Hiber Radio: ከፓሪሱ የአሸባሪዎች ጥቃት ማግስት በብቸኛው መስጊድ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ማሕበረሰቡን ክፉኛ አሳዘነ

canada_mosq_005

በታምሩ ገዳ

ባለፈው ቅዳሜ እለት በካናዳ ማእከላዊ ኦንታሪዮ ግዛት (ፔተርቦሮው) በተባለች ከተማ ውስጥ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ብቸኛ የአምልኮት ስፍራ(መስጊድ) በጥላቻ ስሜት በተነሳሱ ወገኖች መቃጠሉ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ እና ቁጣ ፈጥሯል ተብሏል።

የአካባቢው የሙስሊሞች ማህበር ፕ/ት የሆኑት ኬንዙ አብደላ ለካናዳው ሲቢሲ ቴሊቭዥን እንደገለጹት ከሆነ የታዋቂው ማሲጅድ አልሰላም መሰጊድ በአገሬው የሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 11 ሰእት (በኢትዮጵያ ከምሽቱ 5 ሰእት ) አካባቢ በእሳት ከመጋየቱ ከአንድ ሰአት በፊት በውስጡ በርካታ ምእመናኖች የአንድ ሕጻን ልጅ መወለድን በማሰመልከት ተሰባሰበው ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ነበሩ። “ ሃዘናችን እና ጭነቀታቸን ይሆን የነበረው በመሰጊዱ ላይ እሳቱ ሲለኮስ በውስጡ ሰዎች ቢኖሩ ምን ይከሰት ነበር? የሚለውን መለስ ብለን ስናስበው ነው ።ይህ ሁኔታ በማህበረሰባችን ውስጥ ትልቅ አለመረጋጋት ፈጥሮብናል” ብለዋል። ተወካዩ በማያያዝ እምነታቸውን እና ባህላቸውን ጠብቀው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር መዋሃድ የጀመሩት የፒተርቦሮው ከተማ የሙስሊም እምነት ተከታዮች በደረሰባቸው የእሳት ቃጠሎ ክፉኛመደናገጣቸውን እና ማዘናቸውን አልሸሸጉም።

በካናዳ የሙስሊሞች ካውንስል በበኩሉ ባወጣው መግለጫው” በሰው ህይወት ላይ አደጋ ባለመደረሱ እፎይ ብለናል፡ ይህ አይነቱ የጥላቻ ጥቃት የአብዛኛው የአካባቢው ማህበረሰብ ስሜትን የማይወክል መሆኑን እናምናለን ።በደረሰብን የጥላቻ ጥቃት የእካባቢው የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች እና ፖለቲከኞች ከጎናችን በመቆማቸው በዚህ አጋጣሚ ማመሰገን እንወዳለን” በሏል። ካውንስሉ ወደፊት ተመሳሳይ ጥቃቶች ኣንዳይፈጸሙ ሕዝቡ ነቅቶ እንዲጠብቅ ጥሪም አቅርቧል።

ባለፈው አርብ እለት ፓሪስ(ፈረንሳይ) ላይ አሸባሪዎች ከ130 በላይ ሰላማዊ ዜጎችን ገድለው ከ200 በላይ ማቁሰላቸውን ተከትሎ በአንዳንድ የአለማችን ክፍሎች የሚገኙ በሰሜት እና በቁጣ የተሞሉ ወገኖች ለብቀላ ዘመቻ ይነሳሱ ይሆናል የሚል ፍራቻ የነበረ ሲሆን ሁኔታው በተቃራኒው ሆኖ በካናዳው መሰጊድ ቃጠሎ ላይ በርካት የአካባቢው የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ ነዋሪዎች ሰኞ እለት ከ50ሺህ ዶላር በላይ ለሙስሊም ወገኖቻቸው እርዳታ ማሰባሰባቸውን የተመለከቱት ኬንዙ አብደላ” መሰጊዳችን በደረሰበት ቃጠሎ ክፉኛ በመጎዳቱ የተነሳ ለጊዜው ተሰባሰበን የምናመልክበት ቦታ ባይኖረንም የአብዛኛው ነዋሪ ሕዝብ ለእኛ ያለው አመለካከት ቀና እና አውንታዊ መሆኑን በመመልከታችን በጣም ተደሰተናል”ሲሉ ተናግረዋል ።

የከተማው ከንቲባ ዳርያል ቤነሊቴ በበኩላቸው “የመስጊዱ ስያሜ በራሱ ማሲጅድ አል ሰላም (የሰላም መሰጊድ )የሚል መሆኑ እየታወቀ በአምልኮት ሰፍራ(መስጊድ) ላይ የተፈጸመ ጥቃት በፍጹም ተቀባይነት የለውም። ሁሉም ነዋሪ ከሙስሊም ወገኖች ጎን በመቆም በእሳት ለወደመው መስጊድ መገንቢያ ገንዘብ መርዳት አለብን “ሲሉ ድርጊቱን በጽኑ አወግዘዋል ለህዝቡም ጥሪ አቅርበዋል ። የክልሉ ፖሊስ በበኩሉ የእሳት ቃጠሎው ሆነ ተብሎ(በጥላቻ ስሜት ) የተፈጸመ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ዝርዘር ማብራሪያ ለመሰጠት ጊዜ ይጠይቃል ብሏል። በአፍጋኒስታን ውስጥ ተወልደው ፔተርቦሮው ክልል የመጀመሪያዋ ስደተኛ የሊብራል ፓርቲ የሕዝብ ኣንደራሲ የሆኑት ካዋርታ ማሪያም ሞንሰፍ “እኔንም ጨምሮ በርካታ የማህበረሰባችን ክፍሎች በተቃታብን ጥቃት ብንበሳጭም እንደዚህ አይነቱ የጥላቻ ጥቃት ሁሉንም ማህበረሰብን የማይወክል መሆኑን በጋራ በተግባር ማሳየት አልብን “ሲሉ በመግለጫቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 እና በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *