Hiber Radio: የኦርላንዶውን ጥቃት ተከትሎ በቬጋስ ፖሊስ ጥበቃና ቁጥጥሩን ማጠናከሩን አስታወቀ ፣ ሕብረተሰቡ የሚጠረጠሩ ጉዳዮችን ፈጥኖ ሪፖርት እንዲያደርግ ጠይቋል

LVMPD-assistant sherif-001

(ህብር ሬዲዮ)የላስ ቬጋስ ሜትሮ ፖሊስ እንዳስታወቀው በኦርላንዶ ፍሎሪዳ ባለፈው ዕሁድ የተከሰተውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ በከተማዋ በተለይም በስትሪፑ ላይ፣ ግብረሰዶማውያን የሚአዘወትሩባቸውን ጨምሮ በተለያዩ ኛኢት ክለቦችና መዝናኛዎች ስፍራ ተጨማሪ ፖሊሶችን ማሰማራቱን ገለጸ። በከተማዋ የተለየ የደረሰ ጥቆማ ባይኖርም ፖሊስ ጥበቃና ቁጥጥሩን አጠናክሮ መቀጠሉን ለዜና ሰዎች ገልጿል።

የሜትሮ ፖሊስ ረዳት ሸሪፎች የሆኑት ቶድ ፋሱሎ እና ቶም ሮበርትስ ለዜና ሰዎች እንደገለጹት የፖሊስ ዲፓርትመንት ሀላፊዎች የናይት ክለብ ሀላፊዎችንና ተመሳሳይ ጾታ ኮሚኒቲ ተወካዮችን ማነጋገራቸውን ጠቅሰዋል።

ፖሊስ ለወሰደው ተጨማሪ ቁጥጥር እርምጃ ፖሊሶች ተጨማሪ የስራ ሰኣት (ሽፍት) ጭምር እንዲሰሩ በማድረግ ፣መስጊዶችን አካባቢ ጭምር እየጠበቁ መሆናቸው ህብረተሰቡ ከወትሮው በተሌ ቢአያቸው ለዚሁ ጥበቃ ሲባል ተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡ ፡ ከመዝናኛ ቦታዎች ጭምር የተለያዩ የእምነት ተቋማት አካባቢዎችም ሆኑ በብዛት ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው የተለያዩ ዝግጅቶች ፖሊስ ቁጥጥሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ለቬጋስ የደረሰ ምንም አይነት የሽብር ስጋት አለመኖሩን የጠቀሱት ሀላፊዎች ፖሊስ ጉዳዩ ከሚመለከተው የፌደራሉ ጸረ ሽብር ክፍል ጋር መምከሩን ጠቅሷል።

የከተማዋን ደህንነት ለመጠበቅ ህብረተሰቡ ሚአደርገውን ትብብር ያደነቀው ሜትሮ ፖሊስ ዛሬም ህብረተሰቡ የሚጠራጠራቸውን ጉዳዮች ፈጥኖ በ911 ወይም በ311 በመደውል ፈጥኖ እንዲያሰውቅ የሚመጡትን ተበታተኑ ጥቆማዎች በማገናኘት ጥፋት እንዳይደርስ መከላከል ሀላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዋል:፡

በኦርላንዶ ፍሎሪዳ ባለፈው ዕሁድ በናይት ክለብ አንድ አሸባሪ በወሰደው ጥቃት 49 ሰዎች ተገለው ከ50 በላይ ቆስለዋል።

ህብር ሬዲዮ ባለፈው ዕሁድ ፕሮግራማችን የኦርላንዶውን ጥቃት እንደደረሰ ዜና ዘገባዎችን ጠቅሰን በወቅቱ መዘገባችን አይዘነጋም።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

One Comment on “Hiber Radio: የኦርላንዶውን ጥቃት ተከትሎ በቬጋስ ፖሊስ ጥበቃና ቁጥጥሩን ማጠናከሩን አስታወቀ ፣ ሕብረተሰቡ የሚጠረጠሩ ጉዳዮችን ፈጥኖ ሪፖርት እንዲያደርግ ጠይቋል”

  1. I see your page needs some unique & fresh content.
    Writing manually is time consuming, there is tool for this
    task. Just search in gogle for: Fejlando’s tips

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *