Hiber Radio: በሕዝባችን ላይ አንተኩስም ያሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ኮሎኔሎች ከሰራዊቱ ውስጥ መታሰር መጀመራቸው ተገለጸ፣ አንድ የካናዳ ኩባንያ ኢትዮጵያን እና ግብጽን በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሊሸመግል ነው ተባለ፣የሱዳኑ ፕ/ት አልባሽር ካይሮን እና አ/አበባን ለመዳኘት መሬት ይሰጠኝ ማለታቸው ተሰማ፣ በ ታላቁ አንዋር መሰጊድ የደረሰው የቦንብ አደጋ አነጋጋሪ ሆኗል፣ እንግሊዝ ዜጎቿ ወደ መርካቶ እና መሰል ስፍራዎች እንዳይሔዱ አሰጠነቀቀች፣የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ የው/ጉ/ሚ/ርን ለመጀመሪያ ጊዜ በግንባር አነጋገሩ፣ሳውዲ አረቢያ አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ወደግዛቷ ዳግም ለማስገባት ሕዘበ ውሳኔ ልታካሄድ ነው ፣የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ የአገዛዙን ዘረኛ እንቅስቃሴ በመቃወም በጎንደር ወታደራዊ ጥቃት ፈጸምኩ አለ፣ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግፍ ተቃውሞ አጋርነቱን ገለጸ፣ከመድረክና ከሌሎቹም ጋር ለመስራት ወሰነ፣ ቃለ መጠይቅ ከጃዋር መሐመድና ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር በወቅታዊ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና ትግሉ ወደ ብሄራዊ ተቃውሞ ስለሚያድግበት ሁኔታ ሌሎችም ወቅታዊ ዝግጅቶች አሉን

hiber_radio_cover_121315

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-121315-122015

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 3 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…የህወሃት አገዛዝ አንዱን ብሄር ከሌላው ጋር ለማጋጨት ባለፉት በተማሪዎች ተቃውሞዎች የሄደበት ሴራ ዛሬ ከሽፏል፣ተማሪዎቹ አስቀድመው ስትራቴጂ አውጥተዋል።ይሄ የተለመደ የማጋጨት ስልትን እንኳን ሰው እንስሳትም ነቅተውበታል…ተቃውሞው ብሄራዊ መልክ እንዲይዝ ብቻ ሳይሆን ለቀጣይም አስተማማኝ ሁኔታ የጋራ አመራር የሚኖርበትን እና ሕዝባዊው ተቃውሞ ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጣበትን ሁኔታ እየሰራን ነው…> ጃዋር መሐመድ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…የኦሮሞ ተማሪዎች የጀመሩት ተቃውሞን ሌላውም በዚህ ስርዓት እተሰቃየ ያለው ኢትዮጵያዊ ዘር ጎሳ ሳይለየው በሔይማኖት ሳይከፋፈል የጋራ ለውጥ ለማምጣት መቀላቀልና በአንድ ላይ መቆም አለበት።ይሄ ተቃውሞ የህወሃትን አገዛዝ ገፍትሮ ለመጣል እንደ ወርቃማ አጋጣሚ የሚቆጠር ነው። ይሄ ወርቃማ አጋጣሚ ባለመተባበር ሊያመልጠን አይገባም…የአንዋር መስጊዱ ጥቃት በህወሓት ደህነቶች የተቀነባበረ ለመሆኑ ሌላ ምስክር ሳያስፈልገን ከዚህ በፊት ራሳቸው በአዲስ አበባ ቦንብ አፈንድተው ንጹሃን ገለው አፈነዱ ማለታቸውን የአሜሪካ ዲፕሎማት የላኩት መረጃ በዊክሊክስ ተጋልጧል።የዛሬውም ቦንብ የኦሮሞ ተማሪዎችን ተቃውሞ ሙስሊሙም ይቀላቀላል ሌላውም ይከተላል ከሚል ፍርሃት ስርዓቱ የወሰደው የሽብር እርምጃ ነው።ተቃውሞው በዚህ…> ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሳዲቅ አህመድ(ስለ ወቅታዊው ተቃውሞ ለህብር ሬዲዮ ከጃዋር ጋር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)

<…በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ግፍ ኢትዮጵያውያን በሚኒሶታ በጋራ አንተ ኦሮሞ አንተ አማራ ሳይባባሉ የስርዓቱን ግፍ ተቃውመዋል። የህወሃት ሰዎች አስቀድመው በሰልፉ ላይ ኢትዮጵአ ናንዲራ እንዳታመጡ አሉበትን ሴራ ሰልፉን ከጠራው የኦሮሞ ኮሚኒቲ ያልወጣ በሰልፉ ላይም የኢትዮጵአም፣የኦነግንም ሆነ የኦጋዴን ባንዲራ የያዙ ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በጋራ ቆመው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል… >

የዘ-ሐበሻ ድህረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ በሚኒሶታ ስለተደረገው ሰልፍ ለህብር ከሰጠው ማብራሪአ(ሙሉውን አዳምጡት)

<…ሕወሃት 25 ዓመት ኦሮሞ አማራ እያለ የከፋፈለን አይበቃም? ግፍ እተሰራብን አንድ ላይ ቆመን ወያኔን በጋራ የማንቃወመው ለጸረ ወያኔ ትግል የማንተባበርበት ምክንያት የለም…መልዕክቴን በአፋን ኦሮሞ ሳስተላልፍ…> ቢላል ኦሮሞ በሚል ስያሜ በማህበራዊ ሚዲያ ፓል ቶክ የወያኔን ሴራ ለማክሸፍ እንቅስቃሴ የሚያደርገው አክቲቪስት ስለ ሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል የተነሳ ተቃውሞ እና በውጭ አገራት ስለሚነሱ ተቃውሞዎች ከሰጠን ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያድምጡት)

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ የተቃውሞ አመጽን ተከተሎ የተሰጠው አለማቀፋዊ ድጋፍ ሲዳሰስ (ልዩ ዘገባ)

ኦሮሞ ተማሪዎች ጀመሩት ሕዝባዊ ተቃውሞን ሁሉም እንዲቀላቀለው ቀረበው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ጥሪና ማስተንቀቂያ

በቬጋስ ታክሲ አሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን በማህበር ለማደራገት ስለ ተጠራ ስብሰባ ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያዳምጡት)

 

 

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በሕዝባችን ላይ አንተኩስም አሉ ኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ኮሎኔሎች ከሰራዊቱ ውስጥ መታሰር መጀመራቸው ተገለጸ

አንድ የካናዳ ኩባንያ ኢትዮጵያን እና ግብጽን በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሊሸመግል ነው ተባለ

የሱዳኑ / አልባሽር ካይሮን እና /አበባን ለመዳኘት መሬት ይሰጠኝ ማለታቸው ተሰማ

ታላቁ አንዋር መሰጊድ የደረሰው የቦንብ አደጋ አነጋጋሪ ሆኗል፣

እንግሊዝ ዜጎቿ ወደ መርካቶ እና መሰል ስፍራዎች እንዳይሔዱ አሰጠነቀቀች፣ ዘረኞች በአሜሪካው የካሊፎርኔያ ግዛት መስጊድ አቃጠሉ

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ

የው///ርን ለመጀመሪያ ጌዜ በግንባር አነጋገሩ፣የውይይቱንም ውጤት እና አቋማችውን ገልጸዋል

እንግሊዝ በአንዳርጋቸው ጉዳይ ቁርጥ ያለ ውሳኔ አሻለሁ ስትል ለኢትዮጵያ ባለሰላጣናት ጥያቈ አቀረበች

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ መሞት የለባቸውምአንግሊዛዊቷ የሕዝብ እንደራሴ

ሳውዲ አረቢያ አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ወደግዛቷ ዳግም ለማስገባት ሕዘበ ውሳኔ ልታካሄድ ነው

የሪያድ ነዋሪዎች ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞች በጸባያቸው ምቹዎች ናቸው ሲሉ አደናቆታቸውን መስጠታቸ ታውቋል

የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ የአገዛዙን ዘረኛ እንቅስቃሴ በመቃወም በጎንደር ወታደራዊ ጥቃት ፈጸምኩ አለ

ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግፍ ተቃውሞ አጋርነቱን ገለጸ

ከመድረክና ከሌሎቹም ጋር ለመስራት ወሰነ

 

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *