የኢራኑ ታላቁ ሃይማኖታዊ መሪ የ ገና በአልን ከክርስቲያን ሰማእት ቤተሰቦች ጋር አሳለፉ

Iran_religious_leader_001

በታምሩ ገዳ

“ዛሬ አየሱስ ክርስቶስ በስጋ በምደር ላይ ቢኖር ኖሮ አልቂት፣ ሙሰኝነት እና ጥላቻ ባልነበሩ” ታላቁ አያቶላ ሰይድ ካህሚኒ

በ አሰላማዊ አብዮታዊ ሪፖብሊክ ኢራን ውስጥ ከፖለቲከኞቹ ይበልጥ ወሳኝ ቦታ እና ተሰሚነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ታላቁ ሃይማኖታዊው መሪ አያቶላ ሰይድ አሊ ካህሚኒ ልጃቸውን በ ኢራን እና በኢራቅ የድንበር ጦርነት ወቅት ላጡ እና እዚያው ኢራን ውስጥ በመኖር የጌታ የእየሱስ ክርስቶስ መወለድ ከበረበአልን ከሚያከብሩ ክርሲቲያን ቤተስቦች ዘንድ በመገኘት ባለፈው አርብ እለት የደስታቸው ተካፋይ መሆናቸው ታውቋል። አኤ አ ከ1980 -88 በኢራን እና በኢራቅ መካከል በተካሄደው ጦረነት ላይ 48 ክርስቲያኖች ለ አገራቸው ኢራን ሲሉ መሰዋትን የተቀበሉ ሲሆን 105 ቁሰለኞች 35 ደግሞ የጦር ሙርኮኞች ሆነዋል። ከሰማታቱ መካከል አንዱ የሆነው የሮበርት ላዛር ቤተሰቦችን በገና ክብረበአል ላይ በአካል ተገኝተው የታደሙት አያቶላህ ሰይድ አሊ ካህመኒ” አናሳዎቹ የአርመኒያ እና አሳሪያን ክርስቲያኖች ከ1978ቱ የኢራን አብዮት ጀምሮ ከኢራቅ ጋር ባደረግነው ጦርነት በታማኝነት፣በብልህነት እና በጀግንነት ኢራንን ከወራሪው ከሳዳም ሁሴን ጦር ታድገዋታል”በማለት ለክርስቲያን ወገኖች ያላቸውን ልዩ አክብሮት በራሳቸው ደሀረገጽ ላይ ገልጸዋል። አያቶላው ለክርስቲያኖች በተለይ ደግሞ የክርስትናን ስም መጠርያ ላገኙበት ለጌታ ለእየሱስ ክርስቶስ ልዩ አክብሮት ያላቸው ሲሆኑ በአንድ ወቅትም በወዳጆች መገናኛ ደህረ ገጻቸው(ፊስ ቡክ) ላይ “ ዛሬ እየሱስ ክርስቶስ በሰጋ ከእኛ ጋር ቢኖር ኖሮ የአለማችን አምባገነኖችን፣ ሙሰኞችን፣ ጨቋኞችን ለሰኮንድ ያህል ቸል አይላቸውም ነበር። እየሱስ ከርስቶስ ለተገፉ ሕዝቦች ስማያዊ ሚኒስተራቸው ነው። “ በማለት የዘመኑን ሰርአት አልበኝነት፣ እርዛትን እና ጭቆናን በተመለከት ያላቸውን ቅሬታ እና የአየሱስ ክርስቶስም ጠቀሜታውንም በተመለከተ ለሚያምኑበት ለክርስቲያኑ ማሕበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለሙስሊሙም ወገን ጭምር መሆኑን አሰረድተዋል።፡ በጉብኝታቸውም ወቅት ለሰማእታቱ ቤተሰቦች” ፈጣሪ የሰማእታቱን ነፍስ ይማር፣ለእናነተም የገና በአል እና መጪው አዲሱ አመት የሰላም፡የደስታ እና የጤንነት ይሁንላችሁ።” በማለት ምኞታቸውን ገልጸዋል። በነገራችን ላይ የአርመን ክርስቲያኖች እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፣የግብጽ ኦርቶዶክስ፣የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፣የ ሕንድ እና የሶሪያ ኦርቶዶክስ ተመሳሳይነት የክርስትና አምልኮተ ሰርአት ተከታዮች ናቸው። የክርስቲያኑ እና የሰማእቱ ሮበርት ወላጅ እናት በበኩላቸው በእውንም ይሁን በህልም ያለጠበቋቸው ታላቁ ጥቁር እንግዳ(አያቶላ ካህሚኒ) ከቤታቸው ተገኝተው የጌታ የእየሱስ መወልድ(የገና)በአልን አብረዋቸው ሻይ በመጠጣት፣ ኬክ በመብላት ፣ሰለቤተሰቡ ታሪክ በመጫዎት እና ስጦታ በመስጠትም በማሳለፋቸው ደስታቸውን በእምባ ነበር የገለጹት ትብሏል።”አያቶላው በጣም ተግባቢ እና ቀላል ሰው ናቸው። ከእርሳቸው ጋር ያደረግነው ቆይታ ለረዥም ሰአታት ቢሆን ኖሮ ደሰተኛ ነበርኩ ። ወደ ጎዳና ድረስ ሄጂ እንዳልሸኛቸው ጠባቂዎቻቸው ግርግር እና ትኩረት መጋበዝ በመሆኑ ከእቤቴ እንድሰናበታቸው አድርገውኛል። አያቶላው ሹልክ ብለው መጥተው አንደጎበኙን ሁሉ ሹልክ ብለው ነበር የሂዱት ” ብለዋል።

ኢራን ከጎርቤቷ ከ ኢራቅ ጋር ደም አፋሳሽ ፍልሚያ ውስጥ በነበረችበት እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወላጆች የሃዘን አንባ በነቡባቸው በ1980ዎቹ ወቅት አናሳዎቹ የአርመን ክርስቲያኖች የዘመን መለወጫ ክብረ በአላቸውን ላለማክበር በመወሰናቸው በተቀረው የኢራን ህዝብ በተለይ ደግሞ በታላቁ አያቶላ ፊት ትልቅ ስፍራ ለማግኘት በቅተዋል።አያቶላውም ከ 1984 እኤአ ጀምሮ የአርመን ክርስቲያኖችን በክበረበአላቸው ላይ በመገኘት የሃይማኖት ልዩነት የሰው ልጆችን አንደማይከፋፍላቸው በቅርበት እና በተግባር የማስተማሩን ተግባርን ከሃይማኖታዊ ስራዎቻቸው መካከል አንዱ አድርገውታል ተብሏል። በዙዎችም የማንኛውም ሃይማኖት ታላቅ መሪ እንዲህ አይነቱን መንገድ ቢከተል በአለማቸን ላይ የተንሰራፋው ጥላቻ አና እልቂት ቦታ ባልኖራቸው ነበር በማለት ሰሞኑን አደናቆታቸውን እየቸሯቸው ይገኛሉ። ኢራን በአሜሪካ እና በሸሪኮቿ እይታ “የሰይጣን ማህበርተኛ ( The axis of evil) ከሚባሉት ከ እነ ሰሜን ኮሪያ እና ከእነ ሶሪያ ተርታ ተፈረጃለች።

የ ሃይማኖታዊ ክብረበአል ነገር ከተነሳ ዘንዳ በጎረቤት ሶማሊያ ለሰላም ማሰከብር ተብሎ ከኢትዮጵያ የተላከው ከ 5ሺህ በላይ የመከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ በግዛቲቱ የሚገኙ ወደ 22 ሺህ የአፍሪካ ሕበረት ሰላም አሰከባሪ ጦር እና የባአዳን ሃይሎች የገና በአል ፣ የዘመን መለወጫ እና የፋሲካ በእላትን ወደ አደባባይ ወጥተው በደማቅ ሁኔታ እንዳያከብሩ ሰሞኑን በመቋደሾ ባለሰልጣናት መከልከላቸው ታውቋል። ለእገዳው ሁለት ምክንያቶች የተጠቀሱ ሲሆን እነርሱም “ ሶማሊያ በአብዛኛው የ እሰልምና እመነት ተከታዮች አገር በመሆኗ ይህ አይነቱ ክብረ በአል ከእስልምና እምነት እና ከማህበረሰቡ ባሕል ጋር ሰለሚጻረር፣ ከበረ ባእላቱ ሲከበሩ የአሸባሪዎችን (የ አልሽባብ )የጥቃት ትኩረትን ሊሰቡ ሰለሚችል ነው።”ተብሏል።መልእክቱ እና ማሰጠንቀቂያው በአጭሩ ሲጠናቀቅ “ ከብረ ባእላቱን ማከበር የሚቻለው በአደባባይ እና ከሆቴሎች ጎራ በሎ በፊሽታ ሳይሆን በምሽጋችሁ፣በጦር ካምፓችሁ አሊያም በቤታችሁ ተወሰናችሁ እና በትዘታ ብቻ ነው “የማለት ያህል አስመሰሏል።

ህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *