Hiber radio: በጋምቤላ ከተማ ውጥረት እንደነገሰ ነው አንዲት ኢትዮጵያዊት በደቡብ ሱዳን ስደተኛ በከተማው በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ እንደተፈጸመባት ተነገረ፣በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ ለመከላከል በቂ እርዳታ ያልተገኘው በአገዛዙ ግዴለሽነት ለጋሾች በመዘናጋታቸው መሆኑ ተገለጸ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎችና ወቅታዊ ዘገባዎች በሙሉ ፕሮግራሙ ተካቷል

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 16 ቀን 2008 ፕሮግራም

<… ሰራዊቱ ከጋምቤላ የተወሰዱትን ህጻናት ለማስለቀቅ ከበባ ፈጽማል የሚሉት ነጭ ውሸት ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብን ማታለል አካባቢውን አያውቁም ብሎ ማታለል ነው።ግድአውና አፈናው የተካሄደው ጃካዋ የሚባል ድንበር ላይ ነው እነሱ ሰራዊት ይዘን ሄድን ያሉት ኮክና ጆር ነው በጃካዋና በኮክና ጆር መሐል ከሁለት መቶ እስከ ሶስት መቶ ኪሎ ሜትር ባላይ ርቀት አለ።ማንን ነው የሚአታልሉት…ወያኔ አማራውን፣ኦሮሞውን ራሱ ይገድል የለም በጋምቤላ የሚደረገውን ግድያና ከመሐል አገር በመጡ ወገኖቻችን ላይ ጃካዋ በቀደም ያ አሰቃቂ ግድያ ሲደረግ ግድ የላቸውም። የእነሱና የሪክ ማቸር የምስጢር ግንኙነት ምን አልባት ለታላቃ ትግራይ ግማሱን የጋምቤላ መሬት ወስደው የቀረውን ለሪክ ማቻር ለደቡብ ሱዳን ለመስጠት ያሰበ ይሆናል።ሪክ ማቸርን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ለማድርግ የሚፈልጉት…> አቶ ጊብሰን ኦባንግ የታህሳስ ሶስት ዲማክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበርና የቀድሞ የጋምቤላ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር ም/ሊቀመንበርበጋምቤላ በወቅቱ ያለውን ውጥረትና በደቡብ ሱዳን ስደተኞች  የተወሰደውን ግድያ አስመልክቶ   ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ     (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በሱዳን ካርቱም ብቻ የሞት ፍርድን ጨምሮ በአል ሁዳ ብቻ 51 ኢትዮጵአውአን እስረኞች አሉ። የተሌአየ ስቃይ ይደርስባቸዋል ቢአንስ አገራችን ገብተን እንታሰር እንኳ ብለው የኢትዮጵአ ኤምባሲ አልሰማቸውም ጉዳያቸውን ዞር ብሎ አያይም…የደቡብ ሱዳን ዜጎች የሆኑ 42 እስረኞች ከዚህ ኢትዮጵአውያኑ ካሉበት አል ሁዳ እስር ቤት በዲፕሎማሲ ጥረት ተፈተው ሲሄዱ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ቀርቧል የእኛ ወገኞች ግን አስተዋሽ አጥተዋል። ምንም የማያውቁ ከአገራቸው ግዛት ከድንበር አቅራቢአ ታፍነው መጥተው ሻሸመኔ(በአካባቢው አጠራር ሐሺስ) ታዘዋውራላችሁ ተብለው ታስረዋል። ብዙዎቹ በሻሸመኔና ጫት በማዘዋወር ጉዳይ ነው አንድ ብቻ የ17 ኣመት እያለ የዛሬ አራት ኣመት ሰው ገደለ ተባለው እሱ ሞት ፍርደኛ ነው…> አቶ መሐሪ ሐጎስ ረዳ ከሱዳን በእስር ላይ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምቱት)

<…ሁበርና ሊፍትን እንደ ሙሉ ስራ መስራት ይቻላል።እሱኑ እየሰራሁ ነው። ሁኔታውን ስትመለከተው ከዚህ በሁዋላ የታክሲ ስራ በዚህ በቬጋስ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ቦታ እየቀነሰ ነው የሚሄደው በአንጻሩ የሊፍትና ሁበር ደግሞ እየጨመረ ይሄዳል ። እየታየ ያለውም እሱ ነው…በአብዛኛው የሀበሻ እረፍት ቀናት የሁበርና ሊፍትም ስራ የቀዘቀዘ ነው ያንን ይዘህ ስራው አያዋጣም ማለት አይቻልም እኔ እንካን አሁን የታክሲ ስራው ቀንሶ ሳይሆን ደህና ነው ከሚባልበትም የተሻለ ነው የምሰራው። መፍራት ሳይሆን መሞከር የተሳለ ነው…> አቶ ፍቅረስላሴ ወልደየስ ከቬጋስ ሁበርና ሊፍትን በሙሉ ጊዜው የሚሰራ ስለሁበርና ሊፍት ስራ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

በሜደትራኒያን ባሕር ላይ ሰሞኑን በተከሰተው የሰደተኞች እልቂት በርካታ ኢትዮጵያዊያኖች ሰለመኖራቸ፣ አሳዛኙ ድርጊት ሲፈጸም በሰፍራው የነበርው   ባለቤቱን እና ህጻን ልጁን ያጣው ኢትዮጵያዊ ሰደተኛ መሪር ትዝታው የተዳሰሰበት ዘገባ (ልዩ ጥንቅር)

በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በአገዛዙ አፈና እርምጃ ተጽዕኖና የትግሉ መሪዎችን በተመለከተ የሚነሱ ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ከጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳና ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር የጀመርነው ውይይት ሁለተኛ ክፍል (ሙሉውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በጋምቤላ ከተማ ውጥረት እንደነገሰ ነው አንዲት ኢትዮጵያዊት በደቡብ ሱዳን ስደተኛ በከተማው በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ እንደተፈጸመባት ተነገረ

በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ እና ረሃብ ለመከላከል በቂ እርዳታ ያልተገኘው በአገዛዙ ግዴለሽነት ለጋሾች በመዘናጋታቸው መሆኑ ተገለጸ

በረሃቡ ሳቢያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሕይወት እንዳይቀጥፍ ተሰግቷል

በሱዳን የሞት ፍርድን ጨምሮ ከ10 እስከ ሃያ ዓመት የተፈረደባቸው ኢትዮጵያውያን እስረኞች ከስቃይ አገራችን ገብተን እንታሰር ቢሉ ኤምባሲው ትኩረት መንፈጉ ተገለጸ

በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ባልተጠበቁበት ፍርድ ቤት ድንገት ቀርበው የሽብርተኝነት ክስ ቀረበባቸው

<<እስር ቤት ሰዎች የሚመርጡት ቦታ ሳይሆን ለኢትዮጵአውአን የተሰተ መጥፎ በረከት ነው..>> አቶ በቀለ ገርባ ከመጀመሪአው እስር እንደወጡ ከሰቱት ሰትተውት የነበረ አስተያየት

በቅሊንጦ በእስር ላይ የሚገኙት የሕጋዊው መኢአድ የደቡብ ጎንደር ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ በደረሰባቸው ስቃይ ሕይወታቸው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

ኬኒያ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ግዛቴ ገብተዋል ያለቻቸውን ኢትዮጵያውያን ሰሞኑን አስራ በርካቶቹን ለአገዛዙ አሳልፋ ለመስተት ተዘጋጅታለች ተባለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላ

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-042416-050116

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *