Hiber Radio: አወዛጋቢውን የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር በዚህ ወር እንዲያካልሉ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መመሪያ ተሰጠ፣በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ሕዝቡ ጥያቄ ስላልተመለሰ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል፣የአቶ አንዳረጋቸው ጽጌ የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አንድ ታዋቂ እንግሊዛዊ የጤና ባለሙያ አሳሰቡ፣በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ረሃብ የዓለማ አቀፉ የግብርና ተቋምን በእጅጉ አሳስቦታል፣ በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ባልታወቀ ሁኔታ የሞተው ወጣት ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ፣አገዛዙ ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት አዲስ ዶክመንተሪ ፊልም አውጥቶ የሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከሽብር ጋር አመሳሰለ፣ አልሽባብ በኢትዮ ኬነያ ድንበር ላይ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን እና መማረኩን ገለጸ እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር መረራ ጉዲና ፣ ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር እና ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ  ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ ፣ከላይ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ጋዜጠኛ ሳዲቅ፣አቶ አንዳርጋቸው ከታች ትምቀት በኣል አከባበር፣ሙስሊሙ ማህበረሰብ በኢድ በዓል ላይ አወዛጋቢውን የኢትዮ ሱዳን ድንበር የሚያሳይ ካርታ
የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ ፣ከላይ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ጋዜጠኛ ሳዲቅ፣አቶ አንዳርጋቸው ከታች ትምቀት በኣል አከባበር፣ሙስሊሙ ማህበረሰብ በኢድ በዓል ላይ አወዛጋቢውን የኢትዮ ሱዳን ድንበር የሚያሳይ ካርታ

የህብር ሬዲዮ ጥር 8 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…አዲሱ የፈጠራ ፊልምን ዶክመንተሪ አልለውም ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት ብለው በከንቱ የደከሙበት ነውየኢትዮጵያ ሙስሊምና ክርስቲያን ከሃያ አምስት ዓመቱ የወያኔ ስልጣን በፊት ለረጅም ዘመን አብሮ የኖረ ነው። በየጊዜው በህወሃት ማሸበሪያ የውሸት ፊልም የሚጋጭ አይደለም…> ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ <<የማንቂያ ደውል>> ስለተሰኘው የአገዛዙ ዶክመንተሪ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በሎስ አንጀለስ የጥምቀት በዓል አከባበር(ቆይታ ከጋዜጠኛ ነጻነት ሰለሞን ጋር)

በዘንድሮ ታክስ አሰራርና የሕክምናና ለበጎ አድራጎት ወጪ የሆኑትን በተመለከተ ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች (ውይይት ከአትላንታ ከአቶ ተካ ከለለ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ጋር ሙሉውን ያዳምጡት)

<…140 በላይ ንጹሃን ከተገደሉና በርካቶች ከታሰሩ፣ከቆሰሉ ፣በርካቶች ከተደበደቡ በሁዋላ ኦህዴድ ማስተር ፕላኑን ትቼዋለሁ የሚለውን ቀልድ ነው። ማስተር ፕላኑን ትቼዋለሁ ማለት ያለበት ሕጉን ያወጣው የኦሮሚያ /ቤት ነው። የኦሮሚያ ክልል አሁንም በወታደራዊ እዝ ስር ነው ።አ መቼ ቀረ?ሕዝቡ ተቃውሞውን ቀጠለው በቂ መልስ ስላላገኘ ነውምዕራባውያን ተገቢውን ተጽዕኖ እየፈጠሩ አይደለም። ገዢው ፓርቲ አገሪቱን ወደ አደገኛ ሁኔታ እየመራት መሆኑን ያውቃሉ ችግሩ ያው ጠመንጃ ከያዘው ጎን የመለጠፋቸው ነው። አሁን አገሪቱ መስቀለኛ ሁኔታ ላይ ነች። ሰራዊቱም ቢሆን> / መረራ ጉዲና የኦህዴድን ማስተር ፕላኑ ቀርቷልና የቀጠለውን ተቃውሞ በተመለከተ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከአገር ቤት ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የአሜሪካው / ባራክ ኦባማ የመጨረሻቸው በሆነው በዓመታዊ ንግግራቸው ላይ ያሰሟቸው ታሪካዊ ንግግራቸው እና የቀረቡባቸው ትችቶች (ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

አወዛጋቢውን የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር በዚህ ወር እንዲያካልሉ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መመሪያ ተሰጠ

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተጠናክሮ ቀጥሏል

/ መረራ ጉዲና ሕዝቡ ጥያቄ ስላልተመለሰ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል

የአቶ አንዳረጋቸው ጽጌ የጤንነት ሁኔታ አሳሳቤ እየሆነ መምጣቱን አንድ ታዋቂ እንግሊዛዊ የጤና ባለሙያ አሳሰቡ

አንዳርቸው ጽጌ ባስቸኳይ ካልተለቀቁ ጤንነታቸው ዳግም ወደ ማይመለስበት ሁኔታ ሊሸጋገር ይችላል/ ቤንጃሚን

በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ረሃብ የአለማቀፉ የግብርና ተቋምን በእጅጉ አሳስቦታል

በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ባልታወቀ ሁኔታ የሞተው ወጣት ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አገዛዙ ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት አዲስ ዶክመንተሪ ፊልም አውጥቶ የሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከሽብር ጋር አመሳሰለ

መምህር ግርማ ወንድሙ ከእስር ከተፈቱ በሁዋላ ተከታዮቻቸውን አመሰገኑ

አልሽባብ በኢትዮ ኬነያ ድንበር ላይ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን እና መማረኩን ገለጸ

ኬኔያ በሽብር ቡድኑ ላይ አይቀጡ ቅጣት እርምጃ እንደምትወስድ አስታወቀች

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-011716-012416

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *