Hiber Radio: የኤርትራ መንግስት በጾረና ግንባር የሕወሓት ወታደሮች ጥቃት ሰነዘሩ ሲል የኢትዮጵያው አገዛዝ የካደውን ጦርነት ይፋ አደረገ፣የአገዛዙየሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት በሕግ ፊት ተቀባይነት የለውም ተባለ፣አሜሪካ ኤርትራ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር እንድትተባበር ጥረት አደርጋለሁ አለች፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች የመከፋፈል አደጋ አንዣቦባቸዋል ተባለ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎችና ልዩ ልዩ ወቅታዊ ዝግጅቶች ተካተዋል

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሰኔ 5  ቀን 2008 ፕሮግራም

<…በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ግድያ ፣በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ በአደባባይ ሲፈጸም የነበረው ቶርች፣ወታደሮች በግልጽ ሲገሉ ሲተኩሱ ጭምር እየታየ ይሄ ስርዓቱ የፈጠረው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተመጣጣኝ እርምጃ ነው የወሰደው ማለቱ የሚያሳፍር ሪፖርቱም ተቀባይነት የሌለውና ራሳቸው ይሄን ተቋም በገንዘብ የሚደግፉም ምዕራባውያን ጭምር የማይቀበሉት ነውአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ አካባቢ አንዳንዴ የፓርላማ አባላቱ አንዱ እኔ ለኦጋዴን መብት ብቻ ነው ብሎ ይጠይቃል፣ሌላው እኔ ለኦሮሞ ብቻ አንዱ ደሞ እኔ ለዚህ ብቻ ይላል ይሄን ማስተካከልና ቢያንስ በደላችንን ለማሰማትና ለመደመጥ መተባበር አለብን።ይህ ካልሆነ ግን…> አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም መቀመጫውን ቤልጂየም ያደረገው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ የሚሰራው ማህበር ዋና ዳይሬክተር የአገዛዙ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን ያወጣውን ሪፖርትና የፓርላማውን ውሳኔ በተመለከተ ከሰጠን  ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…የወያኔ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት ራሳቸው ገለው ራሳቸው አጣሪ የሆኑበት ጉዳይ በምንም መንገድ ተቀባይነት የለውም። ሌላው ቀርቶ አቶ ሀይለማሪያም በፓርላማ ስህተቱ የእኛ ነው ሲል የነበረውን የካደ በኦሮሚያ በንጹሃን ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ተመጣጣኝ እርምጃ ነው ያለ በየትኛውም ሕግ ፊት ተቀባይነት የሌለው ሪፖርት ነውበሕግ መርህ አንድን ጉዳይ ራሱ ባለጉዳዩ ወይም በደል ፈጻሚው አያጣራም በገለልተኛ አካል ነው መጣራት ያለበት የወያኔ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን የራሱን ወንጀል ለመሸፈን ያልቻለ ተራ ሪፖርት ነው። ይሄን ተቀባይነት የሌለው ሪፖርት ግን መቃወምና የሚፈጸመው የሰብኣዊ መብት ጥሰት ላይ ትርጉም ያለው ተጽዕኖ እንዲደረግ በጋራ ድምጻችንን ማሰማት አለብን።… > አቶ ነጌሳ ኦዶ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ) ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማህበር ሊቀመንበር የአገዛዙ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርትና የፓርላማ ውሳኔ  ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

 <…የታክስ ወቅት መጥቶ ባለፈ  ቁጥር በየዓመቱ የተለያዩ የማጭበርበር ስልቶች ተግባራዊ ይሆናሉ አይ.አር.ኤስ ሳይቀር ዘንድሮ ከፍተኛ ማጭበርበር ደርሶበታል። ህብረተሰባችን ለእነዚህ በተለያየ መንገድ መረጃችን እጃቸው ለሚገባ አጭበርባሪዎች መጠንቀቅ አለበት።እነዚህ ተጭበርብረው ቀርበው ራሳቸውን ማስተማሪያ ያደረጉትን ከእኛ ስህተት ሌላው ይማር ያሉትን ሳላመሰግን አላልፍም…> አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ ቲኬ ሾው አዘጋጅ በኤይ.አር.ኤስ ስም ስለሚያጭበረብሩ ካደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያድምጡት)

ሟቹ መለስ ዜናዊ የቀመሩት የተቃዋሚዎች  እግሮችን የመቁረጥ እቅድ ከኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ(ኦፊኮ)ቢሮ ዘልቋል።በርካታ የኦሮሞ ታጋዮች በሰበብ ባስባቡ ወደ እስርቤት ሲወረወሩ የፓርቲው  መሪው / መረራ ጉዲና ግን እስከ አሁን ድረስ ለምን አልታሰሩም ? / መረራ ለጥያቄው  አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተውበታል (ልዩ ጥንቅር)

በፍሎሪዳ በኢሚግሬሽን እስር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን መካከል ከእስር ቤት ከወጣው ከአንዱ ጋር ያደረግነው አጭር ቆይታ(ያድምጡት)

በቬጋስ የሁበርና ሊፍት አሽከርካሪዎች ኩባንያዎቹ የገቡትን ቃል ለመፈጸም አልቻሉም ራሳችንን በማህበር  ማደራጀት አለብን ብለዋል(መልዕክታቸውን ይዘናል)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

የኤርትራ መንግስት በጾረና ግንባር የሕወሓት ወታደሮች ጥቃት ሰነዘሩ ሲል የኢትዮጵያው አገዛዝ የካደውን ጦርነት ይፋ አደረገ

የአገዛዙ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰሞኑ ሪፖርትና የፓርላማ ውሳኔ  በሕግ ፊት ተቀባይነት እንደሌለው ተገለጸ

በኢትዮጵያ አትሌቶች መካከል የመከፋፈል ደመና ማንጃበቡ ተሰማ

“ፌዴሬሽኑ ለብራዚሉ የኦሎምፒክ ውድድር የመረጣቸው አትሌቶች እራሳቸውን ከአነ አትሌት ሃይሌ እና ከእነ ቀነኒሳ እራቁ፣

“አትሌቶቹ ወደዚህ ለምን እንዳልመጡ ጠንቅቀን እናውቃለን”አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ

በአውስትራሊያ ሜልቦርን አቶ አባይ ወልዱ የተገኙበት ስብሰባ በተቃው ተበተነ

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኤርትራ መንግስት ላይ ያወጣው ሰሞነኛ ሪፖርት ምሁራኖችን እያነጋገር ነው

አሜሪካ ኤርትራ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር እንደትተባበር ጥረት አደርጋለሁ አለች

በኢትዮጵያ ውስጥ 5.5 ሚሊዮን ህጻናት ለጉልበት ብዛበዛ መዳረጋቸው ታወቀ

የተመድ እና ግብጽ በሶማሊያ ስለወደቁት 60 የኢትዮጵያ  መከላከያ ሰራዊት አባላት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

የኢሕአዲግ መንግስት ግንየሞተብኝ ሆነ የቆሰለብኝ ወታደር የለም  ፣በአልሽባብ ላይም ድልን ተቀዳጅቻለሁይላል

እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-061216

One Comment on “Hiber Radio: የኤርትራ መንግስት በጾረና ግንባር የሕወሓት ወታደሮች ጥቃት ሰነዘሩ ሲል የኢትዮጵያው አገዛዝ የካደውን ጦርነት ይፋ አደረገ፣የአገዛዙየሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት በሕግ ፊት ተቀባይነት የለውም ተባለ፣አሜሪካ ኤርትራ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር እንድትተባበር ጥረት አደርጋለሁ አለች፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች የመከፋፈል አደጋ አንዣቦባቸዋል ተባለ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎችና ልዩ ልዩ ወቅታዊ ዝግጅቶች ተካተዋል”

  1. በጣም ጥሩ እና ወቅታዊ መረጃዎችን አግንቸበታለሁ በዚሁ ቀጥሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *