Hiber Radio: ብጹዕ አቡነ በርናባስ መንጋዎቻቸን ከጉያቸን እየተነጠቁብን ነው ሲሉ ገለጹ፣በሎስሳንጀለስ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

La-welcome-aba-abernabas-003

በታምሩ ገዳ

በሃዋሪያዊ ጉዟቸው እና በሰበከተ ወንጌላቸው በበርካታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ምእመናኖች ዘንድ የሚታወቁት እና በስደት በምትገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ ባለፈው እሁድ አኤ አ ሰኔ 19 2016 በካሊፎርኒያው ኦክላንድ መድሃኒያለም ቤ/ክ ቅዱስ ፓትሪያርኩ ብጹ አቡነ ማርቆሪዮስ በተገኙበት በተካሄደው ባእለ ሲሜት የ ኢጲስ ቆጶስ ማእረግ እና አቡነ በርናባስ የሚል መጠሪያ ስያሜ የተሰጣቸው (የቀድሞው አባ ወልደተንሳይ) ባለፈው እሁድ ሰኔ 26 /2016 እኤአ መንበረ ጵጵስናቸው ወደ ሆነችው በሎሳንጀለስ ከተማ በምትገኘው የድንግል ማሪያም ካቴደራል በመጡበት ወቅት ብዛት ያላቸው ምእመናኖች ደማቅ እና መንፈሳዊ የሆነ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ከ12ቱ ደቀመዛሙርቶቹ መካከል አንዱ ለሆነው ለቅዱስ ጴጥሮስ “በጎቼን ጠብቅ” በማለት የሰጠውን ታልቅ ሰለጠነ ካህነነትን ምሳሌነትን ተግባራዊ ለማድረግ እና ስር አተ ቤተክርስቲያንን ለመፈጸም በብጹ አቡነ ሳሙኤል ፣ በብጹ አቡነ ያ እቆብ ፣ በብጹን ካህናት፣ በመነኮሳት፣በሰባኪያን፣ በዲያቆናት ታጀበው ወደ ቤተክርስቲያኒቱ የመጡት አቡነ በርናባስ የተለያዩ የካልፎርኒያ ግዛቶችን ጭምሮ ከፊሊክስ /አሪዞና ፣ ከላሰቪጋስ/ኒቫዳ ለከብረ በአሉ ሲሉ የተሰባሰቡ የመንፈሳዊ ልጆቻቸው እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል ነበር የተደረገላቸው ።

ከ 17 አመታት በላይ በስልጣነ ክህነት እና በሰበከተ ወንጌል አገልግሎታቸው በርካታ መንፈሳዊ ፍሬዎችን ያፈሩባት የድንግል ማሪያም ካቴደራል የሰበካ ጉባኤ (የቦርድ አባላት) ፣ መዘምራኖች እና ምእመናኖች ለብጹ አቡነ በርናባስ የተለያዩ ሃይማኖታዊ እና የመንፈስ ልጅነት መግለጫዎችን ያበረከቱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል እግዚ አብሔር የእስራኤል ህዝቦችን በመላኩ ሚካኤል አማካኝነት በሙሴ መሪነት ከግብጽ ባርነት ሲወጡ እና የቀይ ባህርን ሲሻገሩ ሙሴ ባህሩን የከፈለበት ፣ በበረሃ ውስጥ በውሃ ጥም ሲቃጠሉ ሙሴ አለቱን ከፍሎ ውሃ ያፈለቀበትን እና የግብጹ ፈርኦን አስማተኞች የላኩትን እባቦች የዋጣቸው ያ ተአምረኛ የሙሴ ብትርን የሚያወሳ (ብትረ ሙሴ )ለአቡነ በርነባስ ያበረከቱላቸው ሲሆን ለቀጣዩ ሃዋሪያዊ ጉዟቸው መታሰቢያ እና ስንቅ እንዲሆናቸው እና በመላው አለም ለሚገኙ የወንጌል ረሃብተኞች የእግዜ አብሔርን ቃል እንዲመግቡበት ይሆናቸው ዘንድ የቅዱስ ወንጌል ሰጦታን አበርክተውላቸዋል። መንፈሳዊ ሰነ ግጥም አሰምተዋል፣ ቀኔም ተቀኝተዋልቸዋል።

ሁለቱ ብጹአን ጳጳሳት፣ ብጹ አቡነ ሳሙኢል እና ብጹ አቡነ ያእቆብ ፣ካህናቱ እና ምእመናኖቹ ብጹ አቡነ በረናባስ(አባ ወልደተንሳይ) ሰለቤተከርስቲያኒቷ እና ሰለመንፈሳዊ ልጆቿ ምን እንዳደረጉ በአወደ ምህረቱ ላይ ምስክርነት የሰጡ ሲሆን ለአብነት ያህል ዛሬ ከመላው የአሜሪካ ግዛቶች እና ከተለያዩ የአለም ዳርቻዎች በሚሰባሰቡ መእመናኖች ዘንድ ተወዳጅነትን ያገኘው በሎሳንጀለስ ከተማ ውስጥ በአየእመቱ በታላቅ የሚከበረው አመታዊው የጥምቀት በአል በሎሳንጀለስ ጃል ሜዳ ክብረ በአል እንዲጎለብት፣ምእመናኖችም ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት ተደራጅተው እንዲመጡ በማድረግ ሰለሃይምኖታቸው ቀኖና ፣ዶግማ እና ህገ ቤተክርስቲያን ጠንቅቀው አንዲያውቁ በማበራታት መንፈሳዊ ሃላፊነታቸውን መወጣታቸውን መስክረውላቸዋል።

እለቱን በማሰመልከት ብጹ አቡነ ሳሙአኤል በሰጡት ምሰክርነት “ ከዛሬ ሱስት አመት በፊት ቤክርስቲያን በውስጥዊ ችግር ላይ ሳለች፣፡ ቅዱስ አባታችን ፓትሪያርኩ አቡነ ማርቆሪዮስ በጠና ህመመ በሚሰቃዩበት ወቅት የያኔው ኣባ ወልደተንሳይ የ አሁኑ ብጹ አቡነ ባርነባስ ሁሉንም ለማረጋጋት የከፈሉት መሰዋትነት የሚዘነጋ አይደለም ። አባ ወልደተንሳይም ቢሆኑ ከህመማቸው ተፈወሰው ፣ቅዱስ ፓትሪያርኩም ከሀመማቸው ተፈወሰው ለዚህ ታላቅ ሃይማኖታዊ በአለ ሰሜት ለመሾም እና ለመሾም ይበቃሉ ያለ ማንም አለነበረም።እግዜብሔር መከራውን ሁሉ ለበረከት አድርጎታል። የሎሳንጀለስ መእመናኖች እንኳን ደስ ያላችሁ።ሌሎች ቤተክርስቲያኖችም እንደእናነተ እንዲሆኑ የዘወትር ጸሎታችን እና ምኞታችን ነው።”ብለዋል

ብጹ አቡነ ያቆብ በበኩላቸው በሰጡት አሰተያየት “ ብጹ እቡነ በረናባስ(አባ ወ/ተንሰይ) ሰበሃት ለ አብ፣ ስብሃት ለ ወልድ፣ ሰበሃት ለመንፈስ ቅዱስ እያሉ የተዘጋውን የቤክርስቲያኑን በር ዛሬ ከፍተው ገብተዋል ። ይህቺ ታላቅ ቀን የተገኘችው በብዙ ውጣ ውረድ፣ በበዙ ደካም በመሆኑ እናንተ የመንፈስ ለጆቻቸው ለዚህ በመብቃታችሁ ደስ ይበላችሁ። በረናባስ የሚለው ሰያሚ የተገኘው ለሃዋሪያዊ ተጋደሎ ሲል ብዙ መሰዋትነት የከፈለው የ ታላቁ የ ወንጊል ሰባኪው የ ቅዱስ ጳወሎስ ሰያሚ በመሆኑ ይህንን ታላቅ ሰያሜ ለተሰጣቸው ለኣቡነ በረናባስ(አባ ወ/ተንሳይ)በአገልግሎት ዘመናቸውም ቢሆን ተገቢውን የ አባትነት ክብረን እንድትሰጧቸው እና እንድተረዷቸውም አደራ አላለሁ ። ብጹ አቡነ በርናባሰም ቢሆኑ ወደ ፊት የሚደቀንባቸውን ችግር እና መከራን በዚያ በታጋሹ ባህሪያቸው አማካኝነት የላሴ አንድነተና እና ሶስትነተን እየመሰከሩ መንጋዎቻቸውን ይጠብቁ ፣ የመንፈስ ልጆቾትንም በቅንነት ያገልግሉ ” በማለት አባታዊ ምክር ያሰሙ ሲሆን ሕዝበ ክርስቲያኑም ት እዛዙን በእልልታ እና በጭብጨባ ተቀብሏል።

በመቀጥለም የቤተክርስቲያኒቱ ሰባኪ እና ካህን የሆኑት ቄሰስ መላኩ በበኩላቸው” ብጹ አባታቸን አቡነ በርናባስ ይህችን ቀን ሲሸሿት ነበር የኖሩት ፣ ዛሬ ግን አግዚአብሔር ይመሰገን ቅዱስ ወንጌል ቀን ወጥቶላታል ። “በማለት ብጹ አቡነ በርናባስ ለህዝበ ክርስቲያኑ ንግግር እንዲያደርጉ ጋበዟቸው ።ብጹነታቸውም ” እኔ ዘውትር የሚታየኝ በመንፈስ ቅዱስ እገዛ የተማርኩትን ለወገኖቼ ኣና ለመንፈስ ልጆቼ ማበርከትን ነበር ፣በሕይወቴ ብዙ ፈተናዎችን አሳልፌለሁ፣ ያንን ሁሉ መንፈሳዊ እና የጤነነት ችግርን አና ፈተናን በማለፍ ከዚህ መብቃቴ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው(ሮሜ 8) እንደሚለው ከዚያ ሁሉ ከችግር እና ከመከራው ተምሬበታልሁ ። ምንም እንኳን ምኞቴ ወደ ግሪክ አገር ተጉዤ መማር እና ማገልገል ቢሆንም እግዜ አብሔር በሁለት ክርስቲያን ቤተሰቦች ላይ አድሮ በሕልሜ ሆነ በእውኔ አስቤው ከማላውቀው ከምድረ አሜሪካ አምጥቶኝ ይሀው የድንግል ማሪያም ካቴድራልን ማረፊያዩ በማድረግ በመላው አለም ላይ ተብታትነው የሚገኙት ክርስቲያን ወገኖቼን የአቅሜን ያህል ለማገልገል በቀቻለሁ ። በሰብከተ ወንጌል ጉዞዎቼ ላይ አንድም ቀን የሰው እጅ እና ፊት ሳላይ ያለ አንዳች ቅሬታ እና ማጉረምረም ሙሉ ወጪየን እየከፈላችሁ እስከዛሬ የረዳችሁኝ እና ከዚህ ያበቃችሁኝ የዚህች ካቴደራል ምእመናኖች በሙሉ እናንተ ለተቀረው ህዝበ ክርስቲያን ታላቅ ምሳሌዎች መሆናቸሁን በተገኘሁባቸው ጎባኤዎች እና አወደ ምህረቶች ላይ ምስክርነት ሰጥቻልሁ፡ወደፊትም ቢሆን እሰጣልሁ ።እኛ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን እምነት ተከታዮች ምንም እንኳን በርካታ ምእመናኖች እና ሰባኪያን ቢኖሩንም የእናንተን የመሰለ መከባበር እና ፍቅር የተላበሱ ቤተክርስቲያናት ቢበዙልን ኖሮ እንደ ቀደምትነታችን ሁሉ ከራሳችን አልፎ በሰበከተ ወንጌል እጦት ሳቢያ በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ የአፍሪካ እና የተቀረው አለም ሕዝቦች እንተርፍ ነበር። የሚያሳዝነው ያንን ማድረግ ተሰኖን ፣ዛሬ የራሳችንን መንጋ(ህዝበ ክርስቲያንን)መጠበቅ አቅቶን ጥቦቶቻቸንን ከጉያቸን እየተዘረፍን ነው ያለነው ። ወደ ፊትም ቢሆን ፈጣሪ የጎደለውን ይሙላላችሁ። ለዚህ ሁሉ ላበቃኝ ለእግዜአብሔር ሰላደረገልኝ ነገር ምን እከፍለዋለሁ?(መዝ 115፡12) ። እናንተን የሰጠኝ አግዜ አብሔር ሰሙ ገናና ይሁን ከማለት ውጪ የምለው የለም።” በማለት ለህዝበ ክርስቲያኑ ያላቸው ልዩ አክብሮትን እና ምክርን ገልጸዋል።

በ ክብረ በዓሉ ላይ ከተገኙት ምእመናኖች መካከል አቶ ሞገሴ የተባሉ የካሊፎርኒያ ግዛት ነዋሪ ለዚህ ጸሃፊ ምን እንደተሰማቸው ሲገልጹ “ምንም እንኳን ወታደር እና ካህን ቋሚ አገር/መደብ የለውም እንደሚባለው ሁሉ የብጹ አቡነ በርናባስ መንፈሳዊ አገለገሎታቸው አለማቀፍ ቢሆንም በባእለ ስሜቱ ላይ መንበረ ጵጵስናቸው ከሎሳንጀለስ ደንግል ማሪያም ካቲደራል አንዲሆን ተወሰኗል መባሉን በአወደ ምህረቱ ላይ በመሰማቴ አባታቸን ብጹ አቡነ በርናባስ ከእኛ ከልጆቻቸው እርቀው ሊሄዱ ነው የሚለው ሰጋቴ በቂ ምላሽ በማግኘቱ እጅጉን ተደስቻልሁ ።”በለዋል።

ለከብረ በአሉ ሲሉ ከፊኒክስ /አሪዞና የመጡት አስካለ ማሪያም የተባሉ መእመኒት በበኩላቸው “ ዛሬ በዘመን አመጣሱ የጎጥ ፖለቲካ ምክንያት የተለከፉ ወገኖች የብጹአን አባቶችን መንፈሳዊ ከብራቸውን ሲያዋርዱ ፣ የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ስጋ እና ደሙ የሚፈተተበት /ሚስጥረ ቁረባን የሚከናወነበት አወደ ምህረት እና ቤክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ለአይን የሚዘገንን ፣ለጆሮም የሚሰቀጥጡ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ያፈነገጠ ፍጹም ክብረ ነክ ስራዎችን ሲያደርጉባቸው የሚያሳዩ አሳዣኝ ገጠመኞችን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃናት አማካኝነት መመልከት በተለመደበት በዚህ ዘመን በተቃራኒው ‘ እናንተ በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል፣እናንተ በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል’ የሚለው ቅዱስ ቃሉ በሎሳንጀለሱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የድንግል ማሪያም ካቲደራል ውስጥ በሺህ በሚቆጠሩ ም እመናኖች ፊት በተግባር ሲከናወን ለማየት በመበቃቴ ለካስ ፈጣሪ ዛሬም አልረሳንም በማለት እንድጸናና አደርጎኛል።የአባታችን የብጹ አቡነ በርነባስ ደካማቸው እና ልፋታቸውም ከንቱ አለመሆኑን ተመልክቻለሁ። “በማለት ደስታቸውን ተናግረዋል።

ከሳንዲያጎ /ካሊፎርኒያ ለክብረ በአሉ ሲሉ የመጡት ሌላይቷ ክርስቲያን እህት ወ/ሮ ስረጉተ አሰፋ በእለቱ የተሰማቸው ስሜትን ሲናገሩ “ ኢትዮጵያዊያኖችን ከአለም ዳርቻዎች በሚያሰባሰበው በካሊፎርኒያው የሎሳንጀለስ የ ጥምቀት ክብረ በአል ላይ ለአራት ጊዜያት ተገኝቻለሁ። ታዲያ የአገራቸንን የጃል ሚዳው የጥምቀት በአልን ከዚህ ያመጡት አባቶች መካከል አቡነ በርናባስ(የቀድሞው አባ ወ/ተንሳይ) አንዱ መሆናቸው ዛሬ በአወደ ምህርቱ ላይ የምስከርነት ቃል ሲሰጥበት ሰሰማ ለእኚህ ታላቅ አባት ያለኝን ልዩ ፍቅር ይበልጥ ጨምሮልኛል።ይህን የመሰለ ታሪካዊ እና መንፈሳዊ የአቀባበል ዝግጅት ላደረጉት ለሎሳንጀለስ ምእመናኖች ምስጋና የገባቸዋል።”ብለዋል።

በተያያዘ ዜና በውጪ አገር የሚገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ በቅረቡ ቅዱስ ፓትሪያርኩ አቡነ ማርቆሪዮስ በተገኙበት በካሊፎርኒያው ኦካልንድ መደሃኒያለም ቤ/ክ ውስጥ ለስድስት የሃይማኖት አባቶች የጵጵስና ሹመት በሰጡበት ወቅት ከተሹሚዎች መካከል አንዱ የሆኑት በሎሳንጀለስ (የሰላውሰኑ) የቅድስት ማሪያም ቤክርስቲያን ታላቅ አባት የሆኑት ብጹ አቡነ ቲዎፍሎስ(ዳግማዊ) የቀደሞው (አባ ጽጌ) በመጪው እሁድ ሃምሌ 3/2016 አኤ አ ብጹአን ኣባቶች በሚገኙበት ታላቅ መንፈሳዊ ዝግጅት ላይ በመገኘት የመንፈስ ለጆቻቸውን እንደሚጎበኙ የወጣው መረሃ ግብር ያመለክታል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *