Hiber Radio: ኢትዮጵያዊው ግለሰብ የሰው ስጋ በመብላት ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ

ethio_somali_land

(በታምሩ ገዳ)

አንድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የታመነ ግለሰብ እራሷን ከሶማሊያ ገንጥላ ሶማሊላንድ ብላ በምትጠራው ግዛት ውስጥ “የሰው ስጋ በመብላት “ ወንጀል ተጠርጥሮ ሰሞኑን በቁጥጥር ሰር መዋሉን የአካባቢው የፖሊስ ሹም ለዜና ሰዎች ከሰጡት መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ቶጋዲር የተባለችው የሶማሊ ላንድ ግዛት የፖሊስ ኮሚሺነር የሆኑት አህመድ ሙሃመድ ጉታሊ ዋቢ ያደረገው ፑንትላንድ ፖስት ደሀረ ገጽ አሮብ ጥር 13 2016 አኤአ እንደገለጸው አንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ እንደሆነ የተገለጠ ለት ግለሰብን ተጠርጣሪ በማለት መታሰሩን ተናገረዋል። ይህ ማነነቱ በውል ያለተገለጸው ፣ነገር ግን ብሄሩ እና ምስሉ ብቻ ለዜና ፍጆታ የቀረበው ይህ ግለሰብ ሊያዝ የቻለው “እርሱ በሚኖርበት አቅራቢያ የአንድ ጨቅላ ህጻን ጭንቅላት ዘግናኝ በሆነ ምክንያት ተቆራርጦ በመገኘቱ እና ከነዋሪዎች አካባቢ በግለሰቡ እንቅስቅሴዎች ዙሪያ ጥርጣሪዎች ገዝፈው በመታየቸው ነው” ብለዋል። ምንም እንኳን ሶማሊላንድ ሰዎችን አድኖ ሰጋቸውን ወይም የውስጥ የሰውነት ክፍላቸውን የመብላት ወይም ጭራቅነት (ካኒባሊዝም) የክስ አንቀጽ ባይኖራትም “የስዎችን ሰጋን በመብላት “በሚል የወንጀል አንቀጽ ሊከሱት በዝግጅት ላይ መሆናቸው እና የግለሰቡም የ እይምሮ ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ (ጤናማ መሆኑ አሊያም መታወኩን) ምርመራ እናደርግለታልን ማለታቸው ታውቋል።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያዊው ግለሰብ ቀንደኛ ተጠርጣሪ ተደርጎ ቢቀርብም የሰዎችን ሰጋ የመብላት እኩይ ባሕሪይ (ካኒባሊዝም) በሶማሊ ላንድ ታሪክ ውስጥ የተለመደ ያለመሆኑ ፣ነገር ግን ቀደም ባሉት ጊዜያት አንዳንድ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጉያ ሲጠፉ “በሰው በላዎች( ጭራቆች ) ሳይበሉ አለቀረም” የሚል መላ ምት በመኖሩ ሰሞኑንም ተከሰቷል በተባለው ጥርጣሬ መላው የሶማሊላንድ ማህበረሰብ ዘንድ መደናደጥን መፍጠሩ ተገልጿል። በዚህ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ላይ በወደቀበት ተጠርታሪነት እና ውንጀላ ዙሪያ በመዲናይቱ በ ሃርጊሳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ/ቆንጽላ ምን አይነት የህግ እና የዲፕሎማሲ ጣልቃ ገብነት ሰለማድረጉ እና የዜጋውን የሰበዊ መብት በማሰከበር ረገድ እያደረገ ሰላለው ሚና እሰከአሁን ድረሰ በውል አልተገለጸም። እኤአ በ 1901 ከሶማሊያ የተገነጠለችው ሶማሊ ላንድ አለማቀፍ እውቅና የሌላት ነገር ግን የራሷ ህጋዊ ገንዘብ፣ ሰንደቅ አላማ ፣ህገ መንግስት ፣ፓርላማ እና የመከላከያ ጦር ያላት አገር ነች። ሶማሊ ላንድ ከ ወቅቱ የ አ/አ ገዢዎች ጋር ጠበቅ ያለ ግንኑነት ያላት ስትሆን እና የማእከላዊ መንግስቱ ተቃዋሚዎች የሆኑት በተለይ የኦሮሚኛ አና የሶማሊኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያኖችን ለአገዛዙ አሳልፋ የመሰጠት ልማድ ያላት ሲሆን የ ተጠርታሪው ግለሰብ መያዝም ፖሊቲካዊ ይዘት ሰለመኖሩ እና ያለመኖሩ ለጊዜው በውል አልታወቀም።

የሰዎችን ሰጋ ወይም ውስጣዊ አካል የመብላት እኩይ ባህሪ(ካኒባሊዝም) ከ 19ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ በአለም ላይ እየተለመደ የመጣ መጥፎ ባህሪይ መሆኑን የተለያዩ የታሪክ መዛግብት የሚገልጹ ሲሆን ኒው ጊኒ እና የሶሎሞን ደሲቶች በተባሉት አካባቢዎች የስዎች ሰጋን በአንድ ወቅት በገበያ ለሽያጭ ይቀርብ እንደነበር ታሪክ ይተርካል ።

ቀደም ባሉት ጊዜያት የሰው ስጋን የመብላቱ መጥፎ ልማድ ከፉጂ ደሴት አንስቶ በአማዞን ወንዝ ፣ኮንጎ እሰከ ኒ ውዚላንድ ይተገበር ነበር ። በኮንጎ እና በላይቤሪያ በተካሀዱት ዘግናኝ የርስ በርስ ጦርነቶች ወቅት ሰዎች የሰዎችን ሰጋ በጭካኔ እንደበሉ፣ የኡራጓዋይ 571ኛ አየር ሃይል አባላት በ ጥቅምት 1972 እኤአ ኢንዱስ በተባለ ተራራ አካባቢ ተከሰክሰው ለ 75 ቀናት ከእይታ በጠፉበት ወቅት የአውሮፕላኑ ሰራተኞች የሚበሉት ሲያጡ ለመኖር ሲሉ የጓዶቻቸውን ሰጋ በልተው በህይወት መትረፋቸውን “በህይወት መኖር”(Alive) በተባለው መጽሃፍ ውስጥ በታሪክነት የተከተበ ሲሆን ከታዋቂ የአለማችን ስዎች መካከል የማእከላዊ አፍሪካ የቀደሞ ፕ/ት የነበሩት ጄያን ቤደኢን ቦካሳ ተቃዋሚዎቻቸውን በመብላት ወንጀል በ ጥቅምት 24 1986 አኤአ ክስ ቀርቦባቸው ነበር ። ይሁን እንጂ ፕ/ት ቦካሳ ብይን አልተሰጠባቸውም ነበር ። አንዳንድ ስዎች በሰለጠነው አለም ጨምሮ ጤነነታቸው ሲታወክ የሰዎችን ሰጋ ሆነ የውስጥ አካላትን አንደሚበሉ እነዚህም ሰዎች ልዩ የህክምና እገዛ ሊደረግላቸው እንደሚገባ እና ዘወትር በ ጥብቅ ደህንነት ጥበቃ ስር መሆን እንዳለባቸው የሕክምና ባለሙያዎች አበክረው ይመክራሉ።

ህብር ሬድዮ  ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8፡30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *