Hiber radio: የ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሴት ልጅ የአንግሊዟ ንግስት አባቷን እንዲያስፈቱላት ተማጸነች፣“ቤታችን አባት አልባ በመሆኑ ይህንን ደብዳቤ ለእርሶ ለመጻፍ ተገድጃለሁ”የ8 አመቷ ምናቤ አንዳርጋቸው

andy_with_kids_queen_elisabeth_01

በታምሩ ገዳ

ከ አንድ አመት ተኩል በፊት በዱባይ በኩል ወደ ኤርትራ ለትጥቅ ትግል ሲጓዙ የመን ሰነኣ ላይ ትራንዚት ሲያረጉ በ የመን የደህንነት ሰራተኞች ታፍነው ለ ወቅቱ የኢትዮጵያ ገዢዎች ተላለፈው የተሰጡት የግንቦት 7ቱ ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳረጋቸው ጽጌ 3 ልጆች መካከል አንዷ የሆነችው የ8 አምቷ ምናቤ አንዳርጋቸው በ አሁኑ ወቅት በ እስራት ላይ ካለ ዘመድ ጥየቃ፣ ካለ የህግ አማካሪ በየሃይማኖት አባት ያለመጎብኘት የመሳሰሉት በቂ እድል ተነፍገው የሚገኙት ወላጅ አባቷ ከእስራት ይፈቱላት የአንግሊዟ ንግስት አሊሳቢጥን በደብዳቤ መማጸኗ ታውቋል። በዝ ፊድ የተባለው ድህረገጽ በትላንትናው እለት አንደዘገበው ከሆነ የአቶ አንዳርጋቸው ልጆች ቀደም ሲል ለእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር ደቪድ ካሜሮን የተማጽኖ ደብዳቤ ቢልኩም የጠ/ሚ/ሩ ሚና ብዙም ያላረካቸው ሲሆን ከአቶ አንዳርጋቸው ልጆች መካከል አንዷ የሆነችው ምናቤ የጻፈችው ደብዳቤ በከፊል “የተከበሩ ንግስት ኢልሳቤጥ ምናቤ አንዳርጋቸው እባላለሁ። የ 8 አመት ታዳጊ ሰሆን ( ስሙ ባልተጠቀሰ ት/ቤት )ተማሪ ነኝ።ወላጅ አባቴ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ ሲሆን ይህንን ደብዳቤ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የምጽፍሎት ወላጅ አባቴን ከቤተሰባችን ጋር እንዲቀላቀል እንደሚረዱን ተሰፋ በማድረግ ነው።ባለፈው አመት እኔ ፣ወንድሜ እና እህቴ ለጠ/ሚ/ር ዴቪድ ካሜሮን የተማጽኖ ደብዳቤ ጽፈን ነበር፣ ይሁን እና ከጠ/ሚ/ሩ በቂ ምላሽ አላገኘንም ፣ አልረካንባቸውም።ከዚህም በተጨማሪ በቤታችን ውስጥ አባት አልባ በመሆናችን ምኞታችንን(የአባታቸው መፈታት) ያሳኩልናል በሚል ተሰፋ በመታጀብ ይህንን የተማጸኖ ደበዳቤን ለመጻፍ ተገደጃለሁ ።ጠ/ሚ/ር ካሜሮን የተቀበሉት ሃላፊነት ውጤት አልባ ሆኖ ሰላገኘሁት እርሶን በአጽንዎት እንዲጠይቁልን /ጣልቃ እንዲገቡ/እለምናለሁ። እህቴ ሰለ አባታችን መፈታት ባደረገቸው ተጋድሎ የሰብ አዊ መብት ተሟጋቹ ሊቤሪቲ ተሸላሚ ሆናለች ፣ጠ/ሚ/ር ዴቪድ ካሜሮን ግን በአባታችን ጉዳይ አንዳችም አልፈየዱም።” ተጻፈ ከ ታዳጊ ህጻን መናቤ አንዳርጋቸው ። የእንግሊዟ ንግስት ኢልሳቢጥ በአገሪቱ ሕግ መሰረት በፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ጣልቃ ገብነት ወሳኝ ባይሆነም ተጽእኖ ማሳደር እና የሚጫውቱት ትላቅ ሚና ግን ቀላል ያለመሆኑን በረካታ ተንታኞች ይናገራሉ። የደብዳቤ ነገር ከተሰንሳ ዘንድ በቀርቡ የሰራ ጊዜያቸውን የጨረሱት በኢትዮጵያ የታላቋ ብሪታኒያ አምባሳደር የነበሩት ግሪግ ዶርይ አቶ አንዳርጋቸውን በእስር ቤት በግንባር ለማገኘት እድሉን ካገኙት ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ ሰለ አቶ አንዳርጋቸው ወቅታዊ ሁኔታ በቅርቡ በጻፉት የግል ማስታዎሻ “አንዳርጋቸው ጠበቃ የማግኘት እድል ተነፈገዋል፣ሰለሚቀርብባቸውም ክስ እሰከአሁን ድረስ የተባለ ነገር የለም።”ብለዋል አምባሳደሩ በዚህ ማሰታወሻቸው ላይ ከአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ከወ/ሮ የምስራች ሃይለማሪያም ለአቶ አንዳርጋቸው የተላከ የፍቅር እና የማጽናኛ ደብዳቤ ለእቶ አንዳርጋቸው ማደረሳቸውን አወስተዋል። ይህ በኣንዲህ ኣንዳለ ወ/ሮ የምስራች በባለቤታቸው ጉዳይ ከእንግሊዙ የወጭ ጉዳይ ፊሊፕ ሆላንዴ ጋር በባለቤታቸው ጉዳይ በቅርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ በግንባር ተገናኝተው ውይይት ማደረጋቸውን ዘውትር አሁድ ከምሽቱ 6 ፡30 pm ( በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 12:30)ከአሜሪካው ምድር ከላስቬጋስ ከተማ የሚተላለፈው ሕብር ራዲዮ ባለፈው እሁድ የዘገበ ሲሆን ራዲዮኑ የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች የሚኖሩበት የሰሜናዊው ሎንዶን እዝሊንግቶን ክፍለ ከተማ የሕዝብ ተወካይ የሆኑት ኢሚሊይ ቲቤሪይ ከ ወ/ሮ የምሰራች ጋር በመሆን የው/ጉ ሚ/ሩ ፊሊፕን ያነጋገሩ ሲሆን የሕዝብ እንደራሲዋ ለዜና ሰዎች በሰጡት አሰተያየት “አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ መሞት የለባቸውም፣ አንዳርጋቸው ተገቢውን ፍትህ ካላገኙ ዜግነት ወደ ሰጠቻቸው ሎንዶን እንዲመለሱ እንግሊዝ ተጽእኖ የመፈጠር ግዴታ አለባት”ሲሉ አሰጠንቅቀዋል ሲል ሕብር ራዲዮ ዘግቧል። የእንግሊዝ የውጪ ጉ/ሚ/ር በበኩሉ የ 60 አመቱ አቶ አንዳርጋቸው መቼ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ቁርጥ ያለ ቀን እንዲሰጠው ለኢትዮጵያ አቻው በቅርቡ ለ19 ኛ ጌዜ ደብዳቤ መላኩን አሰታውቋል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 እና በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *