Hiber radio: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ትግሉ አገር ቤት መግባቱንና እሳቸውም ከትግሉ እንደማይርቁ ገለጹ፣ ግንባሩ የኢትዮጵያን ህልውና ከሚቀበሉ ሀይሎች ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል፣በጋምቤላ ክልል በተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት የበርካት ሰዎች ሕይወት እየጠፋ ነው ቤት ንብረት ወድሟል፣ ምዕራባዊያን ዲፕሎማቶች ዜጎቻቸው ወደ ስፍራው እንዳይጓዙ ጥብቅ ማስጠቀቂያ ማስተላለፋቸው ተገለጸ፣ በጋምቤላ የተከሰተው የጎሳ ግጭት ሳይሆን አገዛዙ የሚያካሂደው የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑ ተገለጸ፣ የሱዳን ከፍተኛ ባለሰልጣናት አወዛጋቢው የኢትዮ- ሱዳን ድንበርን መጎብኘታቸው ታወቀ፣የተመድ ዋና ጸሐፊ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያንነ ሕዝባን እንዲታደጋት አዲስ አበባ ላይ ጥሪ አቀረቡ የሚሉና ቃለ መጠይቅ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለተገኙበት የዲሲ ስብሰባ፣በአገር ቤት ትኩረት ስላላገኘው አሳሳቢ የረሃብ አደጋ፣በጋምቤላ ወቅታዊ የዘር ማጥፋት እርምጃ ለይ እንዲሁም ስለ ዚካ ቫይረስ ወቅታዊ ዘገባ እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ፣ከላይ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣በጋምቤላ የወቅቱን ግችት የሚያሳይ፣ኢ/ር ኦዶል ኦጁሉ፣ከታች ባን ኩሙን፣በድርቁ የተጠቁ ወገኖች፣ጋዜጠና አናኒያ ሶሪና የዚካ ቫይረስ መግለጫ
የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ፣ከላይ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣በጋምቤላ የወቅቱን ግችት የሚያሳይ፣ኢ/ር ኦዶል ኦጁሉ፣ከታች ባን ኩሙን፣በድርቁ የተጠቁ ወገኖች፣ጋዜጠና አናኒያ ሶሪና የዚካ ቫይረስ መግለጫ

የህብር ሬዲዮ ጥር 22 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…የአርበኞች ግንቦት ሰባት ትግል የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ ታልቅ ስብሰባ ነው። / ብርሃኑ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ወታደሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው ትግሉ አገር ቤት ገብቷል ብለዋል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ያህል የነጻነት ፍላጎት እንዳለው የሚያሳይ ስብሰባ ነው/ ብርሃኑ ትግሉን ጥሎ የትም እንደማይሄድ፣በዘር ፖለቲካ ያበዱትን ተዋቸው ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የምትገነባበት ሁኔታ ላይ በጋራ መታገል እንደሚያስፈልግ ተናግሯል። በስብሰባ ቦታ የነበረው ጥበቃ በመሳሪያ የታገዘ ነበር።ይሄም…> አክቲቪስት መኮንን ጌታቸው ከዲሲ ግብረሃይል ከስብሰባው አስተባባሪዎች አንዱ ትላንት በዋሽንግተን ዲሲ ከኤርትራ መልስ / ብርሃኑ ነጋ በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ያደረጉትን አስመልክቶ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ለድርቁ ትኩረት አልተሰጠም። 15 ሺህ ብር የገዛነውን ዕርዳታ ለማከፋፈል በረሃብ ወደተጠቁት ከቀይ መስቀል ጋር የሄዱት አባሎቻችን በፊልም  አስደግፈው ያመጡት መረጃ ዛሬም ወገኖቻችን በረሃቡ ሳቢያ ከፍተኛ ችግር ላይ ናቸው። አንዲት ሴት ምግብ ፍለጋ ወጥታ ስትመለስ ልጇ በረሃብ ሞቶ ለቅሶ ተቀምጣ ደርሰዋል።እርዳታ ለመቀበልም መጥጦ ስምህ ዝርዝር ውስጥ የለም ተብሎ የተመለሰ አለ።በድርቁ ለተጠቁት ፈጥነን መድረስ ካልቻልን ግን…> ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ የቤዛ እንሁን በበጎ ፈቃድ በድርቅ ሳቢያ በረሃብ አደጋ ላይ ለወደቁት ዕርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ስለ ድርቁ ተጠይቆ ከሰጠው ምልሽ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በጋምቤላ እየተደረገ ያለው የጎሳ ግጭት አይደለም በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ሆን ብሎ ኑዌሮችን አስታጥቆ አስቀድሞ አኚዋኮችን ትጥቅ አስፈትቶ ከጀርባ ሆኖ የሚያካሂደው የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው። አኙዋኮች ባለመሬት ባለ አገር ናቸው።በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያነምኑ በመሆናቸው የጥቃት ሰለባ ሆነዋል። ይሄ የዘር ማጥፋት እንጂ ጎሳ ከጎሳ የተጋጨበት የሚለው አይሰራም … > / ኦዶል ኦጁሉበቅርቡ የተመሰረተው  የታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አስተባባሪ   በወቅታዊ ሁኔታ ላይ  ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ኢትዮጵያውያን በዘር መከፋፈል አንተ ኦሮሞ አንተ አማራ ማለት የለባቸውም ።ኦሮሞ ወገኖቻችንን እየገደሉ ያሉ የሚከፋፍሉንን አትስሙ ።ሁሉም ተከባብሮ ተፋቅሮ አንዱ ለአንዱ ጥቃት መድረስ አለበትእግዚያብሄር ኢትዮጵያውያንን አንድ የሚያደርግ የወገኖቹ ችግር የሚሰማው መሪ ይስጠን። ኦሮሞው አማራውን ያክብር አማራውም ኦሮሞውን ያክብር አንዱ …> ብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ በላስ ቬጋስ በአገር ቤት በኦሮሚያ ለሞቱ ወገኖች፣በድርቁ ሳቢያ ለሞቱ፣በሰሜን ጎንደር እየተገደሉ ላሉት በከተማዋ በተጠራው የጸሎትና የሻማ ማብራት ላይ ተገኝተው ከተናገሩት(ቀሪውን  ያድምጡት)

 የአለማችን የወቅቱ ሰጋት የሆነው    እና ቢጫ  ወባ 23 በላይ ሓገሮችን  በማጥቃት  አራት ሚሊዮን በላይ ሕዝብን ለመበሽታ ጋር ተዛማጅነት ያለው  የዚካ ቫይረስን በተመለከተ የዓለማቀፉ ማህበረሰብ አመለካከት እና ምላሾቹ ( ልዩ ዘገባ)

 ሌሎችም

ዜናዎቻችን

/ ብርሃኑ ነጋ ትግሉ አገር ቤት መግባቱንና እሳቸውም ከትግሉ እንደማይርቁ ገለጹ

ግንባሩ የኢትዮጵያን ህልውና ከሚቀበሉ ሀይሎች ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል

በጋምቤላ ክልል  በተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት የበርካት ሰዎች ሕይወት  እየጠፋ ነው  ቤት ንብረት  ወድሟል

 ምእራባዊያን ዲፕሎማቶች ዜጎቻቸው ወደ ስፍራው እንዳይጓዙ   ጥብቅ ማስጠቀቂያ ማስተላለፋቸው ተገለጸ

በጋምቤላ የተከሰተው የጎሳ ግጭት ሳይሆን አገዛዙ የሚያካሂደው የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑ ተገለጸ

የሱዳን ከፍተኛ ባለሰልጣናት አወዛጋቢው የኢትዮሱዳን ድንበርን መጎብኘታቸው ታወቀ

የሱዳን ሕዝብ  ከኢትዮጵያ ታጣቂዎች ጥቃት እንዳይደርስበት  ካርቱም የመከላከያ እና የደህንነት ሃይሏን በድንበሮቹ  ላይ እንድታሰፈር  ተጠየቀ

የተመድ ዋና ጸሃፊ ዓለማቀፉ ማህበረሰብ አትዮጵያን እና ሕዝቧን ከረሃብ እልቂት እንዲያድን  አዲስ አበባ  ላይ ጥሪ አቀረቡ

አትዮጵያን እና ሕዝቧን ከእልቂት የማትረፉ ብቸኛው ጊዜ ቢኖር ዛሬ እና አሁን ብቻ ነውበኢትዮጵያ የአለማቀፉ ሕጻናት አድን ዋና ተጠሪ

ካናዳ ሊሄዱ የነበሩ ሁለት ኤርትራውያን ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ሞቱ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-013116-020616

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *