Hiber Radio: ሐበሻዊቷ የአካል ጉዳተኛ የመጀመሪያዋ የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ በመሆን ልዩ አደናቆት ተቸራት“የአካል ጉዳተኞች ችግሮቻቸውን የሚያሸንፉት በተአምር ሳይሆን ጠንክሮ በመሰራት ብቻ ነው”ጠበቃ ሃቤን ግርማ

harevared_003

በታምሩ ገዳ

ሃቤን ግርማ የዛሬ 27 አመታት ወደዚህ አለም ስትመጣ ከመደበኛ አምስቱ የስሜት ህዋስቶቿ መካከል ሁለቱን (የማድመጥ እና የማየት)ችግሮች ነበሩባት ።የመጥፎው አጋጣሚ የሆነው ደግሞ በቤተሰባቸው ውስጥ እንደ እርሷ ሁሉ ታላቅ ወንድሟም ተመሳሳይ እክል (የማየት እና የመሰማት ችግር) የነበረበት ሲሆን በጊዜው በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ይህ አይነቱ ችግር የተፈጥሮ ችግር ሳይሆን እርግማን እንዳለባቸው ተደረገው የመገለል ሰለባ ሆነው እንደነበር የሴት አያቷ ይናገራሉ። ይሁን እና ወላጆቿ ከኤርትራ ወደ አሜሪካ መሰደዳቸውን ተከትለው በካሊፎርኒኣ ግዛት ሲሰፈሩ በአሜሪካ ወስጥ የተወለደችው ኤርትራዊቷ እና አሜሪካዊቷ ሃቤን ቤተሰቦቿ የልጃቸው (የሃቤን) የወደፊት እጣ ፈንታ በእገር ቤት እንዳለው እብዛኛው የአካል ጉዳተኛ የጨለመ ይሆናል የሚል ሰጋት ነበራቸው። ይሁን እንጂ ሰጋታቸው ወደ መልካም ነገር ተለውጦ በአካለ ሰንኩላን ትምህርት ቤት የቀለም ትምህርት በትጋት የተከታተለችው ወጣቷ ሃቤን የተለያዩ ተጠፈጥሮአዊ ችግሮችን በመቋቋም ከመደበኛው የትርምህርት ቤት አልፋ የዛሬ ሁለት አመት (2013 አኤአ) በአለማችን እጅግ እና የተደነቀው የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በመዝለቅ በህግ ትምህርቷ ተመርቃ የአካል ጉዳተኛ መሆን ማለት የአለም ፈጻሜ አለመሆኑን በተግባር በማሰመሰከር በዩኒቨርስቲው ታሪክ የመጀመሪያይቷ የአለማችን የሴቶች ቁንጮ ለመሆን በቅታለች ። ማየት እና መሰማት የተሳናት ሃቤል በኮሌጅ ቆይታዋ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበ ረላትም። የምትፈልገውን የምግብ አይነት ዝርዝር አይነ ሰውር በመሆኗ ለማንበብ ባለመቻሏ ፣ የመሰማት ችግር ሰለ ነበረባት ከ አሰተናጋጆቹ ለመሰማት ባለመቻሏ በኤሊትሮኒክ መልእክት መስጫ(ኢ-ሜል )እንድትጠይቅ በ ካፍቴሪያው ስራ አስኪያጅ ቃል የተገባላት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ መልእክቱ ማየት የተሳናቸው ሰዎች በሚጠቀሙበት (ብሬል )ወረቀቷ ላይ ሳይጻፈላት እንደሚረሳ አሊያም ጭራሹንም ጆሮ ዳባ ልበሺ እንደተባለች የምታስታውሰው ሃቤል ትኩረት የመነፈጓን ሁኔታን አሜን ብላ አለተቀበለችውም ነበር። የአገሪቱ (የአሜሪካ የአካለ ጉዳተኞች መብት የሚያሰከብረው ህግ፣ መጣሱን በመገንዘብ ለምግብ ቤት ሃላፊዎቹ ቅሬታዋን በግላጭ በመናገሯ ችግሩ ወዲያውኑ ተወግዶ ከርሷም አልፎ ለሌሎች ወገኖች ህጉ በሰጣቸው ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ መንገድ ጠርጋላቸዋልች። በኮሌጅ ቆይታዋ ሰለራሷ አና ሰለሌሎች መብት መከበር ያ በወጣትነቷ የጀማመራት የመብት ተሟጋችነት ዝንባሌ በውስጧ ሰርጾ ወደ ታዋቂው የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በመዝለቅ በህግ ትምህርትም ለመመረቅ በቅታለች።በአሁኑ ወቅት በተማረችበት የህግ ትምህርት በካሊፎርኒያ ግዛት እንደ እርሷ ተመሳሳይ ችግር ላለባቸወ ወገኖች ጥብቅና በመቆም ሰለሰዎች የሰበዊ መብት መከብር በማገልገል ላይ ትገኛለች። ሃቤን ይሄ ቆራጥነቷ እና ይሄ አይበገሬነቷ ከማህበርሰቧ አልፎ የአሜሪካን ማህበረሰብም በማሰደነቁ በቅርቡ በፕ/ት ባራክ ኦባማ ቤተመንግስት ውስጥ በተዘጋጀው 25ኛው አመት የአካል ጉዳተኞች ህግ የተደነገገበት ክብረ በአል (The 25th anniversary of the Americans with Disabilities Act, ADA )ላይ የክብር እንግዳ ተናጋሪ በመሆን ታሪኳን ለአለም ሕዝብ ”የ አካል ጉዳተኞች ችግሮቻቸውን የሚያሸንፉት በተአምር ሳይሆን በተሰጣቸው እድል እና ጠንከረው ሲሰሩ ብቻ ነው። “ በማለት ያሳለፈቸውን የሕይወት ውጣውረድ እና የትጋት ፍሪዋንም በእማኝነት ለፕ/ት ኦባማ ጨምሮ ለበርካታ ታላላቅ ታዳሚዎችቿ ገልጻለች። የዋይት ሃውስም አሮብ እለት ባወጣው መግለጫው ሃቤን እንቅፋቶች ሳይበግሯት ስላደረገቻቸው ተጋድሎዎች አና በትምህርት ገበታዋም ማየት እና መስማት የተሳናት የመጀመሪያዋ የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ተመራቂ በመሆኗ ለሲኬታማነቷ አድናቆቱን ገልጾላታል።በነጩ ቤተ መንግስት(ዋይት ሃውስ) ቆይታዋም ፕ/ት ኦባማን በአካል ለማግኘት አድሉን ከማግኘት አልፋ ዘውተር ለሰራዋ እና ለመገባቢያነት የምትጠቀምበትን ልዮ እና ዘመናዊ የሆነው ዲጂታል የጽህፈት መሳሪያዋ(ብሬይል ) አማካኝነት ፊደላትን በመትየብ ለመግባባት የሞከሩ ሲሆን ፕ/ት ኦባማም “ማቀፍ የሚለወን ቃል መጻፍ ተሰኖኛል” (I could’t type a hug )በማለት በአለማችን የመጀመሪያዋ ማየት እና መሰማት የተሳናት የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሕግ ምሩቅ ፣ወጣቷ እና አይምሮ ብሩሁዋ ሃቤን ግርማን በማቀፍ ልዩ አክብሮታቸውን ገልጸውላታል። የ እንግሊዙ የዜና ማሰራጫ(ቢቢሲ) በበኩሉ ሃቤን ከነበራት ፈታኛ የተፈጥሮ ችግሮች ተላቃ እና ሰው ሰራሽ መሰናክሎችን በማለፍ በራሷ ጥረት ለዚህ ታላቅ ደረጃ በመደርሷ የአገራቸውን እና የአፍሪካን ስም ካስጠሩ ከ8 የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ እንስቶች መካከል አንዷ ነች ሲል መረጧታል።

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣ ብሎ በሰበታ አካባቢ የሚገኘው እና እ አኤ አ በ 1963 የተቋቋመው አንጋፋው የሰበታ ማየት የተሳናቸው ዜጎች አዳሪ ት/ቤት በቢሮክራሲው እና በባጀት እጦት ምክንያት ሊዘጋ ነው፣ ተማሪዎቹም ሊበተኑ ነው የመባሉ ወፍ በረር ወሬን በቅርቡ የሰማሁ መሰሎኛል። ዜናው እውነታነት ካለው ደግሞ ዚጎችን በአኣካላዊ ችግሮች ሳቢያ ምን ያህል አፈንጫችን ስር(አ/አ ጥግ )እንደምናገላቸው ያመላክታል ማለት ይቻላል ። የአካል ጉዳተኞችን ማግለል ሳይሆን ማቅረብ እና መንከባከብ ምን ያህል ለ ዜጋው ፣ለወገን እና ለአገር እንደሚጠቅም የእህታችን የሃቤን ግርማ አጭር የችግር እና የስኬት ጉዞ ከበቂ በላይ እሰተማሪ ነት ሳይኖረው አይቀረም።በኢትዮጵያ ውስጥ የአካል ጉዳተኞች ቁጥር ከአጠቃላዩ ማህበረስብ ጋር ሲነጻጸር ከ2.95% እንደማይበልጥ እና እነዚህ ወገኖቻችንም በአንዳንድ የማሕበረሰብ ክፍሎች የማገለል ጥቃት እንደሚደረሰባቸው ቀደም ያሉ የሰነ ሕዝብ ጥናቶች ይገልጻሉ

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 እና በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *