Hiber Radio: ጠ/ሚ/ር ሃይለማሪያም በጋምቤላው ጭፍጨፋ የደቡብ ሱዳን ጦር እጅ ስለመኖሩ መረጃ ደርሷቸዋል ተባለ፣ቤተሰቦቻቸን ሲጨፈጨፉ ምላሹ ዝመታ ከሆነ እንዴት የዚህች አገር ልጆች ልንባል ይቻለናል?” ለጠ/ሚ/ሩ ከተላከ የቅሬታ ደብዳቤ የተቀነጨበ

gambella-002

በታምሩ ገዳ

ባለፈው አርብ ከ ጎረቤት ደ/ሱዳን እንደመጡ የተነገረላቸው ፣ እጅግ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት የደምብ ልብስ እንደለበሱ የሚነገሪላቸው ከ አራት ሺህ በላይ ታጣቂዎች የኢትዮጵያ ሉእላዊ የግዛት ክልልን በመጣስ በደቡባዊ ምእራብ የአገሪቱ ክፍል በጋምቤላ ክልላዊ መስተዳደር በሚገኙ ሰላማዊ እና ያልታጠቁ ዜጎች በሚኖሩባቸው 10 መንደሮች ውስጥ ከ208 በላይ የኑኢር ማህበረሰብ አባላት ላይ ያድረሱት እጅግ ዘግናኝ እና ጭካኔ የተሞላበት የጅምላ ግደያ፣ ከ 100 በላይ ህጻንትን አፍኖ የመወሰድ እና ከ 2000 በላይ የቀንድ ከብቶችን የመሰረቅ ወንጀል መላው የኢትዮጵያን ሰላም ወዳድ ሕዝብን በተለይ ደግሞ የአካባቢው ተወላጆችን በእጅጉ እሳዝኗል፣ አሰቆጭቶ ሰንብቷል ። አንደ ሃገርም በሔራዊ ውርደትን አሰከትሏል ።

የክልሉ ነዋሪዎች በተይይ ደግሞ ቤተሰቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው የጅምላ ጭፈጨፋው ሰለባዎች የሆኑባቸው በውጪው አለም ( በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳልኝ ሰሞኑን በላኩት ደብዳቤያቸው በከፊል “ ለአስራ ሁለት ሰአታት በዘለቀው ጭፈጨፋ ፣ የደ/ሱዳን የሙሪ ታጣቂዎች የፈለጉትን አደርገው ሲሄዱ ጭፈጨፋውን ለማስቆም የአገር የመከላከያ ሃይሉ ሚና ምን ነበር? ጦሩስ የት ነበር? ከጋምቤላ ከተማ አንስቶ ከግጭቱ እቅራቢያ (ኑኢር ዞን) ለመድረስ የሚያሰችሉት ሁለት አወራ ጎዳናዎች ከ አንድ ሰአት የማይፈጅ መሆኑ እየታወቀ ይህን አይነቱ ዘግናንኝ ጨፈጨፋ በሰላማዊ ወገኖች ላይ ሲካሄድ ወገናዊ ኣና ሙያዊ ምላሽ ለመሰጠት ዘገምተኝነቱ ከየት መጣ?” ሲል ይጠይቅና “ቤተሰቦቻቸን በጅምላ ሲጨፈጨፉ ዝምታው ከበረታ እንዴት የዚህች አገር (የኢትዮጵያ ልጆች ተብለን ልንጠራ ይቻለናል?” በማለት ምሬታዊ ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ። በአካባቢው እንደዚህ አይነት ጭፍጨፋዎች በተለያዩ ጊዜያት እና ወገኖች አማካኝነት ሰፈጸም መመልከት እየተለመደ የመጣ ጉዳይ ቢመሰልም ጥቃቱን ለመከላከል ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል አንዴም የ አጠፋ እርምጃ ሲወስድ አልታዩም። የተለያዩ ምክንያቶች ቢደረደሩም የወቅቱ የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት የሰላማዊ ዜጎቹን ደህንነት ለመታደግ የተሳነው ፣የራሱ ደህንነት እና ፍላጎት እሰከተሟላለት ድረስ ለተቀረው ማህበረሰብ ዴንታ የለውም ማለት ነውን?”ሲል በደበዳቤው የጠየቀው የክልሉ ተወላጆች አቤቱታ የጅማል ጭፈጨፋውን ፣አፈናውን እና ዝርፊያውን በተመለከተ “የደቡብ ሱዳን የመከላከያ ሰራዊት እጁ ሰለመኖሩ የሚያረጋግጥ ደበዳቤ ለጠ/ሚ/ር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ደረሷቸው ነበር ።”የሚል መል እክትም በደብዳቤው ላይ ተካትቷል። የ ዘግናኙ ጭፍጨፋን ትከትሎ የክልሉ ፕ/ት የሆኑት አቶ ጋቱላክ ቶት በ ሁሉም ቀበሌዎች በመዘዋወር ሰለሞቱት ሰዎች፣ ሰለቆሰሉት ፣ ታፈነው ሰለትወሰዱ ሰላማዊ ዜጎች እና በሺዎች ሰልሚቆጠሩት ሰለተዘረፉት የቀንድ ከብቶቻቸው ጉዳይ ለማህበረሰቡ እባላት ማስረዳታቸውን ያወሳው የአካባቢው ተወላጆች (የኑኢር ልጆች ) የአቤቱታ ደበዳቤ የሱዳንን ድንበር ተሻግረው በጋምቤላ ውስጥ በሰላማዊ ዘጎች ላይ ጥቃት የፈጸሙት የሙራሌ ጎሳ ተወላጆች እጅግ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ታጥቀው አንደነበር አና በወቅቱም የደቡስ ሱዳን የጦር ሰራዊት ልብስ(ዩኒፎርም) ማድረጋቸውን የክልሉ ባለሰልጣኑ (አቶ ጋቱላክ) ለማህበረሰቡ መናገራቸው ክ አካባቢው ነዋሪዎች የወጡ ዘገባዎች ገልጠዋል። በረካት የማህበረሰቡም እባላት ይህንንኑ መረጃ በሰፋት ይጋሩታል ተብሏል።

ከአካባቢው ተወላጆች ለጠ/ሚ/ሩ ለአቶ ሃይለማሪያም የተላከው ደብዳቤም ይህ አይነቱ ጥቃት በማንኛውም መንገድ ሊወገዝ እና ተመጣጣኝ እርምጃዎች ሊወሰደበት እንደሚገባው አበክረው የጠየቁ ሲሆን አቶ ሃይለማሪያ ቢሆኑ ሁኔታውን ወደ ደንበር ተሻጋሪ የጎሳዎች ግጭት በማሰመሰል ጉዳዩን ከማሳነስ በማያወላዳ መልኩ ለ/ደ ሱዳን መንግስት የወግዘት እና የጸና አቋም አዘል መልእክት ሊያሰሙ በተገባ ነበር ብሏል። ይሄው የማህበረስቡ ደብዳቤ በመለጠቅም በሃይል ታፈነው የተወሰዱት ከ 125 የኑኢር ህጻናት ሳይውል ሳያድር በ ደ/ሱዳን መንግስት በኩል ከታጣዊዎቹ እጅ ያለቀደመ ድርድር ወደ ትውልድ ቀያቸው እና ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ገዢው መንግስት ፈጣን ጣልቃ ገበነት ሊያድረግ የገባል ሲሉ በተማጽኖ ደብዳቤያቸው ጠይቀዋል።

ምንም እንኳን የወቅቱ ጊዢው መንግስት በ ደ/ሱዳን ታጣቂዎች ላይ እርምጃ በመወሰድ 60 ያህል መግደሉን እና ለወደቁት ወገኖቻቻን የሁለት ቀናት ብሄራዊ የሃዘን ቀን ቢያውጅም በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አይምሮ ውስጥ ሰሞኑን አንድ የሚብላላ ጥያቄ እርሱም “ ከራሱ አልፎ በጎረቤት ሶማሊያ ሰላም እና መረጋጋት ለማሰፈን በሺዎች የሚቆጠር ስራዊቱን የላከ ፣ከሸሃራ በረሃ በታች ጥንካራ ስራዊት ገንብቻለሁ የሚል አገዛዝ በዚያ ሰሞን በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል (ከኤርትራ በኩል ) የኤርትራ ወታድሮች የደንብ ልብስን የለበሱ እና የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሆኑ ታጣቂዎች በትግራይ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በባህላዊ የወርቅ ማውጣት ስራ ላይ የነበሩ ከ80 በላይ ሲቪሎችን አፍነው ወደ ኤርትራ ግዛት በመውሰድ ፣የተወሰኑትን በመግደል ፣ የተቀሩትን ለሳምንታታ ካስሯቸው በሁዋላ የተወሰኑትን መልቀቃቸውን የወጪ ሚዲያዎች ከአገዛዙ ሚዲያዎች ቀድሞው ዘግበውታል። አሁን ደግሞ በጋምቤላ አካባቢ የደ/ሱዳን ጦር ስራዊት ልብስ በለበሱ እና ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ባነገቱ ብዛት ባለቸው ታጣቂዎች ይህን መሰል ዘግናኝ ድርጊት ከተፈጸመ ከአስራ ሁለት ሰአታት በሁዋል አገዛዙ ምርዶውን ይዞ ለሕዝቡ ብቅ አለ። ታዲያ የመከላከያ ስራዊቱ ሃላፊነት እና ሚናው ምንድን ነው? ፣ የኢትዮጵያ ሉአላዊ ክልልስ የቱ ጋር ነው?፣ ኢትዮጵያ እና ዘጎቿ ከጠላት ሃይል የሚታደጋቸው ስራዊት ከሌለ ማን ሊጠብቃቸው ይሆን?፣አያድርገው እና ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ አኢትዮጵያን የሚወረው/ጥቃት የሚያድረሰው ቀጣዩ ጎረቤት አገር እና የጥቃቱ ሰለባ የሚሆነው ባለተራ የየትኛው ማህበረሰብ ክፍል ሊሆን ነው ?” ሲሉ አበክረው ይጠይቃሉ፣ ሰጋታቸውንም በተለያዩ መደረኮች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ ።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *