ስለሴቶች መብት መከበር ፋና ወጊ የሆነው “ድፍረት” ሲኒማ ከአሜሪካ ሲኔማ ቤቶች ገባ

deferet_02

“  የኖቤል ተሸላሚዋ  ማላላ ወደ አደባባይ እንድወጣ አድርጋኛለች

የወሲብ ተጠቂዋ  አበራሽ በቀለ( አውሮፓ)

(በታምሩ ገዳ)

ከሁለት አስር አመት በፊት ትምህርት ቀሰማ ቤተሰቧን አና ማህበረሰቧን ለመረዳት ህልም የነበራት ፣ ነገር ግን ሕልሞቿ ሁሉ በጉልበተኞች  ሰለተ ጨናገፉባት  አንዲት ኢትዮጵያዊት  ልጃገረድ አበራሽ በቀለ ( የሲኒማዋ ሂሩት) ላይ ሰለ ደረሰ የጠለፋ  ጋብቻ ፣ወጣቷም   በጠላፊዋ ላይ ሰለ ወሰደችው እርምጃ፣ በወቅቱ ሰልነበረው የባህል የማሕበረሰብ አመለካከት  እና የህግ አግባብ  እና የወጣቷዋን  ሕይወት  ከሕግ  ክፈተተ  እና ከኋላቀር አሰተሳሰብ ሰለባነት  ለመታደግ  የተከፈለውን አስቸጋሪ  ውጣ  ውረድ እና ነጻነቷን እንዲት አንዳገኘች እና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ የሚያውጠነጥነው  እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘው  “ድፍረት” የተሰኘው ሲኒማ  ከኢትዮጵያዊያን ተመልካቾች አና ሲኒማ ቤቶች   አልፎ  ከአርብ  ጥቅምት 23 2015 አኤአ  ጀምሮ  በ አሜሪካ ሲኒማ ቤቶች (ኔዮርክ ላይ )መታየት ጀምሯል።  በቅርቡም በተለያዩ ከተሞችም የታያል ተብሎ ይጠበቃል።

 

እውቋ የ ሆሊውድ ሲኒማ ተዋኒት ፣ዳይሬክተር ፣ጸሀፊት  እና የስብእና አምባሳደር  አንጀሊና ጁሌ  አሻራዎች ያለበት ፣በኢትዮጵያዊው ደራሲ እና ዳይሬክተር እና  ተሸላሚው   ዘረሰናይ ብርሃኔ መሃሪ ተደረሶ ፣እነ ሜሮን ጌትነት ፣ሞገስ ዮሃንስ ፡ትዘታ ሃገሬ ፣ሽታዮ አብረሃ፣ ግርማ ተሾመ የመሳሰሉት  ሰመ ጥር አርቲስቶች የተካተቱበት    “ ድፈርት “ ሲኒማ 1 ሰእት ከ 39 ደቂቃዎች  የሚፈጅ ሲሆን ሲኒማውን  በተመለከተ በረካታ የምእራባዊያን ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን እየሰጡት ይገኛሉ።

የሲኒማው  ዋንኛ ባለ ታሪክ የሆነችው  አበራሽ  በቀለ  አኤአ  በ 1996 የደረሰባት  አስገድዶ  መጠልፍ ፣ጥጠላፊዋን በገዛ ጠምንጃው በመግደል ወንጀል   ለእስራት መዳረጉዋ ፣ የሲቶች የህግ ባለሙያዋች  ማህበር ሊቀመንበር መሰራች የሆኑት  ወ/ሮ መአዛ አሽናፊ  በግላቸው አና በደረጅታቸው ባደረጉት ጣልቃ ገብነት  የሞት ቅጣት  ይጠብቃት የነበርቸው  ወጣቷ አበራሽ  ከሁለት አመት  ውጣውረድ በሁዋላ  የግድያ   እርምጃውን የወሰደችው እራሷን ለመከላከል በሚል  ውሳኔ በነጻ  መሰናበቷ  አንዳንድ የወንድ የበላይነት አቀንቃኞችን  ያስቆጣ ቢሆንም  በተቃራኒው   ለወትሮው ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ህጻናትን ጠልፎ  ካገባ “አበጅህ” የሚያስብለውን በኢትዮጵያ ውስጥ  የቆየውን ኋላ  ቀር ጎጂ ባህል እና  የሕግ ክፍተትን  እንዲፈተሽ  እና በአሁኑ ወቅት  የድርጊቲ ፈጻሚዎች እሰከ 15 አመት   የሚደረስ እሰራት እንዲ በየንባቸው የሚያስችል  መንገድ ከፍቷል።

የሕግ ባለሙያዋ ወ/ሮ መአዛም  በበኩላቸው  በአንድ ወቅት ስለ አበራሽ ሲናገሩ”አበራሽ  በኢትዮጵያ ውስጥ በ አንዳንድ ሕገወጥ  ወንዶች የሚደርሰው ጾታዊ ትንኮሳን በመጋፈጥ እና ድል በማድረግ   የመጀመሪያዋ ሴት አብዮተኛ ነች ።”ሲሉ ለአበራሽ ያላቸውን ልዩ አክብሮት ገልጸዋል።   በኢትዮጵያ  የጋብቻ ሕግ መሰረት  አንድ ሴት ልጅ  ከ 18 አመት በፊት ማግባት እንደማይፈቀደላት የሚደነግግ ሲሆን  ችግሩ ሙሉ በሙሉ እንዳለተወገደ  መረጃዎች ይገልጻሉ ።ከ  2002 እስከ 2012 ባሉት ጊዜያት 16%ልጃገረዶች  እድሜያቸው  ከ 15 በታች ሳለ እንደሚያገቡ እና 40% ደግሞ 10 አመታቸውን ሳይጨርሱ ትዳር ይይዛሉ ተብሏል። በአሁኑ ወቅት  በደቡብ ኢትዮጵያ ከ6 ልጃገረዶች  መካከል አንዷ ሰትጠልፍ በ ሰሜን ኢትዮጵያ  ደግሞ ከ 20 ልጃገረዶች መካከል አንዷ  እነደምትጠለፍ ኦፊሴላዊ መረጃዎች ይገልጻሉ።

ከጠላፊዎቿ ቤተሰቦች  ብቀላ እንዳይ ደረሰባት በመሰጋት እና ከህግ በላይ ተሰሚነት እንዳለቸው በሚታመኑት የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች ግፊት ሳቢያ  አዲስ አበባ ውስጥ ለመደበቅ የተገደደችው  አበራሽ በሁዋላም ወደ ምእራብ አውሮፓ ( ደብሊን አይር ላንድ) ተሰዳ  ኑሮዋን እየገፋች ሲሆን  ስለ ደረስባት አሳዛኝ ገጠመኝ  በተመለከተ ለዜና ሮይተርስ በ ኢሜል በሰጠችው ምላሽ”ከዚህ ቀደም እራሴን ደብቄ  መኖርን መርጪ ነበር።አሁን ግን በዚህ ሲኒማ (ድፍረት)አማካኝነት እና  በፓኪስታናዊቷ  የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዋ  ማላላ ዮሳፊዝ  (እንዳትማር  ማእቀብ  የጣሉባት አክራሪ ታሊባኖችን  አሻፈረኝ በማለቷ በ2012 አኤ አ  የ 14 አመት ወጣት   ሳለች የግድያ ሙከራ የተደረገባት   እና በተአምር የዳነች ታዳጊ ነች)የእኔንም ብሶት ወደ አደባባይ ወጥቼ አንዳስተምር  አነቃቅቶኛል።” ብላለች። ሲኒማው “ደፈርት” ከከተማዎች አልፎ ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ቢዘልቅ   የብዙ ሴቶች ህይወትን ይታደጋል ፣ትልቅ  ሰኬት ኣንደሚሆን  ምኞቱዋንም ገልጻለች።  አበራሽ  ሪፋይነሪ 29 ለተባለው ደሀረገጽ በኣስተርጓሚ በሰጠችው አስተያየት “አንድ  ቀደም ሲል ያልተሞከረ ነገረን  መተግበር ቀላል አይደለም። ይሁን እና ያነን መጥፎ ገጠምኝን ወደአስተማሪነት   መልክ መለወጥ  መቻሉ አስደስቶኛል ።”ብላለች።   አበራሽ ሴቶች ለሴቶች (Women to Women) የተሰኘ  አገር በቀል ድርጅት  በማቋቋም ለወገኖቿ ለማገልገል ጥረት እያደረገች መሆኑዋን  አስታውቃለች።  በአማሪኛ  ቋንቋ (በደምጽ)  እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ  (በጽሁፍ የታጀበው) “ድፍረት”  ሲኒማ   በ ኢትዮጵያ  ውስጥ  በመታየት ላይ ሲሆን “ድፍረት”የሚለው ቃል በአማሪኛ ሁለት ትርጉሞች  ያለው ሲሆን አንደኛው የወሲባዊ ጥቃት ሰለባነትን ሲገልጽ  ሁለተኛው   ደግሞ ቆራጥነትን ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም ከ ኢትዮጵያ  አንዲት ሴት ልጅን (ዘሃራ) በጉድፊቻ መልክ በመውሰድ  ኢትዮጵያዊ  ቁርኝት የፈጠረችው ታዋቂዋ   የሰኒማ ባለሙያ አንጀሊና ጁሊ በበኩሏ “ሲኔማው  ለአኢትዮጵያ ኪነጥበብ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።ኢትዮጵያ የሚያኮራ ታሪክ  እንዳላት ሁሉ ከ ኢትዮጵያ ውጪ  የጾታ  መደፈር ለሚደረሰባቸው   ሴቶች የሚከፈሉት ቆራጣነትን  ያሳያል፣ ለሴቶች መብት መከበር  ተስፋ ይሰጣል ፣ያሰተምራልም።”ብላለች።

በዚህ ታላቅ እና አለማቀፍ እውቅና ባገኘው “ድፍረት” ሲኒማ ላይ እውነተኛ ባለታሪኳ የሆነችው አበርሽ  በቀለ ብትካተትበት ኖሮ ፊልሙን የበልጥ ተወዳጅ እና  ቀልብ ሳቢ እንደሚያደረገው  የሚተቹ የኪነጥበብ  ቤተሰቦች አልታጡም። የሲኒማው ዳይሬክተሩ  ዘረ  ሰናይ ብርሃኔ   አበርሽ በቀለን በመግኘት በሲኒማው ውስጥ ለማካተት የደረገው ተደጋጋሚ ሙከራዎች እንዳልተሳኩ እና በእርሷ ፋንታ “ሂሩት “የሚል ዋንኛ የገጸባህሪ ስም  ለመሰጠት መገደዱን ይናገራል። “ድፍረት” ሲኒማ በቅርቡ  በአሜሪካው ኦታዋ ግዛት በተደረገው  አመታዊ የሳንዳንስ ሲኒማ ፊስቲቫል እና በ ጀርመን (በሪሊን )የሲኒማ  ፊስቲቫል  ላይ ቀርቦ  ከ 200 በላይ የተለያዩ ሲኒማዎች በልጦ በመገኘቱ  ተሸልሟል

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *