Hiber radio: የኢትዮጵያው አገዛዝ በአወዛጋቢው በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስበት ስጋት እንዳለው የግብጽ ሚዲያዎች አጋለጡ ፣በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞው እንደገና ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፣በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ተሰቅሎ ተገኘ፣አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሽብር ጥቃቱን ቀጥሏልቀጥሏል፣የንጹሃን ሞት ጨምሯል፣የእርዳታ እህልና ዘይት በባለስልጣናት ተዘርፎ እየተሸጠ ነው፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚ/ር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገውን የሰው አልባ አውሮፕላኖች የጸረ ሽብር ዘመቻውን ማቋረጡን አስታወቀ፣ ከኢትዮጵያ የሄዱ የደህነት አባላት የኬኒያ ድንበርን ተሻግረው የአፈና እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ አድርሰዋል ስትል ናይሮቢ ወቀሳዋን አሰማች እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራና ከሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ አዘጋጅ፣ ከላይ የግድቡ ግንባታ፣ ዶ፣ር አክሎግ ቢራራ፣ከታች በረሃብ ችግር ላይ ሆኑ ወገኖች፣ተቃውሞውን ተከትሎ በቦንብ የተመታችው ህጻን ሀና እና የሰቀሉት ጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ አስከሬን የሚያሳይ
የህብር ሬዲዮ አዘጋጅ፣ ከላይ የግድቡ ግንባታ፣ ዶ፣ር አክሎግ ቢራራ፣ከታች በረሃብ ችግር ላይ ሆኑ ወገኖች፣ተቃውሞውን ተከትሎ በቦንብ የተመታችው ህጻን ሀና እና የሰቀሉት ጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ አስከሬን የሚያሳይ

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 24 ቀን 2008 ፕሮግራም

እንኳን ለአዲሱ ዓመትና ለኢትዮጵያውያን የገና ዋዜማ አደረሳችሁ!

<በረሀብ ሳቢያ ችግር ውስጥ ላለው ወገናችን መድረስ አለብን። ከሕዝቡ የሚዋጣውን ገንዘብ በቀጥታ የረሃብ አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖቻችን እንዲደርስ ገንዘቡን ሰብስበን ከምናስረክበው ወርልድ ቪዥን ጋር ተስማምተናል። የቀረው ሕዝቡ ተባብሮ ለወገኖቹ የራሱን አስተዋጽዎ ማድረግ ብቻ ነው። ይህ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵአውያን መብት በሳውዲ ዜጎቻችን የግፍ ሰለባ በሆኑ ጊዜ ተቋቁሞ በርካታ ጠቃሚ ስራዎችን ሰርቷልበአባይ ጉዳይ ላይ የሰሞኑ ፊርማ ብቻ ሳይሆን ባለፈው ማርች ላይ የተደረገው ስምምነት የኢትዮጵያን ጥቅም የማያስጠብቅ የራሷን መብት ለግብጽ አሳልፎ የሚሰጥ ትልቅ ብሄራዊ ክህደት ነው ብዬ ጽፌ ነበር ሰሞኑን ሱዳን ላይ ያደረጉት ያንን ኢትዮጵያን አሳሪ ስምምነት የሚያጸና የአባይ ግድብን ወደ ውሃ የሌለበት ህንጻ ወይም ጉድጓድ ብቻ አድርጎ የሚያስቀር አደገኛ ነው። ይሄን ነው አገዛዙ ጥቅም አስጠባቂ የሚለው?… > / አክሎግ ቢራራ የዓለም አቀፍ ለኢትዮጵያውያን(ግሎባል አሊያንስ) የውጭ ግንኙነት ሀላፊ እና የቀድሞ የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ አማካሪ በወቅታዊ ጉዳይ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት  ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ለማንኛውም ሰላማዊ ጥያቄ ወይ እስር ወይ ድብደባ እና ጥይት ነው ሁኔታው አደገኛ እየሆነ ነው። የሁሉም አገራት ዲፕሎማቶች እያነጋገሩን ነው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለው የሀይል እርምጃ አደገኛ ሁኔታ ሊያስከትል እንደሚችል ገብቷቸዋል። አንድ ከአሜሪካ ኤምባሲ የመጡ ዲፕሎማት መንግስት ለፕ/ ኦባማ የገባውን ቃል አልተገበረም ብለዋል። ሕዝቡም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ተስፋ የቆረጠበት ስርዓት ነውሕዝቡ አገሩን እንዲያስተዳድር ብሄራዊ መንግስት እንዲመሰርት በጥቅሉ ያቀረብነው ጥሪ ሆን ብለን ነው።አንድ ታርጌት ቡድን እየነጠልን ለከሌ ለከሌ ብንል የጥቃት ሰለባ ይሆናሉ እኛ ግን በቻልነው መጠን አፈናው በርትቶም ሁሉንም ወገኖች ያሳተፈ ነገር ለማድረግ በክተኛ ጫና በደህነት ክትትል ውስጥ በእነሱ አጃቢዎች ተከበን እየዋልን ሰብስበው እስኪያስሩንም ሆነ ማንኛውንም እርምጃ እስኪወስዱብን ሰላማዊ ትግላችንን ቀጥለናል… > የሰማያዊ ፓርቲ /ሊቀመንበር አቶ ለገሰ ተፈረደኝ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

 አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን <<የዓመቱ የአፍሪካ ታላቅ ሰው>> ብሎ የሰየማቸው አውሮፓ ላይ የተቀመጠው ናይጄሪያዊ ማንነትና ድህረ ገጹ ሲፈተሽ (ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የኢትዮጵያው አገዛዝ በአወዛጋቢው በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስበት ስጋት እንዳለው የግብጽ ሚዲያዎች አጋለጡ

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞው እንደገና ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው

በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ተሰቅሎ  ተገኘ

በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ በየቀኑ የንጹሃንን ሕይወት እየቀጠፈ ነው

የእርዳታ እህልና ዘይት በባለስልጣናት ተዘርፎ እየተሸጠ ነው

የአሜሪካ መከላከያ / በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገውን የሰው አልባ አውሮፕላኖች የጸረ ሽብር ዘመቻውን ማቋረጡን አስታወቀ

ከኢትዮጵያ የሄዱ የደህነት አባላት የኬኒያ ድንበርን ተሻግረው የአፈና እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ አድርሰዋል ስትል ናይሮቢ ወቀሳዋን አሰማች

የሰማያዊ ፓርቲ አባል የመግደል ሙከራ ተደረገባቸው

በመላው ዓለም የሚገኙ ኤርትራውያን የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው /ቤትን በመቃወም ወደ አደባባዮች ወጡ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-010316-011016

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *