Hiber Radio: ጌታቸው ረዳ በአባይ ጉዳይ የሰጡት ያልተገራ አስተያየት የግብጽ ባለስልጣናትን አስቆጣ፣ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በዝዋይ እስር ቤት የጻፍከው ጽሑፍ ተገኘ በሚል ጨለማ ቤት እንዲገባ ተደረገ፣ ከጋምቤላ የታፈኑት ጨቅላ ህጻናት በደ/ሱዳን ውስጥ ለሽያጭ ሳይቀረቡ እንዳልቀረ ተሰግቷል፣የአሜሪካ ሴኔተሮችና ዲፕሎማቶች በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዙሪያ የተሰማቸውን ስጋትጋት ገለጹ የሚሊና ሌሎችም ዜናዎች የተካተቱበት ሙሉ ፕሮግራሙን ያድምጡት

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ግንቦት 21 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…አሁን ያለው አስተዳደር አንድ ቅርጽ ይዞ እንደ መንግስት የሚሰራ ሳይሆን ጥቂት ግለሰቦች እና ቡድኖች በዙሪያቸው ባሰባሰቧቸው ተጠቃሚዎች የሚመራ የጠባብና ዘረኛ ቡድን   የሚያሽከረክሯት  አገር ነች።…ግንቦት ሃያን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመለከተው እንደ ክፉ ቀን የመጣበት፣ዘረኝነት የተስፋፋበት ፣ሙስና የተስፋፋበት ነው … እነሱ ሃያ አምስት ሲያከብሩ እኛ አንድ ብለን በጋራ ለለውጥ የተምንነሳበት ወሳኝ ወቅት ነው ይህ ካልሆነ ግን…> አቶ ግርማ በቀለ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት ሊቀመንበር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአገር ቤት ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በመኢአድ ስም የተጠራው ጉባዔ ያው የተለመደ ሕገ ወጥ ተግባር አካል ነው።ሕጋዊ የመኢአድ የም/ቤት አባላት አልተጠሩም ። ከዚህ ቀደም ከአንዴም ሁለቴ የተደረገውን ከመላው አገሪቱ የተሰባሰቡ ሕጋዊ የመኢአድ አመራሮች የተሳተፉበትን በራሱ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ ከአንዴ ሁለቴ የተደረገውን ጉባዔ ውጤት ሰርዘው ሕጋዊውን አመራር በፖሊስ ከጽ/ቤት አባረው ከቤቱ አምጥተው የሾሙት ነው ዛሬ ስልጣኑን ለማራዘም የብአዴን አባላትን ሰብስቦ ጉባዔ ጠራሁ ያለው።ህግን መሰረት ያላደረገ ነው…በተቃዋሚዎች ላይ የሚወስዱት እርምጃ ስርዓቱ እንዳሰበው አላጠነከረውም ሕዝቡ የራሱን ትግል እየመረጠ ነው ።በቃኝ ብሏል…> አቶ ማሙሸት አማረ የሕጋዊው መኢአድ ፕሬዝዳንት ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በቬጋስ ተጠርቶ ውቴታማ ያልሆነው የሁበር አሽከርካሪዎች ተቃውሞና ተያያዥ ጉዳዮች

የዛሬ ስድስት ዓመት በኡጋንዳ ከሚገኝ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ላይ ጥቃት በማድረስ የሰው ሕይወት የቀጠፉ አሸባሪዎች ሰሞዩን የተላለፈባቸው ውሳኔ ሲዳሰስ(ልዩ ዘገባ)

በኢሚግሬሽን እስር ቤት ስላሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ጌታቸው ረዳ በአባይ ጉዳይ የሰጡት ያልተገራ አስተያየት የግብጽ ባለስልጣናትን አስቆጣ

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በዝዋይ እስር ቤት የጻፍከው ጽሑፍ ተገኘ በሚል ጨለማ ቤት እንዲገባ ተደረገ

ከጋምቤላ የታፈኑት ጨቅላ ህጻናት  በደ/ሱዳን ውስጥ ለሽያጭ ሳይቀረቡ እንዳልቀረ ተሰግቷል

የአሜሪካ ሴኔተሮችና ዲፕሎማቶች  በአቶ አንዳርጋቸው  ጽጌ ዙሪያ   የተሰማቸውን ስጋትጋት ገለጹ የሚሊና ሌሎችም ዜናዎች የተካተቱበት ሙሉ ፕሮግራሙን ያድምጡት

በተለጣፊው መኢአድ ስም የተጠራው ጉባዔ የስርዓቱ ሕገ ወጥ ተግባር አካል መሆኑን ተቃባይነት እንደሌለው ሕጋዊው የፓርቲው ፕሬዝዳንት ገለጹ

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ለዓለም ጤና ድርጅት መሪነት እሾማለሁ ማለት በአገሪቱ ለሚደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በጤና ስም ሲደረግ የነበረውን ሙስና መደገፍ ነው ሲሉ ከአገር ቤት አንድ የተቃዋሚ መሪ ገለጹ

የኢትዮጵያው አገዛዝ የኤርትራ ተቃወሚዎችን በገንዘብ ለመርዳትና ለማደራጀት መወሰኑ ታወቀ

በሜዲትራኒያን ባህር ሰሞኑን የሰጠሙት ስደተኞች ቁጥር ከሰባት መቶ በላይ ሊሆን እንደሚችል ስጋት አለ

የስፔኑ ሃያል የእግር ኳስ ቡድን ሪያል ማድሪድ ኣትሌቲኮ ማድሪድን  በማሸነፈ በአውሮፓ ሻምፒዮና  ውድድር ታሪክ ሰራ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የባፍሎ ዓመታዊ የማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆኑ

እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ፡30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-052916

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *