Hiber Radio: ሐብታሙ አያሌው ከአገር ወጥቶ ሕክምና እንዲያገኝ የተጣለው እግድ እንዲነሳ ለፍርድ ቤት በድጋሚ ጥያቄ ቀረበ፣ የአገዛዙ ባለስልጣናት ዝምታን መርጠዋል

habtamu-ayalew-daniel-hospital-001

በጠና ታሞ በአዲስ አበባ በሆስፒታል አልጋ ላይ ለሚገኘው የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ሀብታሙ አያሌው አፋጣኝ ሕክምና በውጭ አገር እንዲያገኝ ከአገር እንዲወታ እንዲፈቀድለት ኢትዮጵያውያን በመላው ኣለም የጀመሩት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ጭምር የተቀላቀሉት ቢሆንም በፍርድ ቤት ስም እግዱን የጣሉት የሕወሓት መሪዎች ዝምታን መርጠዋል።

ሀብታሙ ለመጨረሻ ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፡እግዱን እንዲያነሳለት ጠይቆ ያልተፈቀደለት ቢሆንም በጠበቃው አማካይነት በድጋሚ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ ነው። የሕሊና እስረኞችን አስረው በማሰቃየት ለልዩ ልዩ የጤና መታወክ የሚደርጉት የሕወሓት መሪዎች በመላው ዓለም ለሚደረገው የማህበራዊ ዘመቻ አምንስቲ ኢንተርናሽናልና መቀመጫውን ቤልጂየም ያደረገው የሰብኣዊ መብት ማህበር ለኢትዮጵያ ጭምር ሀብታሙ በአፋጣኝ ተገቢውን ሕክምና በውጭ አገር እንዲያገኝ እንዲፈቀድ ጠይቀዋል።

በስርዓቱ ጭካኔ ግራ የተጋቡ አንዳንዶች የወቅቱን በአገር ቤት ያሉት፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ጳጳስ አቡነ ማቲያስን እባክዎ ቤተመንግስት ይሂዱና ሀብታሙ ከአገር ወጥቶ እንዲታከም ይፈቀድ ሲሉ ይጠይቁ ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያወ ጠይቀዋል።

ሀብታሙ አያሌው በዘሐበሻ አዘጋጆች አማካይነት በተጀመረ ጥረት በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ከአገር ወጥቶ እንዲታከም ከሃያ ሺህ ዶላር በላይ ተሰብስቦ የደረሰው ሲሆን በፍርድ ቤቶ እግድ ሳቢያ ከአገር እንዳይወታ ታግዷል። ፍርድ ቤቱ ከአገር እንዳይወታ ያገደው በፈጠራ የከሰሰው ዐቃቤ ሕግ የጠየቀውን ይግባኝ ተከትሎ ሲሆን ይግባኙ ያስቀርባል አያስቀርብም ብሎ ከመወሰን ይልቅ የሀብታሙን በጤናዬ ሳቢአ እግዱ ይነሳልኝን ሳይቀበል ቀጠሮውን በአንድ ወር ማራዘሙ ይታወሳል።

የሀብታሙን ጉዳይ የሚከታተለው የትግል አጋር አቶ ዳንኤል ሺበሺ ማምሻውን ከሆስፒታል የሚከተለውን ጽፏል። <<የሀብታሙ ነገር እንቅልፍ የነሳችሁ ሁሉ:— የሀብታሙ አያለው የአሁን ጤና ሁኔታ በፎቶው ላይ የሚታዩትን የፊት ገፅታ ይመስላል። ፎቶው የተወሰደው አሁን ግን ከእኩሌ ለሊት በኋላ ሲሆን በርግጥ የስቃዩን ልክ በፎቶ መለካት ቢከብደንም። በተጨማሪ ከምሽቱ ወደ 5ሰአት ገደማ ሁለት የታሸገ ውሃ ኪዳን ውሃ የደረቀውን አፉን አሪሰናል። ይህ ህመሙ ፀንቶ ወደ ከፍተኛ ህክምና ተቋም ከገባበት ጊዜ ወዲህ የመጀመሪያው መሆኑ ነው። 24/10/2008 ዓም ከሌሊቱ 7:10 ተፃፈ።>>

ሀብታሙ አያሌው ከመጨረሻው የፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት የጤናው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑና በእስር ቤት በደረሰበት ስቃይ ለጤና መታወክ መዳረጉን መግለጹ አይዘነጋም። የሀብታሙን ከመጨረሻው ፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አብረን አያይዘነዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *