የመን በጦርነት እየተለበለበች ዛሬም በርካታ ኢትዮጵያዊያን እየጎርፉባት ይገኛሉ

Ethiopia_yemen_05

በታምሩ ገዳ

(ህብር ሬዲዮ)ካለፈው የፈረንጆቹ መጋቢት ወር አንስቶ እንደ ሰደድ እሳት እየጠቀጣጠለ ያለው የየመኖች የእርሰ በርሰ ጦርነት እና የ ጎረቤት ሰወዲ አረቢያ የአየር ላይ ድበደባዎች ያሰከተለው የሰብአዊ ቀወስን ተከተሎ የመን ዜጎቿ አካባቢያቸውን ጥለው በሚሰደዱበት በአሁኑ ወቅት ብዛታቸው ቀላል የማይባሉ ኢትዮጵያዊያኖች ባህር እና የብሰ በሟቆራረጥ ወደ የመን እየተሰደዱ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት አስታውቀ።

የአለማቀፉ የሰደቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ( UNHCR) በትላንትናው እለት ጥቅምት 28 2015 ባወጣው መግለጫው በየመን የተቀሰቀሰው የአማጸያኑ የሁቴ ሸማቂዎች እና በ ፕ/ት አብዲ ሩቦ ማንሱር ሃዲ መንግስት ደጋፊዎች እና የ ስወዲ አረቢያ የአየር ላይ ተደጋጋሚ ደብደባዎች የመንን ወደ ድንጋይ ቁልልነት ሲለውጧት ብዛታቸው ከ 70 ሺህ በላይ የሚገመቱ ተሰፋ የቆረጡ የኢትዮጵያ እና የ ሶማሊያ ሰደተኞች ወደ የመን ጎርፈዋል ብሏል። የተቋሙ ቃለ አቀባይ የሆኑት አደሪያን ኢደዋርድ ለዜና ሰዎች በሰጡት አስተያየት በጦርነት እሳት እየተለበለበች ያለችው የመን በ አሁኑ ወቅት ብዛታቸው ከ 260 ሺህ በላይ ሰደተኞች በጉያዋ ይዛለች ብለዋል። እንደ እኚሁ ባለሰልጣን ገለጻ ከሆነ “በአሁኑ ወቅት ወደ የመን የሚደረገው ጉዞ በተለይ የባሕር ላይ ጉዞ አይመከረም። በዚህ አመት ውስጥ ከ86 በላይ ሰደተኞች ወደ የመን በሚያደረጉት ጉዞ ላይ ከ የመን የብስ ሳይደርሱ ሕይወታቸውን ባሕር ላይ አጥተዋል። በቅርቡ ከ ሶስት ሳምንት በፊት እንኳን 65 ስደተኞችን ከ አፍሪካ ቀንድ አካባቢ የጫነች ጀልባ ተገልብጣ 35 ስዎች ባሕር ላይ ሰጥመዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሰደተኞቹ የመን እንኳን ቢደረሱ የ መሰረተ ልማቶች በጦርነቱ በመፈራረሳቸው እና የ ተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጽፈት ቤት ሰደተኞች ተቋም ሰራውን በመታወኩ ሰደተኞች የሚጠብቃቸው ችግሮች ቀላል አይደለም።” ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።

የመንግስታቱ የሰደተኞች ተቋም ማይፊር በሚባለው አካባቢ ባለው ቢሮው አማካኝነት ባሕር አቋርጠው ሕይወታቸውን አተርፈው የመን ለሚደረሱ አዳዲስ ሰደተኞች መጠነኛ የሆነ የመጠለያ፣ የምግብ እና የሕክምና አገልግሎት በመስጠት እርዳታ ቢያደረግም የአዳዲስ ሰደተኞች ቁጥር ባለፈው መሰከረም እና በጥቅምት ወር ብቻ በ10 ሺዎች በመቆጠሩ የሁኔታዎችን ውሰብሰብነት አባብሶታል ተብሏል። የመን በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የራሷ ዜጎች አገሪቱን ጥለው ወደ ጎረቤት አገሮች ወደ ጅቡቲ አለማቀፍ እውቅና ለተነፈገችው ሶማሊ ላንድ እና ፑንትላንድ ሲኮበልሉ ከኢትዮጵያ እና ከሶማሊያ የሚሰደዱ ሰደተኞች ቁጥር ባለፉት ጥቂት ወራት በ 50% ጨምሮ መገኘቱ እነዚህ አዳዲስ ሰደተኞች ስለ ወቅታዊው የየመን ቀወስ መረጃ የሌላቸው ይሆናሉ፣ ከአገራችን የባሰ/ያለተሻለ የለም አሊያም በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ተታለዋል የሚሉ ግምቶች አሉ።

የመንግስታቱ የሰደተኞች ኮሚሽንም በበኩሉ መነሻቸው እና አላማቸው ምንም ይሁን ምን አንዚህ ከለላ እና ተገን ያጡት ሰደተኛ ወገኖችን መታደግ የሁሉንም አካል ጥረት እና እርብርቦሽን ይጠይቃል ሲል ተማጽኗል። በየመን በኩል ወደ ተሻለ ሶሰተኛ አገር ለመሻገር እድሉን ያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ጨምሮ በርካታ ስደተኞች ከሰማይ የ ስወዲ አረቢያ ጄቶች በሚያዘንቡት ቦንቦች ፣ከምድር ደግሞ በ ሁቲ አማጺያን እና በአፍቃሪ ፕ/ት አብዲ ማንሱር ታጣቂዎች በሚደረጉ እለታዊ የጎዳና ላይ ግጭቶች መወጫው አንደ ጠፋባቸው እና ለአካላዊ እና ሰነልቦናዊ ችግሮች መጋለጣቸው ይነገራል። እነዚህ ተሰፋ የቆረጡ ሰደተኞችን በአንደ ወቅት ወደአገር ቤት ለመመለሰ ወይም ወደተሻለ ሰፈራ ለማዘዋወር በኢሕ አዲግ እና በአንዳንድ ወገኖች መካከል ተጀመሮ የነበረው የማራቶን ሮጫ “ፈጻሜው እና አሸናፊው ምን እና ማን እንደሆነ ሳይታወቅ በነበረ ቀርቷል” የሚሉ ወገኖች በርካታ ናቸው ።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *