Hiber Radio: በኢትዮጵያ በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ በዓል ብዙሃኑን ሕዝብ የሚያሳቅቅ መሆኑ ተገለጸ፣ኢትዮጵያ ሰራዊቷን በ/ደ/ሱዳን ግዛት ውስጥ እንዳታስገባ የአገሪው ማህበረሰብ ተወካዮች አጥብቀው አስጠነቀቁ፣ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ገዚዎች ዛሬም ቀንደኛ የነጻ ፕሬስ ጠላቶች ተብለው ተፈርጀዋል ሌሎችም ዜናዎችና ሙሉ ፕሮግራሙን አድምጡ

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 23 ቀን 2008 ፕሮግራም

ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳዔው አደረሳችሁ

<…በዓሉ ለብዙሃኑ ሕዝብ የሚያሳቅቅ ነው።የኖሮ ውድነቱ የሕዝቡን መቸገር ታዋለህ። ይህ ሲባል ዓመቱን በሙሉ በዓል የሆነላቸው ጥቂቶች አልተፈጠሩም ማለት አይደለም። ሙስናውና ለስርዓቱ ማጎብደድ እነዚህን ፈጥሯልየኢትዮጵያ ትንሳዔ ቅርብ ነው ሊነጋ ሲል ይጨልማል የሚባለው ለዚህ ነው።ተመልከት በኢትዮጵያ አሁን ሞቱም፣እስሩም ፣ረሃቡም ሁሉም ተከታትሎ እየመጣ ነው። ከዚህ በሁዋላ የሚመጣው ብሩህ ቀን ነው።ያ እንዲመጣ ግን እያንዳንዱ…> ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የአዲስ ገጽ ዋና አዘጋጅ የዘንድሮ በዓልንና የብዙሃኑን ኑሮ በተመለከተና ተያያዥ ወቅታዊ ጉዳዮችን ላይ ተወያይተናል (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ከሁለት ሳምንት በፊት ሜዲትራኒያን ባህር ላይ ከሰጠሙ ወገኖቻችን ወዲህ ሌሎች ሁለት መቶ ሰዎች ሄደዋል ይባላል መረጃ ማግኘት ይከብዳል ሰው አማራጭ ስላጣ ያንን መንገድ ይከተላል.ኤን.ኤች..አር ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ትኩረት አይሰጥም። እኛን መስማት አይፈልግም ችግራችንን እየተረዳ አይደለም…> አቶ እንዳልካቸው ይልማ በግብጽ የኢትዮጵአውያን ስደተኞች ማህበር /ጸሐፊ   ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡት)

እየተሟሟቀ  እና አየተካረረ የመጣው የአሜሪካዊያን  እጩ ፕሬዘዳንታዊ  ምረጡኝ   የቅሰቀሳ ዘመቻ ሰሞናዊ  ውሎው የጫረው አግራሞት  ፣ቱጃሩ  ዶናልድ ትራምፕ ለተቃዋሚዎቻቸው የላኩት የመጨረሻው መልእክት ምን ይላል?፣እውን ዶናል ትራምፕ በጸረ  ሙስሊሞች እና በጸረ ሰደተኖች አቋማቸው  ይገፉበት ይሆን? የቅደሞዋ  የወጪ // ሂለሪ ክሊንተን  ተፎካካሪያቸው በርኒ ሳንደረስን ለምን አወደሷቸው ?(ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ በዓል ብዙሃኑን ሕዝብ የሚያሳቅቅ መሆኑ ተገለጸ፣ኢትዮጵያ ሰራዊቷን በ/ደ/ሱዳን ግዛት ውስጥ እንዳታስገባ የአገሪው ማህበረሰብ ተወካዮች አጥብቀው አስጠነቀቁ፣

ከግብጽ ተጨማሪ ሁለት መቶ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በባህር ለመሻገር መሄዳቸው ተሰማ

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ለኢትዮጵአውአን ስደተኞች ትኩረት እንደማይሰጥ ተገለጸ

በቅርቡ ከጋምቤላ ታፍነው ወደ ደ/ሱዳን ከተወሰዱት 125 ጨቅላ ህጻናት ውስጥ 32ቱ በገፍ ተጥለው ተገኙ

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ገዚዎች ዛሬም ቀንደኛ   የነጻ ፕሬስ ጠላቶች ተብለው ተፈርጀዋል

የዞን 9 ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች የዓመቱ የተሸላሚዎች ምርጫን አሸነፉ

16 ኪሎ የሺሻ ቱምባሆን በህገወጥ መንገድ ወደ ም/አወሮፓ ለማሰገባት የሞከረች ኢትዮጵያዊት ለአስራት ተዳረገች

በጋምቤላ ለተፈጠረው ችግር የስርዓቱ ባለስልጣናት ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች በስብሰባ ላይ ገለጹ

ግብጽ በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ፈጻሚዎች ላይ ከባድ ቅጣት ጣለች፥አለማቸውን ሲቀጩ የነበሩ የድርጊቱ ፈጻሚዎችንም በካይሮ ጎዳናዎች ላይ አራቁትታቸውን አንዲሂዱ አድርጋለች

የጎርቤት ሶማሊዎች ኢትዮጵያ የልዩ ሃይል ታጣቂዎች  በደል እና ስቃይ አየድረሰብን ነው ሲሉ አማረሩ

ሁኔታውን ለማርገብ የአገዛዙ ባለስልጥናት ወደ ስፍራው ሊጓዙ  መሆኑ ተነገረ

ዘንድሮም የበዓል ገበያ በአገር ቤት እንደተወደደ አለፈ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-050116-050816

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *