Hiber Radio: የሱዳን ዲፕሎማት አወዛጋቢው መሬት ቀድሞም የኢትዮጵያ ሳይሆን እኛ የሰጠናችሁ ነው ሲሉ ተናገሩ ፣የአማራ ክልል ባለስልጣናት ታጣቂዎችን እያደራጁ አስወጉን ሲሉ አወገዙ፣ የአባይ ወንዝን በተናጠል መገንባት እና መጠቀም ጦር ሊያማዝዝ ይችላል ተባለ፣በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅና ረሃብ አገሪቱንና ሕዝቧን እየተፈታተነ መሆኑ ተነገረ፣የጋሞ ብሄርን የሚያንቋሽሽ መጽሐፍ መውጣቱን ከተቃወሙ ውስጥ ዋና ዋና አስተባባሪ የተባሉት 69 ሰዎች በግንቦት ሰባት ስም ተወንጅለው መታሰራቸው ተገለጸ፣የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አውሮፓ ፓርላማ ድርቁን አስመልክቶ ለንግግር መጋበዝ ምዕራባውያን ለሚደረገው የትጥቅ ትግል ያላቸውን ድጋፍ ያሳያል ተባለ ፣ በአገር ቤት በበጎ ፈቃደኞች በረሃቡ የተጎዱትን ለማገዝ የተቋቋመው <ቤዛ እንሁን> ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፣በመምህር ግርማ ጉዳይ ወቅታዊ ዘገባና ሌሎችም አሉን

habtamu4

የህብር ሬዲዮ ህዳር 19 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…በረሃቡ ሳቢያ ለተጎዳው ወገን ቅድሚያ መድረስ አለብን ገና ለገና መንግስት ገንዘብ ይበላል ተብሎ ሰው ለቤተሰቡ ሳይልክ አይቀርም ።ለነዚህ ወገኖቻችንም በአፋጣኝ መድረስ አለብን።ለተራበ ሰው ችግሩን ማን እንደፈጠረው ከምትነግረው መጀመሪያ ምግብ የሚያገኝበትን ሁኔታ ማድረግ ቀጥሎ ችግሩን ማን ፈጠረው በሚለው ላይ ተወያይቶ የፖለቲካ አቋም መውሰድና ያን ለመለወጥ መታገል ይቻላልለተጎዱት ለተራቡት በተለይ ለእናቶችና ህጻናት ከዚሁ ከአገር ውስጥ አልሚ ምግብ ገዝተን ከቀይ መስቀል ጋር አካባቢው ድረስ ሄደን ለመስጠት እቅድ አለን…>

ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ <<ቤዛ እንሁን ለወገን>> ለረሃቡ የተጎዱትን ለመደገፍ በአገር ቤት በበጎ ፈቃድ የተቋቋመው ኮሚቴ ቃል አቀባይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

በመምህር ግርማ ላይ የቀረበው አዲስ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል እና ከዚህ ቀደም የቀረቡት ውንጀላዎች ማስረጃ አልባ መሆን ጉዳዩን ወዴት አመራዋል( ልዩ ወቅታዊ ዘገባ)

<…ሃያ ሰባት ዓመት ቬጋስ ላይ ታክሲ ሳሽከረክር የሚያስከፋ ነገር ገጥሞኝ አያውቅም በእርግጥ አንድ ጊዜ አደጋ ደርሶብኝ ራሴን እስከመሳት ደርሼ በማግስቱ ነው የነቃሁት።አደጋ እንዴት እንደደረሰ ዛሬም ድረስ አላውቅም። የሚአስቀኝ ገጠመኝ ግን አለ…> አቶ ገዛኘኘኝ ተፈራ ሃያ ሰባት ዓመት በቬጋስ ታክሲ አሽከርክረው በጡረታ ላይ ካሉበት አነጋግረናቸዋል(ክፍል አንድን ያዳምጡ)

የሩሲያና የቱርክ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ወዴት ያመራል? (ልዩ ጥንቅር )

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የሱዳን ዲፕሎማት አወዛጋቢው መሬት ቀድሞም የኢትዮጵያ ሳይሆን እኛ የሰጠናችሁ ነው ሲሉ ተናገሩ

የአማራ ክልል ባለስልጣናት ታጣቂዎችን እያደራጁ አስወጉን ሲሉ አወገዙ

የአባይ ወንዝን በተናጠል መገንባት እና መጠቀም ጦር ሊያማዝዝ ይችላል ተባለ

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅና ረሃብ አገሪቱንና ሕዝቧን እየተፈታተነ መሆኑ ተነገረ

የጋሞ ብሄርን የሚያንቋሽሽ መጽሐፍ መውጣቱን ከተቃወሙ ውስጥ ዋና ዋና አስተባባሪ የተባሉት 69 ሰዎች በግንቦት ሰባት ስም ተወንጅለው መታሰራቸው ተገለጸ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር / ብርሃኑ ነጋ አውሮፓ ፓርላማ ድርቁን አስመልክቶ ለንግግር መጋበዝ ምዕራባውያን ለሚደረገው የትጥቅ ትግል ያላቸውን ድጋፍ ያሳያል ተባለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-112915-120615

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *