባ ውጤት ያላመጡት ምእራባዊያኖችን በተለይ የአሜሪካው ፕ/ት ባራክ ኦባማን ወርፈዋል። ፑቲን ሰለ አሳድ የሞስኮ እንግድነት በተመለከተ ለሰውዲ አረቢያው እና ለዮርዳኖሱ ንጉሶች ፣ለግብጽ እና ለቱርክ ፕሬዚዳንቶች በሰልክ አስረድተዋቸዋል ተብሏል።

የሁንና የቱርኩ ጠ/ሚ/ር አሃማት ዲቮቶጎሎ ሰለ ባላንጣቸው ፕ/ት አሳድ ደንገተኛው የሞስኮ ጉብኝት ሲናገሩ “ ለሶሪያ ሕዝብ ጸላቂ ሰላም ሲባል ፕ/ት አላ አሳድ እዚያው ሞስኮ ውስጥ ትንሽ ቢቆዩ ወይም ከ አነ አካቴው ቢቀሩ መልካም ነው ። ከዚያ በሁዋላ የሽግግር መንግስት ምስረታ ድርድር ይጀመራል ።” በማለት መኞታቸውን ገልጸዋል። 31% የቱርክ ሕዝብ ጸረ ኣሳድ አቁዋም ሲኖረው 51% ያህሉ የቱርክ ጣልቃ ገብነትን በጽኑ ይቃወማሉ ። የአሳድን መወገድ የምትሻው ጎረቤት ቱርክ የሶሪያን እለቂት ካቀጣጠሉት መካከል አንዷ መሆኑዋን ፕ/ት አሳድ አዘወትረው ይናገራሉ።

አንደ ቱርክ ሁሉ ጸረ ኣላ አሳድ አቋምዋን በአደባባይ የምትገልጸው አሜሪካም “በኬሚካል መርዝ ዜጎቻቸውን የፈጁት ፕ/ት ኣላ አሳድ ሞስኮ ላይ ቀይ ምንጣፍ ሲነጠፍላቸው ተመልክተናል።” በማለት ቅሪታዋን ገልጻ ለች። በርካታ ምእራባዊያን መዲያዎችም የ ፕ/ት እሳድን የሞስኮ ድንገተኛ ጉብኝትን በተለያየ መልኩ ዘግበውታል ።አሳድም በበኩላቸው ” እድሜ ለሞስኮ እና ለ ፕ/ት ፑቲን “ በማለት አንደ ቀድሞው የሊቢያ ፕ/ት ሙሃመድ ቃዛፊ እና የኢራቁ አቻቸው ሳዳም ሁሴን ከየተደበቁ በት ተይዘው አሳዛኝ እና አሸማቃቂ ከሆነው አሟሟታቸው ለጊዜው ተርፈው ፕ/ት ኣሳድ ከአራት አመት ወዲህ የመጀመሪያቸው የሆነወን ኦፊሴላዊ የባህር ማዶ ጉብኝት ሹልክ ብለው አጠናቀው ሹልክ ብለው ተመልሰዋል( ጉብኝቱን በተመለከተ ኣል አሳድ ደማሰቆ እሰከሚመለሱ ድረስ ሁሉም ነገር በምስጢር ነበር የተያዘው ) ተብሏል።

ከዛሬ ነገ ከበትረ ሰልጣናቸው ሊወገዱ ነው ሲባሉ በተቃራኒው ዙፋናቸውን አረጋገተው ከሞስኮው ክሬሚሊን ቤተ መንግስት የተገኙት አል አሳድ እና የከፉ ቀን ባለ ውለታቸው ፕ/ት ፑቲን ግንኙነት አንዳንድ የፖለቲካ ተቺዎች “ ማራባዊያኖችን አፍ ያስከፈተ የዲፕሎማሲዊ መፈንቅለ መንግስት ነው።” ብለውታል።ሩሲያ በሶሪያ ሰማያት ላይ የጦር አውሮፕላኖቿን ማሰማራቷን ከጅማሪው የተቃወመችው እና ወደ ጦርነት ልንገባ እንችል ይሆናል ብላ የዛተችው አሜሪካ ማክሰኞ እለት ከሩሲያ ጋር በሶሪያ ሰማያት ላይ ፓየለቶቻቸው “ላለመጋጨት”‘ የሚስችላቸው የ መግባቢያ ሰንድ መፈራረሟ/መሰማማቷ አንዳንድ ከፍተኛ የአገሪቱ ባለሰልጣናትን አስቆጡቷል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በምክር ቤቱ የመከላከያ ኮሚቴ ሰበሳቢ የሆኑት ሪፖብሊካኑ እና የአሪዞናው ግዛት ተወካይ ጆን ማኬይ ከዩኤስ ቱድይ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለመልልስ “ሰምምነቱ የኢራን አግረኛ ወታደሮች እና የሩሲያ ጄቶች በሶሪያ በሚገኙ አፍቃሪ አሜሪካ የሆኑ ታጣቂዎችን አንዲ ደመሰሱ መፍቀድ ያህል እና ለእነዚህ ወዳጆቻችን የገባነው ቃል ኪዳንን የማፍረስ ያህል ያሰቆጥራል ።” ሲሉ ሰምምነቱን ክፉኛ ተችተዋል።

አሜሪካ እና ሸሪኮቿ የሩሲያ ሰሞነኛው በሶሪያ ሰማያት ላይ ጥቃት 90% ኢላማውን “አልመታም” የሚል ስሞታ የሚያቀርቡ ሲሆን ሞስኮ በበኩሏ የምእራባዊያኑ ጥቃት ተጨማሪ አሸባሪዎችን ከመቀፍቀፍ ውጪ ባለፈው አንድ አመት በተጨባጭ ያስገኘው ነገር የለም በማለት መከራከሪያ ሃሳቧን ታሰማለች።በሶሪያው ግጭት ሳቢያ ከ ሰባት ሜሊዮን በላይ ሰላማዊ ዘጎች ተሰደዋል ፣ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይነገራል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *