Hiber radio:ታንዛኒያ ረሃብን የሸሹ በርካታ ኢትዮጵያዊያንን “ከአገሬ ጠራርጌ አባርራልሁ” አለች ፣ግብጽ እና ሳውዲ አረቢያም ኢትዮጵያዊያኖችን ማዋከቡን ተያይዘውታል

Ethiopian_tanezania_01

በታምሩ ገዳ

የምስራቅ አፍሪካዋ አገር ታንዛኒያ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ግዛቷ በመግባት ወደ ደ/አፍሪካ ለመሸጋገር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ያደረገቻቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደትኞችን ወደ አገራቸው በ ሃይል ለመመልስ መዘጋጀቷን አሳወቀች። የታንዛኒያው የአገር ውስጥ ደህንንት ሹም የሆኑት ቻርልስ ኪታዋንጋን ዋቢ ያደረገው ዜና ሮይተርስ በማክሰኞ ጥር 26 /2016 እኤ አ እንደገለጸው በኢትዮጵያ የተከሰተውን መጠነ ሰፊ ረሃብን በመሸሽ ለተሳለ ኑሮ ሲሉ ለደላሎች ከ አንድ ሺህ እስከ ሁለት ሺህ ዶላር በመክፈል በታንዛኒያ እና በማላዊ በኩል ወደ ደ/አፍሪካ እና ወደ አውሮፓ ለማምራት አቅደው በአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች እጅ የወደቁ በርካታ ኢትዮጵያዊያኖች እና ሶማሊያዊያኖችን በሕግ አግባብነት በማሰሰ እና በእስራት በመቅጣት ወደ አገራቸው ለማባረር በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ታንዛኒያ በአትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ ጠጠር ያለ እርምጃ ስትውስድ የመጀመሪያዋ አይደለም። በቅርቡ ከ አርባ በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በደላሎቻቸው “ወደ ደ/አፍሪካ እናሸጋግራችኋለን “ ተብለው ተሰፋ ከተሰጣቸው በሁዋላ በሁለት ባዶ ቤት ውስጥ ታጭቀው ሳሉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸው ታውቋል። ቀደም ባለው ጊዜም እኤ አ በሰኔ 29/ 2012 ቁጥራቸው 43 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በእቃ መያዢያ/ኮንቴነር/ ውስጥ ተሸሽገው ከታንዛኒያ ወደ ደ/አፍሪካ ሲጓዙ በረሃብ ፣በውሃ ጥእም እና በአየር እጦት ታፍነው የመሞታቸው የበረካታዎችን ልብ የሰበረው ገጠመኝ አለማቀፋዊ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል። ጎረቤት ማላዊም አንደሁ ቁጥራቸው ከ 250 በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰድተኞችን የጤንነቱ አያያዝ በጣም ዝቅተኛ በሆነ እና እጅግ ዘግናኝ በሆነ እስር ቤት ወስጥ በማጎር ወደ አገራቸው ለማባረር እንቅሰቃሴዎችን መጀመሯን ቀደም ሲል አሰታውቃለች። ከዚሁ ከህገውጥ የሰደተኞች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዜና ግብጽ ሰሞኑን አኢትዮጵያዊኣኖችን ጨምሮ የተለያዩ አገር ዜጎች የተካተቱትበት ከ 40 በላይ ሰደተኞችን በግብጹ ስነይ በረሃ በኩል ወደ እስራኤል ለመሻገር ሲጥሩ ያዝኳቸው በማለት ወደ መጡበት አገር ማባረሯን ካይሮ ፖስት ጋዜጣ ሰሞኑን ዘገቧል ሰውዲ አረቢያም እንዲሁ ሰሞኑን በአንድ በሕገውጥ አዘዋዋሪ የሶማሊያ ዜጋ አማካኝነት ደንበሯ ውስጥ ዘልቀው ሲጓዙ የነበሩ አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች እና አንድ ጨቅላ ልጅ መያዛቸውን ሳውዲ ጋዜት የተባለ የአገሪው ጋዜጣ ዘገቧል። ጋዜጣው በሃተታው ላይ ተጠርጣሪው ግለሰብ በአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ተይዞ አብረውት በመኪና ውስጥ ሰለነበሩት ገለሰቦቹ ማነነት ሲጠየቅ “ቤተሰቦቼ ናቸው” በማለት ህገውጥ መታወቂያ በማሳየት ለማታለል ቢሞክርም ሁሉም ተጠርጣሪዎች ከ ፖሊስ መዳፍ ከመወደቅ አላመለጡም ተብሏል።ሰውዲ አረቢያ ከ አንድ አመት በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያኖችን ከ አገሯ በገፍ ማባረሯ በሔራዊ ሃዘን እና ቁጣ መቀሰቀሱ አይዘነጋም። ታዲያ ይህ አይነቱ የረሃብ እና የመልካም አሰተዳደር እጦት ሰለባ የሆኑ የበርካታ ኢትዮጵያዊያን አሰከፊ የሰደት ጎዞ እና ያሰቡት ሳይሳካ ህይወታቸውን እሰከ ማጣት ጨምሮ ለተለያዩ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች የመዳረጋቸው እጣ ፈንታ መቼ ይቆም ይሆን? በሎ መጠየቁ እና ለችግሩ መንሴዎችም መፈትሄ ማፈላለጉ ግድ ይላል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *